የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ኢሳ​ይ​ያስ 18

18
ስለ ኢት​ዮ​ጵያ የተ​ነ​ገረ
1በኢ​ት​ዮ​ጵያ ወን​ዞች ማዶ ላለች፥ ክንፍ ያላ​ቸው መር​ከ​ቦች ላሉ​ባት ምድር ወዮ​ላት! 2መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን በባ​ሕር ላይ፥ ደብ​ዳ​ቤ​ዎ​ች​ንም በውኃ ላይ ይል​ካል። ፈጣ​ኖች መል​እ​ክ​ተ​ኞች ወደ ረዥ​ምና ወደ ባዕድ፥ ወደ ክፉም ሕዝብ ይሄ​ዳ​ሉና፤ ተስፋ የቈ​ረ​ጡና የተ​ረ​ገጡ ሕዝብ እነ​ማን ናቸው? ዛሬ ግን የም​ድር ወን​ዞች ሁሉ፥ ሰዎች እን​ደ​ሚ​ኖ​ሩ​ባት ሀገር ይኖ​ራሉ። 3በየ​ሀ​ገ​ራ​ቸው ይቀ​መ​ጣሉ፤ ከተ​ራ​ሮች ራሶ​ችም እንደ ዓላማ ይይ​ዙ​ታል፤ እንደ መለ​ከት ድም​ፅም ይሰ​ማል።
4እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ “እንደ ቀትር ብር​ሃን፥ በአ​ጨ​ዳም ወራት እንደ ጠል ደመና በማ​ደ​ሪ​ያዬ ጸጥታ ይሆ​ናል” ብሎ​ኛ​ልና። 5እርሱ ከመ​ከር በፊት አበባ በረ​ገፈ ጊዜ የወ​ይ​ንም ፍሬ ጨርቋ ሲይዝ የወ​ይ​ኑን ቀጫ​ጭን ዘንግ በማ​ጭድ ይቈ​ር​ጣል፤ ጫፎ​ቹ​ንም ይመ​ለ​ም​ላል፤ ያስ​ወ​ግ​ድ​ማል። 6ለሰ​ማይ ወፎ​ችና ለም​ድር አው​ሬ​ዎ​ችም በአ​ን​ድ​ነት ይቀ​ራሉ፤ የሰ​ማይ ወፎ​ችና የም​ድር አው​ሬ​ዎ​ችም ሁሉ ይሰ​በ​ሰ​ቡ​ባ​ቸ​ዋል። 7በዚያ ዘመን ለሠ​ራ​ዊት ጌታ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ ከተ​ዋ​ረ​ደና ከደ​ከመ ሕዝብ፥ ከዛሬ እስከ ዘለ​ዓ​ለም ታላቅ ከሆነ ወገን፥ ተስፋ ከሚ​ያ​ደ​ር​ግና ከሚ​ረ​ገጥ፥ በሀ​ገሩ ወንዝ ዳር ከሚ​ኖር ሕዝብ ዘንድ የሠ​ራ​ዊት ጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም በተ​ጠ​ራ​በት በደ​ብረ ጽዮን እጅ መንሻ ይቀ​ር​ባል።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ