የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ኤር​ም​ያስ 9

9
1ስለ ተገ​ደሉ ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ሰዎች ሌሊ​ትና ቀን አለ​ቅስ ዘንድ ለራሴ ውኃን፥ ለዐ​ይ​ኔም የዕ​ን​ባን ምንጭ ማን በሰ​ጠኝ? 2ሁሉም አመ​ን​ዝ​ሮች፥ የዐ​መ​ጸ​ኞች ጉባኤ ናቸ​ውና ሕዝ​ቤን እተ​ዋ​ቸው ዘንድ ከእ​ነ​ር​ሱም እለይ ዘንድ በም​ድረ በዳ ማደ​ሪ​ያን ማን በሰ​ጠኝ? 3“ምላ​ሳ​ቸ​ውን ለሐ​ሰት እንደ ቀስት ገተሩ፤ በም​ድ​ርም በረቱ፤ ነገር ግን ለእ​ው​ነት አይ​ደ​ለም፤ ከክ​ፋት ወደ ክፋት ይሄ​ዳ​ሉና፥ እኔ​ንም አላ​ወ​ቁ​ምና፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። 4ወን​ድ​ምም ሁሉ ያሰ​ና​ክ​ላ​ልና፥ ባል​ን​ጀ​ራም ሁሉ በጠ​ማ​ማ​ነት ይሄ​ዳ​ልና እና​ንተ ሁሉ ከባ​ል​ን​ጀ​ሮ​ቻ​ችሁ ተጠ​ን​ቀቁ፤ በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁም አት​ታ​መኑ። 5እያ​ን​ዳ​ንዱ በባ​ል​ን​ጀ​ራው ላይ ይሣ​ለ​ቃል#ዕብ. “ሰውም ሁሉ ባል​ን​ጀ​ራ​ውን ያታ​ል​ላል” ይላል። በእ​ው​ነ​ትም አይ​ና​ገ​ርም፤ ሐሰት መና​ገ​ር​ንም ምላ​ሳ​ቸው ተም​ሮ​አል፤ በደሉ መመ​ለ​ስ​ንም እንቢ አሉ። 6አራ​ጣ​ንም በአ​ራጣ ላይ ይቀ​በ​ላሉ፤ ተን​ኰ​ልን በተ​ን​ኰል ላይ ይሠ​ራሉ፤ “እኔ​ንም ያው​ቁኝ ዘንድ እንቢ ብለ​ዋል፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።
7ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ፥ አቀ​ል​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እፈ​ት​ና​ቸ​ው​ማ​ለሁ፤ ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ክፋት እን​ደ​ዚሁ አደ​ር​ጋ​ለ​ሁና። 8ምላ​ሳ​ቸው የተ​ሳለ ፍላጻ ነው፤ ንግ​ግ​ራ​ቸው ሽን​ገላ ነው፤ ለባ​ል​ን​ጀ​ራ​ቸው ሰላ​ምን ይና​ገ​ራሉ፤ በል​ባ​ቸው ግን ጥላ​ቻን ይይ​ዛሉ። 9በውኑ ስለ​ዚህ ነገር በመ​ቅ​ሠ​ፍት አል​ጐ​በ​ኝ​ምን? ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ነፍ​ሴስ እን​ደ​ዚህ ባለ ሕዝብ ላይ አት​በ​ቀ​ል​ምን?
10በተ​ራ​ሮቹ ላይ አል​ቅሱ፤ በም​ድረ በዳም ጎዳና ላይ እዘኑ፤ ሰው ጠፍ​ት​ዋ​ልና፤ የሚ​መ​ላ​ለ​ስም የለ​ምና ሙሾ​ው​ንም አሙሹ፤ የሰ​ማይ ወፍ ድም​ፅ​ንም እስከ ከብት ድምፅ ድረስ አይ​ሰ​ሙም፤ ደን​ግ​ጠ​ውም ተማ​ር​ከው ሄዱ። 11ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም የፍ​ር​ስ​ራሽ ክምር፥ የቀ​በ​ሮም ማደ​ሪያ አደ​ር​ጋ​ታ​ለሁ፤ የይ​ሁ​ዳ​ንም ከተ​ሞች ሰው እን​ዳ​ይ​ቀ​መ​ጥ​ባ​ቸው አጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለሁ።
12ይህን የሚ​ያ​ስ​ተ​ውል ጠቢብ ሰው ማን ነው? ያወ​ራስ ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አፍ ለማን ተና​ገረ? ሰው እን​ዳ​ያ​ል​ፍ​ባት ምድ​ርስ ስለ ምን ጠፋች፤ እንደ ምድረ በዳስ ስለ ምን ተቃ​ጠ​ለች? 13እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ አለኝ፦ ሕዝቤ በፊ​ታ​ቸው የሰ​ጠ​ኋ​ቸ​ውን ሕጌን ትተ​ዋል፤ ቃሌ​ንም አል​ሰ​ሙም። 14ነገር ግን የል​ባ​ቸ​ውን ምኞ​ትና አባ​ቶ​ቻ​ቸው ያስ​ተ​ማ​ሩ​አ​ቸ​ውን ጣዖት ተከ​ት​ለ​ዋል፤ 15ስለ​ዚህ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ፥ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ ይህን ሕዝብ መከ​ራን#ዕብ. “እሬ​ትን” ይላል። አበ​ላ​ዋ​ለሁ፤ የሐ​ሞ​ት​ንም ውኃ አጠ​ጣ​ዋ​ለሁ። 16እነ​ር​ሱና አባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም በአ​ላ​ወ​ቋ​ቸው አሕ​ዛብ መካ​ከል እበ​ት​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እስከ አጠ​ፋ​ቸ​ውም ድረስ በስተ ኋላ​ቸው ሰይ​ፍን እሰ​ድ​ድ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ።
17እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እን​ዲ​መጡ አል​ቃ​ሾች ሴቶ​ችን ጥሩ፤ ወደ ብል​ሃ​ተ​ኞች ሴቶ​ችም ላኩ፤ መጥ​ተ​ውም ይን​ገ​ሩ​አ​ችሁ፤ 18ፈጥ​ነ​ውም ሙሾ ያሙ​ሹ​ላ​ችሁ፤ ዐይ​ኖ​ቻ​ች​ሁም እን​ባን ያፍ​ስሱ፤ ከዐ​ይ​ኖ​ቻ​ች​ሁም ሽፋ​ሽ​ፍ​ቶች ውኃ ይፍ​ለቅ። 19ምድ​ርን ትተ​ና​ልና፥ ቤቶ​ቻ​ች​ን​ንም ጥለን ሄደ​ና​ልና እን​ዴት ጐሰ​ቈ​ልን! እን​ዴት አፈ​ርን! የሚል የል​ቅሶ ድምፅ በጽ​ዮን ተሰ​ም​ቶ​አል። 20እና​ንተ ሴቶች ሆይ! የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ፤ ጆሮ​አ​ች​ሁም የአ​ፉን ቃል ትቀ​በል፤ ለሴ​ቶች ልጆ​ቻ​ች​ሁም ልቅ​ሶ​ውን፥ እያ​ን​ዳ​ን​ድ​ዋም ለባ​ል​ን​ጀ​ራዋ ዋይ​ታን ታስ​ተ​ምር። 21ሕፃ​ና​ቱ​ንም በመ​ን​ገድ፤ ጐል​ማ​ሶ​ቹ​ንም በአ​ደ​ባ​ባ​ዮ​ቻ​ችን ያጠፋ ዘንድ ሞት በመ​ስ​ኮ​ቶ​ቻ​ችን ወደ ሀገ​ራ​ችን ገብ​ቶ​አ​ልና። 22የሰ​ዎ​ቻ​ች​ሁም ሬሳ እንደ ጕድፍ በእ​ርሻ ላይ፥ ማንም እን​ደ​ማ​ይ​ሰ​በ​ስ​በው ከአ​ጫ​ጆች በኋላ እን​ደ​ሚ​ቀር ቃር​ሚያ ይወ​ድ​ቃል።
23እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ጠቢብ በጥ​በቡ አይ​መካ፤ ኀያ​ልም በኀ​ይሉ አይ​መካ፤ ባለ​ጠ​ጋም በብ​ል​ጥ​ግ​ናው አይ​መካ፤ 24ነገር ግን የሚ​መ​ካው፦ ምሕ​ረ​ት​ንና ፍር​ድን፥ ጽድ​ቅ​ንም በም​ድር ላይ የማ​ደ​ርግ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሆ​ኔን በማ​ወ​ቁና በማ​ስ​ተ​ዋሉ በዚህ ይመካ፤ ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኘኝ ይህ ነውና፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።
25“እነሆ ዘመን ይመ​ጣል፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። የተ​ገ​ረ​ዙ​ት​ንና ያል​ተ​ገ​ረ​ዙ​ትን ሁሉ በአ​ን​ድ​ነት እጐ​በ​ኛ​ለሁ። 26አሕ​ዛብ ሁሉ ያል​ተ​ገ​ረዙ ናቸ​ውና፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቤት ሁሉ ልባ​ቸው ያል​ተ​ገ​ረዘ ነውና የተ​ገ​ረ​ዙ​ትን ሁሉ፥ ግብ​ጽ​ንና ይሁ​ዳን፥ ኤዶ​ም​ያ​ስ​ንም፥ የአ​ሞ​ን​ንም ልጆች፥ ሞዓ​ብ​ንም፥ በም​ድረ በዳም የተ​ቀ​መ​ጡ​ትን ጠጕ​ራ​ቸ​ውን በዙ​ሪያ የተ​ላ​ጩ​ት​ንም ሁሉ የም​ጐ​በ​ኝ​በት ዘመን እነሆ ይመ​ጣል።”

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ