የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ኢዮብ 10

10
1“ነፍሴ ስለ ተጨ​ነ​ቀች
ቃሌን በእ​ን​ጕ​ር​ጕሮ አሰ​ማ​ለሁ፤
ነፍ​ሴም እየ​ተ​ጨ​ነ​ቀች በም​ሬት እና​ገ​ራ​ለሁ።
2እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ዲህ እለ​ዋ​ለሁ፦
ኀጢ​ኣ​ተኛ እን​ድ​ሆን አታ​ስ​ተ​ም​ረኝ፤
ለም​ንስ እን​ደ​ዚህ ፈረ​ድ​ህ​ብኝ?
3ኀጢ​ኣ​ተኛ ብሆን በአ​ንተ ዘንድ መል​ካም ነውን?
የእ​ጅ​ህን ሥራ ቸል ብለ​ሃ​ልና፤
የኃ​ጥ​ኣ​ን​ንም ምክር ተመ​ል​ክ​ተ​ሃ​ልና።
4በውኑ የሰው ዐይን አለ​ህን?
ወይስ መዋቲ ሰው እን​ደ​ሚ​ያይ ታያ​ለ​ህን?
5ዘመ​ንህ እንደ ሰው ዘመን ነውን?
ወይስ ዓመ​ታ​ትህ እንደ ሰው ዓመ​ታት ናቸ​ውን?
6ክፋ​ቴን ትፈ​ላ​ለግ ዘንድ፥
ኀጢ​ኣ​ቴ​ንም ትመ​ረ​ምር ዘንድ፥
7ከዚህ በላይ በደ​ለኛ እን​ዳ​ል​ሆ​ንሁ፥ አንተ ታው​ቃ​ለህ።
ነግር ግን ከእ​ጅህ የሚ​ያ​መ​ልጥ ማን ነው?
8“እጆ​ችህ ፈጠ​ሩኝ፤ ሠሩ​ኝም፤
ከዚ​ያም በኋላ ዞረህ ጣል​ኸኝ።
9ከጭቃ እንደ ፈጠ​ር​ኸኝ አስብ፤
ዳግ​መ​ኛም ወደ ትቢያ ትመ​ል​ሰ​ኛ​ለህ፤
10በውኑ እንደ ወተት አላ​ፈ​ሰ​ስ​ኸ​ኝ​ምን?
እንደ እር​ጎስ አላ​ረ​ጋ​ኸ​ኝ​ምን?
11ቍር​በ​ትና ሥጋን አለ​በ​ስ​ኸኝ፤
በአ​ጥ​ን​ትና በዥ​ማ​ትም አጠ​ነ​ከ​ር​ኸኝ።
12ሕይ​ወ​ትና ቸር​ነ​ትን ሰጠ​ኸኝ።
መጐ​ብ​ኘ​ት​ህም መን​ፈ​ሴን ጠበ​ቀ​ልኝ።
13ይህ ሁሉ በአ​ንተ ዘንድ አለ።
ሁሉን ነገር ማድ​ረግ እን​ደ​ም​ት​ችል፥
የሚ​ሳ​ን​ህም እንደ ሌለ አው​ቃ​ለሁ።
14ኀጢ​ኣት ብሠራ አንተ ትጠ​ባ​በ​ቀ​ኛ​ለህ፤
ከኀ​ጢ​ኣ​ቴም ንጹሕ አታ​ደ​ር​ገ​ኝም።
15በደ​ለኛ ብሆን ወዮ​ልኝ፤
ጻድ​ቅም ብሆን ራሴን አላ​ነ​ሣም፤
ጕስ​ቍ​ል​ና​ንም ጠገ​ብ​ኋት።
16ለመ​ገ​ደል እንደ አን​በሳ ታደ​ንሁ።
ተመ​ል​ሰ​ህም ፈጽ​መህ ታጠ​ፋ​ኛ​ለህ።
17ዳግ​መ​ኛም ከጥ​ንት ጀምሮ ትመ​ረ​ም​ረ​ኛ​ለህ፤#ዕብ. “ምስ​ክ​ሮ​ችን” ሲል ግሪክ ሰባ. ሊ. ደግሞ “ሥቃ​ዮ​ችን ታድ​ስ​ብ​ኛ​ለህ” ይላል።
ታላቅ መቅ​ሠ​ፍ​ትን አመ​ጣ​ህ​ብኝ።
ፈተ​ና​ዎ​ች​ንም ላክ​ህ​ብኝ።
18“ስለ ምን ከማ​ኅ​ፀን አወ​ጣ​ኸኝ?
ዐይ​ንም ሳያ​የኝ ለምን አል​ሞ​ት​ሁም?
19እን​ዳ​ል​ነ​በ​ረስ ለምን አል​ሆ​ን​ሁም?
ከማ​ኅ​ፀ​ንም ወደ መቃ​ብር ለምን አል​ወ​ረ​ድ​ሁም?
20የሕ​ይ​ወቴ ዘመን አጭር አይ​ደ​ለ​ምን?
ጥቂት አርፍ ዘንድ ተወኝ፤
21ወደ​ማ​ል​መ​ለ​ስ​በት ስፍራ፥
ወደ ጨለ​ማና ወደ ጭጋግ ምድር፥
22የዘ​ለ​ዓ​ለም ጨለ​ማም ወደ አለ​ባት፥
ብር​ሃ​ንም ወደ​ሌ​ለ​ባት፥
ማንም የሟ​ችን ሕይ​ወት ወደ​ማ​ያ​ይ​ባት ምድር ሳል​ሄድ ጥቂት አርፍ ዘንድ ተወኝ።”

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ