ትንቢተ ኤርምያስ 10
10
ባዕድ አምልኮትና እውነተኛ አምልኮ
1እናንተ የእስራኤል ቤት ሆይ! እግዚአብሔር በእናንተ ላይ የተናገረውን ቃል ስሙ። 2እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “የአሕዛብን መንገድ አትማሩ፤ ከሰማይ ምልክትም አትፍሩ፤ አሕዛብ ከእነርሱ የተነሣ ይፈራሉና። 3የአሕዛብ ልማድ ከንቱ ነውና፥ ከዱር በመጥረቢያ እንደሚቈረጥ፥ በሠራተኛም እጅ እንደሚሠራ እንጨት ነው። 4በብርና በወርቅ ይለብጡታል፤ እንዳይናወጥም በችንካርና በመዶሻ ይቸነክሩታል። 5እንደ ተቀረጸ ብር ናቸው፤ እነርሱም አይናገሩም፤ መራመድም አይቻላቸውምና ይሸከሙአቸዋል። ክፉ መሥራትም አይቻላቸውምና፥ ደግሞም መልካም ይሠሩ ዘንድ አይችሉምና አትፍሩአቸው።”
6አቤቱ! እንደ አንተ ያለ የለም፤ አንተ ታላቅ ነህ ስምህም በኀይል ታላቅ ነው። 7የአሕዛብ ንጉሥ ሆይ! በአሕዛብ ጥበበኞች ሁሉ መካከል፥ በመንግሥታቸውም ሁሉ እንደ አንተ ያለ ስለሌለ፥ ለአንተ ክብር ይገባልና አንተን የማይፈራ ማን ነው? 8በአንድ ጊዜ ሰንፈዋል፥ ደንቍረውማል፤ ጣዖታት የሚያስተምሩት የእንጨት ነገር ብቻ ነው። 9የሠራተኛና የአንጥረኛ እጅ ሥራ የሆነ ከተርሴስ ጥፍጥፍ ብር፥ ከአፌዝም ወርቅ ይመጣል፤ ልብሳቸውም ሰማያዊና ቀይ ግምጃ ነው፤ ሁሉም የብልሃተኞች ሥራ ናቸው። 10እግዚአብሔር ግን እውነተኛ አምላክ ነው፤ እርሱም ሕያው አምላክና የዘለዓለም ንጉሥ ነው፤ ከቍጣው የተነሣ ምድር ትንቀጠቀጣለች፤ አሕዛብም መዓቱን አይችሉም። #ምዕ. 10 ከቍ. 5 እስከ 8 እና ቍ. 10 በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም
11እናንተም፦ ሰማይንና ምድርን ያልፈጠሩ እነዚህ አማልክት ከምድር ላይ፥ ከሰማይም በታች ፈጽመው ይጥፉ ትሉአቸዋላችሁ።
12ምድርን በኀይሉ የፈጠረ፥ ዓለሙን በጥበቡ ያጸና፥ ሰማያትንም በማስተዋሉ የዘረጋ እርሱ ነው። 13በላይ በሰማይ ውኆችን ይሰበስባል፤ ከምድርም ዳርቻ ደመናትን ከፍ ያደርጋል፤ ለዝናብም መብረቅን ያደርጋል፤ ነፋስንም ከቤተ መዛግብቱ ያወጣል። 14ሰው ሁሉ ዕውቀት አጥቶ ሰንፎአል፤ አንጥረኛም ሁሉ ከቀረጸው ምስል የተነሣ አፍሮአል፤ ቀልጦ የተሠራ ምስሉ ውሸት ነውና፥ እስትንፋስም የለውምና። 15አገጣጥመው የሚሠሩት ሥራ ከንቱ ነው፤ በተጐበኙ ጊዜም ይጠፋሉ። 16የያዕቆብ ዕድል ፈንታ እንደ እነዚህ አይደለም፤ እርሱ ሁሉን የፈጠረ ነውና እስራኤልም የርስቱ ነገድ ነውና፤ ስሙም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው።
ስለሚመጣው ስደት
17በምሽግ ውስጥ የተቀመጥሽ ሆይ! ኀይልሽን ከውጭ ሰብስቢ፤ 18እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ እነሆ በምድሪቱ የሚኖሩትን በመከራ አሰናክላቸዋለሁ፤ መቅሠፍትሽም እንዲያገኛቸው#ዕብ. “እስኪሰማቸው ድረስ በዚህ ጊዜ እወነጭፋቸዋለሁ” ይላል። አስጨንቃቸዋለሁ።
19ስለ ስብራቴ ወዮልኝ! ቍስሌም ክፉ ነው፤ እኔ ግን፦ በእውነት የመከራ ቁስሌ ነው፤ እርሱንም መሸከም ይገባኛል አልሁ። 20ድንኳኔም ተበዘበዘ፤ አውታሬም ሁሉ ተቈረጠ፤ ልጆችና በጎችም የሉም#ዕብ. “ልጆችም ከእኔ ወጥተው ሄደዋል” ይላል። ከእንግዲህ ወዲህ ለድንኳኔም ቦታ የለም ለመንጎችም መሰማሪያ የለም፤#ዕብ. “መጋረጃዎችንም የሚያነሳ የለም” ሲል ግሪክ ሰባ. ሊ. “ለመጋረጃዬ ቦታ የለም” ይላል። 21እረኞች አእምሮአቸውን አጥተዋልና፥ እግዚአብሔርንም አልፈለጉትምና፤ ስለዚህም መሰማሪያውን አላወቁም፤ መንጎቻቸውም ሁሉ ተበትነዋል። 22የወሬ ድምፅ ተሰማ፤ እነሆም የይሁዳን ከተሞች ባድማና የሰገኖ ማደሪያ ያደርጋቸው ዘንድ ከሰሜን ምድር ታላቅ መነዋወጥ መጥቶአል።
23አቤቱ! የሰው መንገድ ከራሱ እንደ አይደለ አውቃለሁ፤ ሰውም አይሄድባትም፤ መንገዱንም ጥርጊያ አላደረገም። 24አቤቱ! ቅጣን፤ ነገር ግን ፈጽመህ እንዳታጠፋን በፍርድህ ይሁን እንጂ በቍጣህ አይሁን። 25ያዕቆብን በልተውታልና፥ አጥፍተውትማልና፥ ማደሪያውንም አፍርሰዋልና በማያውቁህ አሕዛብ፥ ስምህንም በማይጠሩ ትውልድ#ግእዝ “ስምህን በማትጠራ መንግሥት” ይላል። ላይ መዓትህን አፍስስ።
Currently Selected:
ትንቢተ ኤርምያስ 10: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ