የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ኢሳ​ይ​ያስ 27

27
ስለ እስ​ራ​ኤል መዳን
1በዚ​ያም ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፈ​ጣኑ እባብ ደራ​ጎን ላይ፥ በክ​ፉ​ውም እባብ ደራ​ጎን ላይ ልዩ፥ ታላ​ቅና ብርቱ ሰይ​ፍን ያመ​ጣል። በባ​ሕ​ርም ውስጥ ያለ​ውን ዘንዶ ይገ​ድ​ለ​ዋል።
2በዚ​ያም ቀን ለተ​ወ​ደ​ደው የወ​ይን ቦታ ተቀ​ኙ​ለት። 3እኔ የጸ​ናች ከተማ ነኝ፤ አን​ድ​ዋን ከተማ ይወ​ጋሉ። በከ​ንቱ አጠ​ጣ​ኋት፤ በሌ​ሊት ትጠ​መ​ዳ​ለች፤ በቀ​ንም ግድ​ግ​ዳዋ ይወ​ድ​ቃል፤ የሚ​ያ​ነ​ሣ​ትም የለም።#ዕብ. “እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጠባ​ቂው ነኝ ፤ ሁል​ጊዜ አጠ​ጣ​ዋ​ለሁ ፤ ማንም እን​ዳ​ይ​ጐ​ዳው በሌ​ሊ​ትና በቀን እጠ​ብ​ቀ​ዋ​ለሁ” ይላል። 4ስለ ጠቡ በእ​ሳት አቃ​ጥ​ለው ዘንድ ቀር​ቃ​ሃና ሣርን ማን በሰ​ጠኝ! አሁ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ና​ገ​ረ​ውን ሁሉ ዛሬ አደ​ረገ፤ እነ​ርሱ ተቃ​ጥ​ለ​ዋ​ልና።#ዕብ. “አል​ቈ​ጣም እሾ​ህና ኩር​ን​ችት በእኔ ላይ ምነው በሰ​ልፍ በነ​በሩ፥ በእ​ነ​ርሱ ላይ ተራ​ምጄ በአ​ን​ድ​ነት ባቃ​ጠ​ል​ኋ​ቸው ነበር!” ይላል። 5በው​ስጧ የሚ​ኖሩ ይጮ​ሃሉ፤ ከእ​ርሱ ጋር ሰላ​ምን እና​ድ​ርግ፤ ከእ​ርሱ ጋር ሰላ​ምን እና​ድ​ርግ። 6በሚ​መ​ጣው ዘመን የያ​ዕ​ቆብ ልጆች ሥር ይሰ​ድ​ዳሉ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ያብ​ባል፤ በፍ​ሬ​ያ​ቸ​ውም የዓ​ለ​ሙን ፊት ይሞ​ላሉ።
7በውኑ የመ​ቱ​ትን እንደ መታ እን​ዲሁ እር​ሱን መታ​ውን? ወይስ እነ​ርሱ እንደ ተገ​ደ​ሉ​በት መገ​ደል እርሱ ተገ​ድ​ሎ​አ​ልን? 8በጠ​ብና በን​ቀት ይሰ​ዳ​ቸ​ዋል፤ በቍ​ጣና በክፉ መን​ፈስ ትገ​ሥ​ጻ​ቸው ዘንድ ትጀ​ም​ራ​ለ​ህን?#ዕብ. “ነዳ​ቸው፥ ሰደ​ዳ​ቸው፥ ቀሠ​ፋ​ቸው፥ የም​ሥ​ራቅ ነፋስ እን​ደ​ሚ​ነ​ፍ​ስ​በት ቀን በጠ​ን​ካራ ዐውሎ አስ​ወ​ገ​ዳ​ቸው” ይላል። 9ስለ​ዚ​ህም የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀ​ዶ​ችና የፀ​ሐይ ምስ​ሎች ዳግ​መኛ እን​ዳ​ይ​ነሡ የመ​ሠ​ዊ​ያ​ውን ድን​ጋይ ሁሉ እንደ ደቀቀ እንደ ኖራ ድን​ጋይ ባደ​ረገ ጊዜ ፥ እን​ዲሁ የያ​ዕ​ቆብ በደል ይሰ​ረ​ያል፤ ይህም ኀጢ​አ​ትን የማ​ስ​ወ​ገድ ፍሬ ሁሉ ነው። 10በዚ​ያም የተ​ሰ​ማ​ራው መንጋ እንደ ተተወ መንጋ ይሆ​ናል፤ ምድ​ሩም ለብዙ ዘመን መሰ​ማ​ሪያ ይሆ​ናል፤ በዚ​ያም መን​ጋው ይሰ​ማ​ራል፤ ያር​ፋ​ልም። 11ዘግ​ይቶ ይደ​ር​ቃል፤ በው​ስ​ጡም ልም​ላሜ ሁሉ አይ​ገ​ኝም፤ ከቲ​ኣሳ የም​ት​መጡ ሴቶች፥ ኑና ለሕ​ዝቤ አል​ቅሱ፤ የማ​ያ​ስ​ተ​ውል ሕዝብ ነውና፤ ስለ​ዚህ ፈጣ​ሪው አይ​ራ​ራ​ለ​ትም፤ ሠሪ​ውም ምሕ​ረት አያ​ደ​ር​ግ​ለ​ትም።
12በዚያ ቀን እን​ዲህ ይሆ​ናል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከወ​ንዝ ፈሳሽ ጀምሮ እስከ ግብፅ ወንዝ ድረስ ዐጥር ያጥ​ራል፤ እና​ን​ተም የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሆይ፥ አንድ በአ​ንድ ትሰ​በ​ሰ​ባ​ላ​ችሁ።
13በዚ​ያም ቀን እን​ዲህ ይሆ​ናል፤ ታላቅ መለ​ከት ይነ​ፋል፤ በአ​ሦ​ርም የጠፉ፥ በግ​ብፅ ምድ​ርም የተ​ሰ​ደዱ ይመ​ጣሉ፤ በተ​ቀ​ደ​ሰ​ውም ተራራ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሰ​ግ​ዳሉ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ