ትን​ቢተ ኢሳ​ይ​ያስ 65

65
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዐመ​ፀ​ኞ​ችን እን​ደ​ሚ​ቀጣ
1ያል​ፈ​ለ​ጉኝ አገ​ኙኝ፤ ላል​ጠ​የ​ቁ​ኝም ተገ​ኘሁ፤ ስሜን ላል​ጠራ ሕዝብ፥ “እነ​ሆኝ” አል​ሁት። 2በጽ​ድቅ መን​ገድ ወደ​ማ​ይ​ሄዱ፥ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን ወደ​ሚ​ከ​ተሉ ዐመ​ፀ​ኞች ሕዝብ ቀኑን ሁሉ እጆ​ችን ዘረ​ጋሁ። 3እኒህ ሕዝብ ዘወ​ትር የሚ​ያ​ስ​ቈ​ጡኝ ናቸው፤ እነ​ርሱ በአ​ት​ክ​ልት ውስጥ የሚ​ሠዉ በጡ​ብም ላይ ለአ​ጋ​ን​ንት የሚ​ያ​ጥኑ፥ 4በመ​ቃ​ብ​ርም መካ​ከል የሚ​ተኙ፥ በዋሻ ውስጥ የሚ​ያ​ልሙ፥ የእ​ሪያ ሥጋም የሚ​በሉ ናቸው። የመ​ሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸ​ውን ደምና ዕቃ​ቸ​ው​ንም ሁሉ ያረ​ክ​ሳሉ። 5“እኔ ንጹሕ ነኝና ከእኔ ራቁ፥ ወደ እኔም አት​ቅ​ረቡ” ይላሉ። ስለ​ዚ​ህም የቍ​ጣዬ ጢስ በዘ​መኑ ሁሉ እንደ እሳት ይነ​ድ​ድ​ባ​ቸ​ዋል። 6እነሆ፥ በፊቴ ተጽ​ፎ​አል፦ ኀጢ​አ​ቶ​ቻ​ች​ሁ​ንና የአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ሁን ኀጢ​አት በአ​ንድ ላይ ወደ ብብ​ታ​ቸው ፍዳ አድ​ርጌ እመ​ል​ሳ​ለሁ እንጂ ዝም አል​ልም፤ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ 7በተ​ራ​ሮ​ችም ላይ ስላ​ጠኑ፥ በኮ​ረ​ብ​ቶ​ችም ላይ ስለ አሽ​ሟ​ጠ​ጡኝ ስለ​ዚህ አስ​ቀ​ድ​መው የሠ​ሩ​ትን ሥራ​ቸ​ውን በብ​ብ​ታ​ቸው እሰ​ፍ​ራ​ለሁ።
8እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “የወ​ይን ፍሬ በዘ​ለ​ላው በተ​ገ​ኘች ጊዜ፦ በረ​ከት በእ​ር​ስዋ ላይ አለና አታ​ጥ​ፉት እን​ደ​ሚ​ባ​ለው፥ ሁሉን እን​ዳ​ላ​ጠፋ ስለ ባሪ​ያ​ዎች እን​ዲህ አደ​ር​ጋ​ለሁ። 9የያ​ዕ​ቆ​ብን ዘርና የይ​ሁ​ዳን ዘር አመ​ጣ​ለሁ፤ የተ​ቀ​ደ​ሰው ተራ​ራ​ዬ​ንም ይወ​ር​ሳሉ፤ እኔ የመ​ረ​ጥ​ኋ​ቸ​ውና ባሪ​ያ​ዎ​ችም ይወ​ር​ሱ​አ​ታል፤ በዚ​ያም ይኖ​ራሉ። 10በመ​ን​ጋው መሰ​ማ​ሪ​ያና በዛፍ መካ​ከል በአ​ኮር ሸለ​ቆና በቆ​ላ​ውም የላ​ሞች መመ​ሰ​ግያ ለፈ​ለ​ጉኝ ሕዝቤ ይሆ​ናል።
11“እና​ንተ ግን እኔን ተዋ​ች​ሁኝ፤ ቅዱ​ሱ​ንም ተራ​ራ​ዬን ረሳ​ችሁ፥ ለአ​ጋ​ን​ን​ትም ማዕድ አዘ​ጋ​ጃ​ችሁ፤ ዕድል ለተ​ባለ ጣዖ​ትም የወ​ይን ጠጅ ለመ​ጠጥ ቍር​ባን ቀዳ​ችሁ፤ 12እኔም ለሰ​ይፍ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ ሁላ​ች​ሁም በሰ​ይፍ ትገ​ደ​ላ​ላ​ችሁ፤ በፊቴ ክፉ ነገር አደ​ረ​ጋ​ችሁ፤ ያል​ወ​ደ​ድ​ሁ​ት​ንም መረ​ጣ​ችሁ እንጂ በጠ​ራ​ኋ​ችሁ ጊዜ አል​መ​ለ​ሳ​ች​ሁ​ል​ኝ​ምና፥ በተ​ና​ገ​ር​ሁም ጊዜ አል​ሰ​ማ​ች​ሁ​ኝ​ምና።”
13ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እነሆ፥ ባሪ​ያ​ዎች ይበ​ላሉ፤ እና​ንተ ግን ትራ​ባ​ላ​ችሁ፤ እነሆ፥ ባሪ​ያ​ዎች ይጠ​ጣሉ፤ እና​ንተ ግን ትጠ​ማ​ላ​ችሁ፤ እነሆ፥ ባሪ​ያ​ዎች ደስ ይላ​ቸ​ዋል፤ እና​ንተ ግን ትጐ​ሰ​ቍ​ላ​ላ​ችሁ፤ 14እነሆ፥ ባሪ​ያ​ዎች ሐሤት ያደ​ር​ጋሉ፤ እና​ንተ ግን ከል​ባ​ችሁ ኀዘን የተ​ነሣ ትጮ​ኻ​ላ​ችሁ፤ መን​ፈ​ሳ​ች​ሁም ስለ ተሰ​በረ ወዮ! ትላ​ላ​ችሁ። 15ስማ​ች​ሁ​ንም እኔ ለመ​ረ​ጥ​ኋ​ቸው ሕዝቤ ጥጋብ#ዕብ. “ርግ​ማን” ይላል። አድ​ር​ጋ​ችሁ ትተ​ዋ​ላ​ችሁ፤ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያጠ​ፋ​ች​ኋል፤ ባሪ​ያ​ዎች ግን በሐ​ዲስ ስም ይጠ​ራሉ። 16እን​ዲ​ሁም በም​ድር ላይ የተ​ባ​ረኩ ይሆ​ናሉ፤ እው​ነ​ተ​ኛ​ውን አም​ላክ ያመ​ሰ​ግ​ና​ሉና፥ በም​ድ​ርም ላይ በእ​ው​ነ​ተ​ኛው አም​ላክ ይም​ላ​ሉና፤ የቀ​ድ​ሞ​ው​ንም ጭን​ቀት ረስ​ተ​ዋ​ልና፤ በል​ቡ​ና​ቸ​ውም አያ​ስ​ቡ​ት​ምና።
17“እነሆ፥ አዲስ ሰማ​ይና አዲስ ምድር ይሆ​ና​ልና፤ የቀ​ደ​ሙ​ትም አይ​ታ​ሰ​ቡም፤ ወደ ልብም አይ​ገ​ቡም። 18ነገር ግን በው​ስ​ጥዋ ደስ​ታ​ንና ሐሤ​ትን ያገ​ኛሉ፤ እኔም ለኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ደስ​ታን ለሕ​ዝ​ቤም ሐሤ​ትን አደ​ር​ጋ​ለሁ። 19እኔም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ሐሤ​ትን አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ በሕ​ዝ​ቤም ደስ ይለ​ኛል፤ ከዚ​ያም ወዲያ የል​ቅሶ ድም​ፅና የዋ​ይታ ድምፅ በው​ስ​ጥዋ አይ​ሰ​ማም። 20ከዚ​ያም ወዲያ ጥቂት ዘመን ብቻ የሚ​ኖር ሕፃን፥ ወይም ዕድ​ሜ​ውን ያል​ፈ​ጸመ ሽማ​ግሌ አይ​ገ​ኝም፤ ጐል​ማ​ሳው የመቶ ዓመት ሆኖት ይሞ​ታ​ልና፥ ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውም የመቶ ዓመት ሆኖት የተ​ረ​ገመ ይሆ​ና​ልና። 21ቤቶ​ች​ንም ይሠ​ራሉ፤ ይቀ​መ​ጡ​ባ​ቸ​ው​ማል፤ ወይ​ኑን ይተ​ክ​ላሉ፤ ፍሬ​ው​ንም ይበ​ላሉ። 22ሌላ እን​ዲ​ቀ​መ​ጥ​በት አይ​ሠ​ሩም፤ ሌላም እን​ዲ​በ​ላው አይ​ተ​ክ​ሉም፤ የሕ​ዝቤ ዕድሜ እንደ ሕይ​ወት ዛፍ ዕድሜ ይሆ​ና​ልና፥ እኔም የመ​ረ​ጥ​ኋ​ቸው በእ​ጃ​ቸው ሥራ ረዥም ዘመን ደስ ይላ​ቸ​ዋል። 23እነ​ርሱ ከእ​ነ​ል​ጆ​ቻ​ቸው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቡሩ​ካን ዘር ናቸ​ውና በከ​ንቱ አይ​ደ​ክ​ሙም፤ ለር​ግ​ማ​ንም አይ​ወ​ል​ዱም።
24“እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ ሳይ​ጠሩ እመ​ል​ስ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ገናም ሲና​ገሩ እነሆ፥ አለሁ እላ​ቸ​ዋ​ለሁ። 25ያን​ጊዜ ተኵ​ላና በግ በአ​ን​ድ​ነት ይሰ​ማ​ራሉ፤ አን​በ​ሳም እንደ በሬ ገለባ ይበ​ላል፤ የእ​ባ​ብም መብል ትቢያ ይሆ​ናል። በተ​ቀ​ደ​ሰው ተራ​ራዬ ሁሉ አይ​ጐ​ዱም፤ አያ​ጠ​ፉ​ምም፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ