1
ትንቢተ ኢሳይያስ 65:24
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
“እንዲህም ይሆናል፤ ሳይጠሩ እመልስላቸዋለሁ፤ ገናም ሲናገሩ እነሆ፥ አለሁ እላቸዋለሁ።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
ትንቢተ ኢሳይያስ 65:17
“እነሆ፥ አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር ይሆናልና፤ የቀደሙትም አይታሰቡም፤ ወደ ልብም አይገቡም።
3
ትንቢተ ኢሳይያስ 65:23
እነርሱ ከእነልጆቻቸው የእግዚአብሔር ቡሩካን ዘር ናቸውና በከንቱ አይደክሙም፤ ለርግማንም አይወልዱም።
4
ትንቢተ ኢሳይያስ 65:22
ሌላ እንዲቀመጥበት አይሠሩም፤ ሌላም እንዲበላው አይተክሉም፤ የሕዝቤ ዕድሜ እንደ ሕይወት ዛፍ ዕድሜ ይሆናልና፥ እኔም የመረጥኋቸው በእጃቸው ሥራ ረዥም ዘመን ደስ ይላቸዋል።
5
ትንቢተ ኢሳይያስ 65:20
ከዚያም ወዲያ ጥቂት ዘመን ብቻ የሚኖር ሕፃን፥ ወይም ዕድሜውን ያልፈጸመ ሽማግሌ አይገኝም፤ ጐልማሳው የመቶ ዓመት ሆኖት ይሞታልና፥ ኀጢአተኛውም የመቶ ዓመት ሆኖት የተረገመ ይሆናልና።
6
ትንቢተ ኢሳይያስ 65:25
ያንጊዜ ተኵላና በግ በአንድነት ይሰማራሉ፤ አንበሳም እንደ በሬ ገለባ ይበላል፤ የእባብም መብል ትቢያ ይሆናል። በተቀደሰው ተራራዬ ሁሉ አይጐዱም፤ አያጠፉምም፥” ይላል እግዚአብሔር።
7
ትንቢተ ኢሳይያስ 65:19
እኔም በኢየሩሳሌም ሐሤትን አደርጋለሁ፤ በሕዝቤም ደስ ይለኛል፤ ከዚያም ወዲያ የልቅሶ ድምፅና የዋይታ ድምፅ በውስጥዋ አይሰማም።
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች