የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ኢዮብ 9

9
የኢ​ዮብ መልስ
1ኢዮ​ብም እን​ዲህ ሲል መለሰ፦
2“በእ​ው​ነት እን​ዲህ እንደ ሆነ ዐወ​ቅሁ፤
ሰውስ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ጻድቅ መሆን እን​ዴት ይች​ላል?
3ከእ​ርሱ ጋር ይከ​ራ​ከር ዘንድ ቢወ​ድድ፥
ከሺህ ነገር አን​ዱን መመ​ለስ አይ​ች​ልም።
4በልቡ ጠቢብ ነው፥ ኀይ​ለ​ኛም፥ ታላ​ቅም ነው፤
ክፉስ ሆኖ በፊቱ የቆመ ማን ነው?
5ተራ​ሮ​ችን ይነ​ቅ​ላል፤ አያ​ው​ቁ​ት​ምም፤
በቍ​ጣ​ውም ይገ​ለ​ብ​ጣ​ቸ​ዋል።
6ምድ​ርን ከሰ​ማይ በታች ከመ​ሠ​ረቷ ያና​ው​ጣ​ታል፥
ምሰ​ሶ​ዎ​ች​ዋም ይን​ቀ​ጠ​ቀ​ጣሉ።
7ፀሐ​ይን ያዝ​ዛ​ታል፥ አት​ወ​ጣ​ምም፤
ከዋ​ክ​ብ​ት​ንም ያት​ማል።
8ሰማ​ያ​ትን ብቻ​ውን ይዘ​ረ​ጋል፥
በም​ድር ላይ እን​ደ​ሚ​ሄድ በማ​ዕ​በል ላይ ይሄ​ዳል።
9ድብ#በግ​እዝ “ትርያ” በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. “ፕሊ​አዛ” ይላል። የሚ​ባ​ለ​ውን ኮከ​ብና ኦሪ​ዮን#በግ​እዝ “ደብ​ራን” በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. “ኤስ​ፕ​ሮን” ይላል። የሚ​ባ​ለ​ውን ኮከብ፥
የአ​ጥ​ቢያ ከዋ​ክ​ብ​ት​ንም፥#በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. “አር​ኩ​ቱ​ሮስ” ይላል።
በአ​ዜ​ብም በኩል ያሉ​ትን የከ​ዋ​ክ​ብት ማደ​ሪ​ያ​ዎች ፈጥ​ሮ​አል።
10ታላ​ቁ​ንና የማ​ይ​መ​ረ​መ​ረ​ውን ነገር፥
እን​ዲ​ሁም የከ​በ​ረ​ው​ንና እጅግ መል​ካም የሆ​ነ​ውን
የማ​ይ​ቈ​ጠ​ረ​ው​ንም ተአ​ም​ራት አደ​ረገ።
11እነሆ፥ ቢመ​ጣ​ብኝ አላ​የ​ውም፤
ቢያ​ል​ፍ​ብ​ኝም አላ​ው​ቀ​ውም።
12እርሱ ቢያ​ርቅ የሚ​መ​ልስ ማን ነው?
እር​ሱ​ንስ፦ ምን ታደ​ር​ጋ​ለህ? የሚ​ለው ማን ነው?
13እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እኔን ከመ​ቅ​ጣት አል​ተ​መ​ለ​ሰም፥ #ግሪክ ሰባ. ሊ. “ቍጣ​ውን ቢመ​ልስ” ይላል
ከእ​ር​ሱም የተ​ነሣ ከሰ​ማይ በታች ያሉ አና​ብ​ርት ይዋ​ረ​ዳሉ።
14ቃሌን እን​ዴት ይሰ​ማ​ኛል?
እን​ዴ​ትስ ይተ​ረ​ጕ​መ​ዋል?
15በጽ​ድቅ ብጠ​ራው፥ ባይ​ሰ​ማ​ኝም፥
የእ​ር​ሱን ፍርድ እለ​ም​ና​ለሁ።
16ብጠ​ራው፥ እር​ሱም ቢመ​ል​ስ​ልኝ ኖሮ፥
እንደ ሰማኝ አላ​ም​ንም ነበር።
17“በዐ​ውሎ ነፋስ ይቀ​ጠ​ቅ​ጠ​ኛል፤
ያለ ምክ​ን​ያት ብዙ ጊዜ ያቈ​ስ​ለ​ኛል።
18እተ​ነ​ፍስ ዘንድ አይ​ተ​ወ​ኝም፤
ነገር ግን መራራ ነገ​ርን አጥ​ግ​ቦ​ኛል።
19እርሱ በኀ​ይል ይይ​ዛ​ልና፤
ፍር​ዱን ማን ይቃ​ወ​ማል?
20ጻድቅ ብሆን አፌ ይወ​ቅ​ሰ​ኛል፤
ፍጹ​ምም ብሆን ጠማማ ያደ​ር​ገ​ኛል።
21ንጹሕ ነኝ፤ ራሴ​ንም አላ​ው​ቅም፤
ነገር ግን ሕይ​ወቴ ጠፋች።
22“ስለ​ዚህ እን​ዲህ እላ​ለሁ፦
ታላ​ቁና ኀያሉ መቅ​ሠ​ፍ​ትን ይል​ካል።#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ቍጣ ታላ​ቁ​ንና ኀይ​ለ​ኛ​ውን ያጠ​ፋል” ይላል።
23የኃ​ጥ​ኣን ሞታ​ቸው ክፉ ነውና፥
በጻ​ድ​ቃን ይስ​ቃሉ።
24በኃ​ጥ​ኣን እጅ ተሰ​ጥ​ተ​ዋ​ልና፤
የም​ድር ፈራ​ጆ​ችን ፊት ይሸ​ፍ​ናል፤
እርሱ ካል​ሆነ ማን ነው?#ግእዙ “እኔ ምን​ድን ነኝ” ይላል
25ሕይ​ወቴ ከሚ​ሮጥ ሰው ይልቅ ይፈ​ጥ​ናል፤
ይሸ​ሻል፥ መል​ካ​ም​ንም አያ​ይም።
26የመ​ር​ከብ መን​ገድ ፍለጋ፥
ወይም የሚ​በ​ርና የሚ​በ​ላ​ውን የሚ​ፈ​ልግ የን​ስር ፍለጋ እን​ደ​ማ​ይ​ታ​ወቅ ሕይ​ወቴ እን​ዲሁ ሆነ።
27እኔ ብና​ገር የሚ​ጠ​ቅ​መኝ የለም፤
ፊቴም በጩ​ኸት ወደቀ፤
28ሰው​ነ​ቶቼ ሁሉ ተነ​ዋ​ወጡ፤
እን​ግ​ዲህ ንጹሕ አድ​ር​ገህ እን​ደ​ማ​ት​ተ​ወኝ አው​ቃ​ለሁ፥
29“ኃጢ​ኣ​ተኛ ሰው ከሆ​ንሁ፤
ስለ ምን አል​ሞ​ት​ሁም?
30ብታ​ጠብ፥ እንደ በረ​ዶም ብነጻ፥
እጆ​ቼ​ንም እጅግ ባነጻ፥
31በአ​ዘ​ቅት ውስጥ ታሰ​ጥ​መ​ኛ​ለህ፤
ልብ​ሴም ይጸ​የ​ፈ​ኛል።
32የሚ​ከ​ራ​ከ​ረኝ ሰው ቢሆን ኖሮ፥
ወደ አደ​ባ​ባይ በአ​ን​ድ​ነት በሄ​ድን ነበር!
33ማዕ​ከ​ላዊ ዳኛ ቢኖር፥
በሁ​ለ​ታ​ች​ንም መካ​ከል የሚ​ሰማ ቢገኝ ኖሮ፥
34በትሩ ከእኔ ላይ በራቀ ነበር፤
ግር​ማ​ውም ባላ​ስ​ፈ​ራኝ ነበር።
35እና​ገ​ርም ነበር፤ አል​ፈ​ራ​ምም ነበር፤
የማ​ው​ቀ​ውም ነገር የለም።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ