ትን​ቢተ ኢሳ​ይ​ያስ 19

19
ስለ ግብፅ የተ​ነ​ገረ ትን​ቢት
1ስለ ግብፅ የተ​ነ​ገረ ራእይ። እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፈ​ጣን ደመና ተቀ​ምጦ ወደ ግብፅ ይመ​ጣል፤ የግ​ብ​ፅም የእ​ጆ​ቻ​ቸው ሥራ​ዎች#ዕብ. “ጣዖ​ታት” ይላል። በፊቱ ይዋ​ረ​ዳሉ፤ የግ​ብ​ፃ​ው​ያ​ንም ልብ በው​ስ​ጣ​ቸው ይቀ​ል​ጣል። 2“ግብ​ፃ​ው​ያን በግ​ብ​ፃ​ው​ያን ላይ ይነ​ሣሉ፤ ወን​ድ​ምም ወን​ድ​ሙን፥ ሰውም ባል​ን​ጀ​ራ​ውን ይገ​ድ​ላል፤ ከተ​ማም ከተ​ማን፥ መን​ግ​ሥ​ትም መን​ግ​ሥ​ትን ይወ​ጋል። 3የግ​ብ​ፅም መን​ፈስ በው​ስ​ጣ​ቸው ትደ​ነ​ግ​ጣ​ለች፤ ምክ​ራ​ቸ​ውን አጠ​ፋ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም አማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንና ጣዖ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን፥ ድም​ፃ​ቸ​ውን ዝቅ አድ​ር​ገው የሚ​ና​ገ​ሩ​ትን መና​ፍ​ስት ጠሪ​ዎ​ቻ​ቸ​ው​ንም ይጠ​ይ​ቃሉ። 4ግብ​ፃ​ው​ያ​ን​ንም በጨ​ካኝ ጌቶች እጅ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ለሁ፤ ጨካ​ኞች ነገ​ሥ​ታ​ትም ይገ​ዟ​ቸ​ዋል” ይላል የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። 5ግብ​ፃ​ው​ያን ከባ​ሕር ውኃን ይጠ​ጣሉ፤#ዕብ. “ውሆች ከባ​ሕር ይደ​ር​ቃሉ” ይላል። ወን​ዙም ያን​ሳል፤ ደረ​ቅም ይሆ​ናል። 6ወን​ዞ​ችም ይነ​ጥ​ፋሉ። ቦዮ​ችና መስ​ኖች ያን​ሳሉ፤ ይደ​ር​ቃ​ሉም፤ ደን​ገ​ልና ቄጤማ ይጠ​ወ​ል​ጋሉ። 7በዓ​ባይ ወንዝ ዳር ያለው መስክ፥ በዓ​ባ​ይም ወንዝ አጠ​ገብ የተ​ዘራ እርሻ ሁሉ በነ​ፋስ ይመ​ታል፤ ይደ​ር​ቃ​ልም፤ 8ዓሣ አጥ​ማ​ጆቹ ያዝ​ናሉ፤ በዓ​ባ​ይም ወንዝ መቃ​ጥን የሚ​ጥ​ሉት ሁሉ ያለ​ቅ​ሳሉ፤ በው​ኆ​ችም ላይ መረብ የሚ​ዘ​ረ​ጉት ያለ​ቅ​ሳሉ። 9የተ​ቈ​ራ​ረ​ጠ​ው​ንም መረብ የሚ​ጠ​ግኑ፥ ነጩ​ንም ልብስ የሚ​ሠሩ ሸማ​ኔ​ዎች ያፍ​ራሉ። 10በእ​ነ​ር​ሱም የሚ​ሠሩ ይሠ​ቃ​ያሉ፤ በሐር ኩብ የሚ​ነ​ግዱ ሁሉ ይቀ​ል​ጣሉ፤ ልቡ​ና​ቸ​ውም ያዝ​ናል።#ምዕ. 19 ቍ. 10 በዕብ. ልዩ​ነት አለው።
11የጣ​ኔ​ዎስ አለ​ቆች ሰነ​ፎች ይሆ​ናሉ፤ ነገ​ሥ​ታ​ትን የሚ​መ​ክሩ ጥበ​በ​ኞ​ችም ምክ​ራ​ቸው ስን​ፍና ትሆ​ና​ለች። ንጉ​ሥን፥ “እኛ የጥ​በ​በ​ኞች ልጆች፥ የቀ​ደሙ ነገ​ሥ​ታ​ትም ልጆች ነን እን​ዴት ትሉ​ታ​ላ​ችሁ?” 12አሁን ጥበ​በ​ኞ​ችህ የት አሉ? አሁን ያብ​ስ​ሩህ፤ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በግ​ብፅ ላይ ያሰ​በ​ውን እስኪ ይን​ገ​ሩህ። 13የጣ​ኔ​ዎስ አለ​ቆች አለቁ፤ የሜ​ም​ፎ​ስም አለ​ቆች ከፍ ከፍ አሉ፤ ግብ​ፃ​ው​ያን በየ​ወ​ገ​ና​ቸው ተሳ​ሳቱ።#ዕብ. “የነ​ገ​ዶ​ችዋ የማ​ዕ​ዘን ድን​ጋ​ዮች የሆኑ ግብ​ፅን አሳቱ” ይላል። 14እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ያ​ስት መን​ፈ​ስን ልኮ​ባ​ቸ​ዋ​ልና፤ ሰካ​ርም፥ ደም ያዞ​ረ​ውም እን​ዲ​ስት እን​ዲሁ ግብ​ፃ​ው​ያን በሥ​ራ​ቸው ሁሉ ሳቱ። 15ለግ​ብ​ፃ​ው​ያን ራስ ወይም ጅራት፥ መጀ​መ​ሪያ ወይም መጨ​ረሻ#ዕብ. “የሰ​ሌን ቅር​ን​ጫፍ ወይም እን​ግጫ” ይላል። ያለው ሥራ የላ​ቸ​ውም።
16በዚ​ያም ቀን የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሚ​ያ​ወ​ር​ድ​ባ​ቸው ፍር​ሀ​ትና መን​ቀ​ጥ​ቀጥ የተ​ነሣ ግብ​ፃ​ው​ያን እንደ ሴቶች ይሆ​ናሉ። 17የይ​ሁ​ዳም ምድር ግብ​ፅን የም​ታ​ስ​ደ​ነ​ግጥ ትሆ​ና​ለች፤ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከመ​ከ​ረ​ባት ምክር የተ​ነሣ ስም​ዋን የሚ​ሰማ ሁሉ ይፈ​ራል።
18በዚያ ቀን አም​ስት የግ​ብፅ ከተ​ሞች በከ​ነ​ዓን ቋንቋ ይና​ገ​ራሉ፤ በሠ​ራ​ዊት ጌታ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስም ይጠሩ ዘንድ ከተ​ሞች አንድ ይሆ​ናሉ፤ ከእ​ነ​ዚ​ህም አን​ዲቱ የጽ​ድቅ ከተማ ተብላ ትጠ​ራ​ለች።#ዕብ. “አን​ዲ​ቱም ከተማ የጥ​ፋት ከተማ ትባ​ላ​ለች” ይላል።
19በዚያ ቀን በግ​ብፅ ምድር መካ​ከል አን​ዲቱ ከተማ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ትሆ​ና​ለች፤ በዳ​ር​ቻ​ዋም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ዐ​ምድ#ግእዙ “ቤተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር” ይላል። ይሆ​ናል። 20ይህም ለሠ​ራ​ዊት ጌታ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በግ​ብፅ ምድር ለዘ​ለ​ዓ​ለም ምል​ክት ይሆ​ናል፤ ከሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቋ​ቸው የተ​ነሣ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይጮ​ኻ​ሉና፥ እር​ሱም የሚ​ያ​ድ​ና​ቸ​ውን ሰው ይል​ክ​ላ​ቸ​ዋል፤ ይፈ​ር​ዳል፤ ያድ​ና​ቸ​ዋ​ልም። 21በዚ​ያም ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በግ​ብፅ የታ​ወቀ ይሆ​ናል፤ በዚ​ያም ጊዜ ግብ​ፃ​ው​ያን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያው​ቃሉ፤ መሥ​ዋ​ዕ​ትም ያቀ​ር​ቡ​ለ​ታል፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስእ​ለት ይሳ​ላሉ፤ መባ​ኡ​ንም ያገ​ባሉ። 22እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ግብ​ፅን በታ​ላቅ መቅ​ሠ​ፍት ይመ​ታ​ታል፤ ይፈ​ው​ሳ​ታ​ልም፤ ከዚ​ያም በኋላ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ለ​ሳሉ፤ እር​ሱም ይሰ​ማ​ቸ​ዋል፤ ይፈ​ው​ሳ​ቸ​ው​ማል።
23በዚ​ያም ወራት ከግ​ብፅ ወደ አሦር መን​ገድ ይሆ​ናል፤ አሦ​ራ​ዊ​ውም ወደ ግብፅ፥ ግብ​ፃ​ዊ​ውም ወደ አሦር ይገ​ባል፤ ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም ለአ​ሦ​ራ​ው​ያን ይገ​ዛሉ። 24በዚ​ያም ወራት እስ​ራ​ኤል ለግ​ብ​ፅና ለአ​ሦር ሦስ​ተኛ ይሆ​ናል፤ በም​ድ​ርም መካ​ከል በረ​ከት ይሆ​ናል። 25የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ “በግ​ብፅ ውስጥ ያለ ሕዝቤ፥ በአ​ሦር መካ​ከ​ልም ያለ ሕዝቤ፥ ርስ​ቴም እስ​ራ​ኤል የተ​ባ​ረከ ይሁን” ብሎ ይባ​ር​ካ​ቸ​ዋ​ልና።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ