የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ሰቆ​ቃወ ኤር​ም​ያስ ነቢይ 5

5
ምሕ​ረ​ትን ለማ​ግ​ኘት የቀ​ረበ ጸሎት
1አቤቱ፥ የሆ​ነ​ብ​ንን ዐስብ፤
ተመ​ል​ከት ስድ​ባ​ች​ን​ንም እይ።
2ርስ​ታ​ችን ለሌላ፥
ቤቶ​ቻ​ች​ንም ለእ​ን​ግ​ዶች ሆኑ።
3ድሀ-አደ​ጎች ሆነ​ናል፤ አባ​ትም የለ​ንም።
እና​ቶ​ቻ​ችን እንደ መበ​ለ​ቶች ሆነ​ዋል።
4ውኃ​ች​ንን በገ​ን​ዘብ ጠጣን፤
እን​ጨ​ታ​ችን በዋጋ በት​ከ​ሻ​ችን ይመ​ጣል።
5ጠላ​ቶ​ቻ​ችን አሳ​ደ​ዱን፤
እኛም ደክ​መ​ናል፤ ዕረ​ፍ​ትም የለ​ንም።
6ግብ​ፃ​ው​ያ​ንና አሦ​ራ​ው​ያን፥#ዕብ. “ለግ​ብ​ፃ​ው​ያ​ንና ለአ​ሦ​ራ​ው​ያን” ይላል።
እን​ጀ​ራን ያጠ​ግ​ቡን ዘንድ እጃ​ቸ​ውን ሰጡን።#ዕብ. “እን​ጠ​ግብ ዘንድ እጅ ሰጠን” ይላል።
7አባ​ቶ​ቻ​ችን ኀጢ​አ​ትን ሠሩ፤ ዛሬም የሉም፤
እኛም በደ​ላ​ቸ​ውን ተሸ​ከ​ምን።
8ባሪ​ያ​ዎች ሠል​ጥ​ነ​ው​ብ​ናል፤
ከእ​ጃ​ቸ​ውም የሚ​ታ​ደ​ገን የለም።
9ከም​ድረ በዳ ሰይፍ የተ​ነሣ፥
በሕ​ይ​ወ​ታ​ችን እን​ጀ​ራ​ች​ንን እና​መ​ጣ​ለን።
10ከራብ የተ​ነሣ ሰው​ነ​ታ​ችን ጠወ​ለገ፤
ቍር​በ​ታ​ች​ንም እንደ ምድጃ ጠቈረ።
11በጽ​ዮን ሴቶች፥
በይ​ሁዳ ከተ​ሞ​ችም ደና​ግል ተዋ​ረዱ።
12አለ​ቆች በእ​ጃ​ቸው ተሰ​ቀሉ፤
የሽ​ማ​ግ​ሌ​ዎ​ች​ንም ፊት አላ​ከ​በ​ሩም።
13ጐል​ማ​ሶች ወፍ​ጮን ተሸ​ከሙ፤#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ምር​ጦች በል​ቅሶ ድም​ፃ​ቸ​ውን አሰሙ” ይላል።
ልጆ​ችም በእ​ን​ጨት ደከሙ።
14ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ከአ​ደ​ባ​ባይ ጠፉ፤
ጐል​ማ​ሶ​ችም ከበ​ገ​ና​ቸው ተሻሩ።
15የል​ባ​ችን ደስታ ተሽ​ሮ​አል፤
ዘፈ​ና​ችን ወደ ልቅሶ ተለ​ው​ጦ​አል።
16የራ​ሳ​ችን አክ​ሊል ወድ​ቆ​አል፤
ኀጢ​አ​ትን ሠር​ተ​ና​ልና ወዮ​ልን!
17ስለ​ዚህ ልባ​ችን ታም​ሞ​አል፤
ስለ​ዚ​ህም ነገር ዐይ​ና​ችን ፈዝ​ዞ​አል፤
18የጽ​ዮን ተራራ ባድማ ሆና​ለ​ችና፥
ቀበ​ሮ​ዎ​ችም ተመ​ላ​ል​ሰ​ው​ባ​ታ​ልና።
19አቤቱ፥ አንተ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ትኖ​ራ​ለህ፤
ዙፋ​ን​ህም ከት​ው​ልድ እስከ ትው​ልድ ነው።
20ስለ ምን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ትረ​ሳ​ና​ለህ?
ስለ ምንስ ለረ​ዥም ዘመን ትተ​ወ​ና​ለህ?
21አቤቱ፥ ወደ አንተ መል​ሰን፤ እኛም እን​መ​ለ​ሳ​ለን፤
ዘመ​ና​ች​ንን እንደ ቀድሞ አድስ።
22ፈጽ​መህ ጥለ​ኸ​ና​ልና፤
እጅ​ግም ተቈ​ጥ​ተ​ኸ​ናል።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ