የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ኤር​ም​ያስ 10

10
ባዕድ አም​ል​ኮ​ትና እው​ነ​ተኛ አም​ልኮ
1እና​ንተ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ና​ንተ ላይ የተ​ና​ገ​ረ​ውን ቃል ስሙ። 2እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “የአ​ሕ​ዛ​ብን መን​ገድ አት​ማሩ፤ ከሰ​ማይ ምል​ክ​ትም አት​ፍሩ፤ አሕ​ዛብ ከእ​ነ​ርሱ የተ​ነሣ ይፈ​ራ​ሉና። 3የአ​ሕ​ዛብ ልማድ ከንቱ ነውና፥ ከዱር በመ​ጥ​ረ​ቢያ እን​ደ​ሚ​ቈ​ረጥ፥ በሠ​ራ​ተ​ኛም እጅ እን​ደ​ሚ​ሠራ እን​ጨት ነው። 4በብ​ርና በወ​ርቅ ይለ​ብ​ጡ​ታል፤ እን​ዳ​ይ​ና​ወ​ጥም በች​ን​ካ​ርና በመ​ዶሻ ይቸ​ነ​ክ​ሩ​ታል። 5እንደ ተቀ​ረጸ ብር ናቸው፤ እነ​ር​ሱም አይ​ና​ገ​ሩም፤ መራ​መ​ድም አይ​ቻ​ላ​ቸ​ው​ምና ይሸ​ከ​ሙ​አ​ቸ​ዋል። ክፉ መሥ​ራ​ትም አይ​ቻ​ላ​ቸ​ው​ምና፥ ደግ​ሞም መል​ካም ይሠሩ ዘንድ አይ​ች​ሉ​ምና አት​ፍ​ሩ​አ​ቸው።”
6አቤቱ! እንደ አንተ ያለ የለም፤ አንተ ታላቅ ነህ ስም​ህም በኀ​ይል ታላቅ ነው። 7የአ​ሕ​ዛብ ንጉሥ ሆይ! በአ​ሕ​ዛብ ጥበ​በ​ኞች ሁሉ መካ​ከል፥ በመ​ን​ግ​ሥ​ታ​ቸ​ውም ሁሉ እንደ አንተ ያለ ስለ​ሌለ፥ ለአ​ንተ ክብር ይገ​ባ​ልና አን​ተን የማ​ይ​ፈራ ማን ነው? 8በአ​ንድ ጊዜ ሰን​ፈ​ዋል፥ ደን​ቍ​ረ​ው​ማል፤ ጣዖ​ታት የሚ​ያ​ስ​ተ​ም​ሩት የእ​ን​ጨት ነገር ብቻ ነው። 9የሠ​ራ​ተ​ኛና የአ​ን​ጥ​ረኛ እጅ ሥራ የሆነ ከተ​ር​ሴስ ጥፍ​ጥፍ ብር፥ ከአ​ፌ​ዝም ወርቅ ይመ​ጣል፤ ልብ​ሳ​ቸ​ውም ሰማ​ያ​ዊና ቀይ ግምጃ ነው፤ ሁሉም የብ​ል​ሃ​ተ​ኞች ሥራ ናቸው። 10እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን እው​ነ​ተኛ አም​ላክ ነው፤ እር​ሱም ሕያው አም​ላ​ክና የዘ​ለ​ዓ​ለም ንጉሥ ነው፤ ከቍ​ጣው የተ​ነሣ ምድር ትን​ቀ​ጠ​ቀ​ጣ​ለች፤ አሕ​ዛ​ብም መዓ​ቱን አይ​ች​ሉም። #ምዕ. 10 ከቍ. 5 እስከ 8 እና ቍ. 10 በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም
11እና​ን​ተም፦ ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን ያል​ፈ​ጠሩ እነ​ዚህ አማ​ል​ክት ከም​ድር ላይ፥ ከሰ​ማ​ይም በታች ፈጽ​መው ይጥፉ ትሉ​አ​ቸ​ዋ​ላ​ችሁ።
12ምድ​ርን በኀ​ይሉ የፈ​ጠረ፥ ዓለ​ሙን በጥ​በቡ ያጸና፥ ሰማ​ያ​ት​ንም በማ​ስ​ተ​ዋሉ የዘ​ረጋ እርሱ ነው። 13በላይ በሰ​ማይ ውኆ​ችን ይሰ​በ​ስ​ባል፤ ከም​ድ​ርም ዳርቻ ደመ​ና​ትን ከፍ ያደ​ር​ጋል፤ ለዝ​ና​ብም መብ​ረ​ቅን ያደ​ር​ጋል፤ ነፋ​ስ​ንም ከቤተ መዛ​ግ​ብቱ ያወ​ጣል። 14ሰው ሁሉ ዕው​ቀት አጥቶ ሰን​ፎ​አል፤ አን​ጥ​ረ​ኛም ሁሉ ከቀ​ረ​ጸው ምስል የተ​ነሣ አፍ​ሮ​አል፤ ቀልጦ የተ​ሠራ ምስሉ ውሸት ነውና፥ እስ​ት​ን​ፋ​ስም የለ​ው​ምና። 15አገ​ጣ​ጥ​መው የሚ​ሠ​ሩት ሥራ ከንቱ ነው፤ በተ​ጐ​በኙ ጊዜም ይጠ​ፋሉ። 16የያ​ዕ​ቆብ ዕድል ፈንታ እንደ እነ​ዚህ አይ​ደ​ለም፤ እርሱ ሁሉን የፈ​ጠረ ነውና እስ​ራ​ኤ​ልም የር​ስቱ ነገድ ነውና፤ ስሙም የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው።
ስለ​ሚ​መ​ጣው ስደት
17በም​ሽግ ውስጥ የተ​ቀ​መ​ጥሽ ሆይ! ኀይ​ል​ሽን ከውጭ ሰብ​ስቢ፤ 18እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፦ እነሆ በም​ድ​ሪቱ የሚ​ኖ​ሩ​ትን በመ​ከራ አሰ​ና​ክ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ መቅ​ሠ​ፍ​ት​ሽም እን​ዲ​ያ​ገ​ኛ​ቸው#ዕብ. “እስ​ኪ​ሰ​ማ​ቸው ድረስ በዚህ ጊዜ እወ​ነ​ጭ​ፋ​ቸ​ዋ​ለሁ” ይላል። አስ​ጨ​ን​ቃ​ቸ​ዋ​ለሁ።
19ስለ ስብ​ራቴ ወዮ​ልኝ! ቍስ​ሌም ክፉ ነው፤ እኔ ግን፦ በእ​ው​ነት የመ​ከራ ቁስሌ ነው፤ እር​ሱ​ንም መሸ​ከም ይገ​ባ​ኛል አልሁ። 20ድን​ኳ​ኔም ተበ​ዘ​በዘ፤ አው​ታ​ሬም ሁሉ ተቈ​ረጠ፤ ልጆ​ችና በጎ​ችም የሉም#ዕብ. “ልጆ​ችም ከእኔ ወጥ​ተው ሄደ​ዋል” ይላል። ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ለድ​ን​ኳ​ኔም ቦታ የለም ለመ​ን​ጎ​ችም መሰ​ማ​ሪያ የለም፤#ዕብ. “መጋ​ረ​ጃ​ዎ​ች​ንም የሚ​ያ​ነሳ የለም” ሲል ግሪክ ሰባ. ሊ. “ለመ​ጋ​ረ​ጃዬ ቦታ የለም” ይላል። 21እረ​ኞች አእ​ም​ሮ​አ​ቸ​ውን አጥ​ተ​ዋ​ልና፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አል​ፈ​ለ​ጉ​ት​ምና፤ ስለ​ዚ​ህም መሰ​ማ​ሪ​ያ​ውን አላ​ወ​ቁም፤ መን​ጎ​ቻ​ቸ​ውም ሁሉ ተበ​ት​ነ​ዋል። 22የወሬ ድምፅ ተሰማ፤ እነ​ሆም የይ​ሁ​ዳን ከተ​ሞች ባድ​ማና የሰ​ገኖ ማደ​ሪያ ያደ​ር​ጋ​ቸው ዘንድ ከሰ​ሜን ምድር ታላቅ መነ​ዋ​ወጥ መጥ​ቶ​አል።
23አቤቱ! የሰው መን​ገድ ከራሱ እንደ አይ​ደለ አው​ቃ​ለሁ፤ ሰውም አይ​ሄ​ድ​ባ​ትም፤ መን​ገ​ዱ​ንም ጥር​ጊያ አላ​ደ​ረ​ገም። 24አቤቱ! ቅጣን፤ ነገር ግን ፈጽ​መህ እን​ዳ​ታ​ጠ​ፋን በፍ​ር​ድህ ይሁን እንጂ በቍ​ጣህ አይ​ሁን። 25ያዕ​ቆ​ብን በል​ተ​ው​ታ​ልና፥ አጥ​ፍ​ተ​ው​ት​ማ​ልና፥ ማደ​ሪ​ያ​ው​ንም አፍ​ር​ሰ​ዋ​ልና በማ​ያ​ው​ቁህ አሕ​ዛብ፥ ስም​ህ​ንም በማ​ይ​ጠሩ ትው​ልድ#ግእዝ “ስም​ህን በማ​ት​ጠራ መን​ግ​ሥት” ይላል። ላይ መዓ​ት​ህን አፍ​ስስ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ