የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ሰቆ​ቃወ ኤር​ም​ያስ ነቢይ 4

4
ምዕ​ራፍ 4 ።
ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ከው​ድ​ቀት በኋላ
1አሌፍ። ወርቁ እን​ዴት ደበሰ! ጥሩው ብር እን​ዴት ተለ​ወጠ!
የከ​በ​ረው ዕንቍ በጎ​ዳ​ናው ሁሉ እን​ዴት ተበ​ተነ!
2ቤት። ጥሩ ወርቅ የሚ​መ​ስሉ የከ​በሩ የጽ​ዮን ልጆች፥
የሸ​ክላ ሠሪ እጅ እንደ ሠራው እንደ ሸክላ ዕቃ እን​ዴት ተቈ​ጠሩ!
3ጋሜል። አራ​ዊት እንኳ ጡታ​ቸ​ውን ገል​ጠው ግል​ገ​ሎ​ቻ​ቸ​ውን አጠቡ፤
የወ​ገኔ ሴት ልጆች ግን እንደ ምድረ በዳ ሰጐን ጨካ​ኞች#“ጨካ​ኞች” የሚ​ለው በግ​እዝ የለም። ሆኑ።
4ዳሌጥ። ጡት የሚ​ጠ​ባው የሕ​ፃን ምላስ ከጥም የተ​ነሣ ወደ ትና​ጋው ተጣ​በቀ፤
ሕፃ​ናት እን​ጀራ ለመኑ፤ የሚ​ቈ​ር​ስ​ላ​ቸ​ውም የለም።
5ሄ። የጣ​ፈጠ ነገር ይበሉ የነ​በሩ በመ​ን​ገድ ጠፉ፤
በቀይ ግምጃ ያድጉ የነ​በሩ የፍግ ክምር አቀፉ።
6ዋው። የማ​ንም እጅ ሳይ​ወ​ድ​ቅ​ባት ድን​ገት ከተ​ገ​ለ​በ​ጠች፥
ከሰ​ዶም ኀጢ​አት ይልቅ የወ​ገኔ ሴት ልጅ ኀጢ​አት በዛች።
7ዛይ። ቅዱ​ሳ​ኖ​ችዋ ከበ​ረድ ይልቅ ነጡ፤ ከወ​ተ​ትም ይልቅ ነጡ፤
በመ​ው​ጣ​ታ​ቸ​ውም ሰን​ፔር ከሚ​ባል ዕንቍ ይልቅ ፈጽ​መው ቀሉ።
8ሔት። ፊታ​ቸው ከጥ​ቀ​ርሻ ይልቅ ጠቍ​ሮ​አል፤ በመ​ን​ገ​ድም አል​ታ​ወ​ቁም፤
ቍር​በ​ታ​ቸው ወደ አጥ​ን​ታ​ቸው ተጣ​ብ​ቆ​አል፤ ደር​ቆ​አል፤ እንደ እን​ጨ​ትም ሆኖ​አል።
9ጤት። በሰ​ይፍ የሞ​ቱት በራብ ከሞ​ቱት ይሻ​ላሉ፤
እነ​ዚህ የም​ድ​ርን ፍሬ አጥ​ተው#ግእዝ “በት​እ​ዛዘ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር” ይላል። ተወ​ግ​ተ​ውም ዐል​ፈ​ዋል።
10ዮድ። የር​ኅ​ሩ​ኆች ሴቶች እጆች ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ቀቅ​ለ​ዋል፤
የወ​ገኔ ሴት ልጅ በመ​ቀ​ጥ​ቀ​ጥዋ መብል ሆኖ​አ​ቸው።
11ካፍ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መዓ​ቱን ፈጽ​ሞ​አል፤ ጽኑ ቍጣ​ው​ንም አፍ​ስ​ሶ​አል፤
እሳ​ትን በጽ​ዮን ውስጥ አቃ​ጠለ፤ መሠ​ረ​ቷ​ንም በላች።
12ላሜድ። የም​ድር ነገ​ሥ​ታት፥ በዓ​ለ​ምም የሚ​ኖሩ ሁሉ፥
አስ​ጨ​ና​ቂና ጠላት በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በር እን​ደ​ሚ​ገባ አላ​መ​ኑም።
13ሜም። የጻ​ድ​ቃ​ንን ደም በው​ስ​ጥዋ ስላ​ፈ​ሰሱ፥
ስለ ነቢ​ያቷ ኀጢ​አ​ትና ስለ ካህ​ናቷ በደል ነው።
14ኖን። እነ​ርሱ ታው​ረው#“እነ​ርሱ” የተ​ባ​ሉት በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. “ጠባ​ቂ​ዎ​ችዋ” ተብ​ለ​ዋል። በመ​ን​ገድ ላይ ተቅ​በ​ዘ​በዙ፤
ልብ​ሳ​ቸ​ውም እን​ዳ​ይ​ዳ​ሰስ በደም ረክ​ሰ​ዋል።
15ሳም​ኬት። እና​ንተ ከር​ኩ​ሳን ራቁ፥ አስ​ተ​ም​ሩ​አ​ቸው፤ ራቁ፥ ራቁ በሉ​አ​ቸው፤ አት​ን​ኩ​አ​ቸ​ውም።
ታው​ከ​ዋ​ልና ዳግ​መኛ እን​ዳ​ይ​ኖ​ሩ​ባት ለአ​ሕ​ዛብ ንገ​ሩ​አ​ቸው።
16ዔ። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፍ​ላ​ቸው ነበረ። ነገር ግን ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አይ​መ​ለ​ከ​ታ​ቸ​ውም፤
የካ​ህ​ና​ቱን ፊት አላ​ፈ​ሩም፤ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቹ​ንም አላ​ከ​በ​ሩም።
17ፌ። በማ​ያ​ድን ወገን እያ​መ​ንን ረዳ​ታ​ችን ከንቱ ስለ ሆነ፥
እኛ ገና በሕ​ይ​ወት ሳለን ዐይ​ኖ​ቻ​ችን ጠፉ።
18ጻዴ። ልጆ​ቻ​ች​ንን ወደ አደ​ባ​ባ​ያ​ችን እን​ዳ​ይ​ወጡ ከለ​ከ​ልን፤
የም​ን​ጠ​ፋ​በት ጊዜ ደር​ሷ​ልና ዘመ​ና​ችን አለቀ፤ የም​ን​ጠ​ፋ​በ​ትም ጊዜ ቀረበ።
19ቆፍ። አሳ​ዳ​ጆ​ቻ​ችን ከሰ​ማይ ንስር ይልቅ ፈጣ​ኖች ሆኑ፤
በተ​ራ​ሮች ላይ አሳ​ደ​ዱን፤ በም​ድረ በዳም ሸመ​ቁ​ብን።
20ሬስ። ስለ እርሱ፥ “በአ​ሕ​ዛብ ውስጥ በጥ​ላው በሕ​ይ​ወት እን​ኖ​ራ​ለን” ያል​ነው፥
በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀባ፥ የሕ​ይ​ወ​ታ​ችን እስ​ት​ን​ፋስ፥ በወ​ጥ​መ​ዳ​ቸው ተያዘ።
21ሣን። በዖፅ ምድር የም​ት​ኖሪ የኤ​ዶ​ም​ያስ ሴት ልጅ ሆይ፥ ደስ ይበ​ልሽ፥ ሐሤ​ትም አድ​ርጊ፤
የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽዋ ደግሞ ወደ አንቺ ያል​ፋ​ልና፥ አን​ቺም ትሰ​ክ​ሪ​አ​ለሽ፥ ትራ​ቆ​ቻ​ለ​ሽም።
22ታው። የጽ​ዮን ሴት ልጅ ሆይ፥ በደ​ልሽ ተፈ​ጸመ፤ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አያ​ስ​ማ​ር​ክ​ሽም።
የኤ​ዶ​ም​ያስ ሴት ልጅ ሆይ፥ በደ​ል​ሽን ይጐ​በ​ኘ​ዋል፤ ኀጢ​አ​ት​ሽ​ንም ይገ​ል​ጣል።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ