ትንቢተ ኢሳይያስ 18
18
ስለ ኢትዮጵያ የተነገረ
1በኢትዮጵያ ወንዞች ማዶ ላለች፥ ክንፍ ያላቸው መርከቦች ላሉባት ምድር ወዮላት! 2መልእክተኞችን በባሕር ላይ፥ ደብዳቤዎችንም በውኃ ላይ ይልካል። ፈጣኖች መልእክተኞች ወደ ረዥምና ወደ ባዕድ፥ ወደ ክፉም ሕዝብ ይሄዳሉና፤ ተስፋ የቈረጡና የተረገጡ ሕዝብ እነማን ናቸው? ዛሬ ግን የምድር ወንዞች ሁሉ፥ ሰዎች እንደሚኖሩባት ሀገር ይኖራሉ። 3በየሀገራቸው ይቀመጣሉ፤ ከተራሮች ራሶችም እንደ ዓላማ ይይዙታል፤ እንደ መለከት ድምፅም ይሰማል።
4እግዚአብሔር፥ “እንደ ቀትር ብርሃን፥ በአጨዳም ወራት እንደ ጠል ደመና በማደሪያዬ ጸጥታ ይሆናል” ብሎኛልና። 5እርሱ ከመከር በፊት አበባ በረገፈ ጊዜ የወይንም ፍሬ ጨርቋ ሲይዝ የወይኑን ቀጫጭን ዘንግ በማጭድ ይቈርጣል፤ ጫፎቹንም ይመለምላል፤ ያስወግድማል። 6ለሰማይ ወፎችና ለምድር አውሬዎችም በአንድነት ይቀራሉ፤ የሰማይ ወፎችና የምድር አውሬዎችም ሁሉ ይሰበሰቡባቸዋል። 7በዚያ ዘመን ለሠራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር፥ ከተዋረደና ከደከመ ሕዝብ፥ ከዛሬ እስከ ዘለዓለም ታላቅ ከሆነ ወገን፥ ተስፋ ከሚያደርግና ከሚረገጥ፥ በሀገሩ ወንዝ ዳር ከሚኖር ሕዝብ ዘንድ የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ስም በተጠራበት በደብረ ጽዮን እጅ መንሻ ይቀርባል።
Currently Selected:
ትንቢተ ኢሳይያስ 18: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ