የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ሆሴዕ 8

8
የእ​ስ​ራ​ኤል ሕዝብ ጣዖት በማ​ም​ለ​ካ​ቸው መገ​ሠ​ጻ​ቸው
1በብ​ብ​ታ​ቸው እንደ መሬት፤#ዕብ. “መለ​ከ​ትን ወደ አፍህ አቅ​ርብ” ይላል። በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት እንደ ንስር ይመ​ጣል። ቃል ኪዳ​ኔን ተላ​ል​ፈ​ዋ​ልና፥ በሕ​ጌም ላይ ዐም​ፀ​ዋ​ልና። 2አም​ላክ ሆይ! እኛ እስ​ራ​ኤል#“እስ​ራ​ኤል” የሚ​ለው በዕብ. ብቻ። ዐወ​ቅ​ንህ ብለው ወደ እኔ ይጮ​ኻሉ። 3እስ​ራ​ኤል ደግ​ነ​ቱን ጥሎ​አ​ልና፤ ጠላ​ትም ያሳ​ድ​ደ​ዋ​ልና። 4ራሳ​ቸ​ውን አነ​ገሡ፤ ከእ​ኔም ዘንድ አይ​ደ​ለም፤ አለ​ቆ​ች​ንም አደ​ረጉ፤ እኔም አላ​ወ​ቅ​ሁም፤ ለጥ​ፋ​ታ​ቸ​ውም ከብ​ራ​ቸ​ውና ከወ​ር​ቃ​ቸው ጣዖ​ታ​ትን ለራ​ሳ​ቸው አደ​ረጉ። 5ሰማ​ርያ ሆይ! እም​ቦ​ሳ​ሽን መልሺ፤ ቍጣ​ዬም በላ​ያ​ቸው ነድ​ዶ​አል፤ እስከ መቼም ድረስ ንጹሕ ሊሆኑ አይ​ች​ሉም። 6ይህ ደግሞ በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ነው፤ ሠራ​ተኛ ሠራው፤ እር​ሱም አም​ላክ አይ​ደ​ለም፤ ሰማ​ርያ ሆይ! እን​ቦ​ሳሽ ተቅ​በ​ዝ​ብ​ዞ​አ​ልና። 7ነፋ​ስን ዘር​ተ​ዋ​ልና ዐውሎ ነፋ​ስን አጨዱ፤ ለነ​ዶ​አ​ቸ​ውም ኀይል የለ​ውም፤ ከፍ​ሬ​ውም ዱቄት አይ​ገ​ኝም፤ ቢገ​ኝም ጠላት ይበ​ላ​ዋል።#ዕብ. “እን​ግ​ዶች ይበ​ሉ​ታል” ይላል።
8እስ​ራ​ኤል ተው​ጦ​አል፤ በአ​ሕ​ዛ​ብም መካ​ከል ዛሬ እንደ ግትቻ ዕቃ ሆኖ​አል። 9ለብ​ቻ​ውም እን​ደ​ሚ​ቀ​መጥ እንደ ምድረ በዳ አህያ ወደ አሦር ወጥ​ተ​ዋል፤ ኤፍ​ሬ​ምም እንደ ገና ለመ​ለመ፤ እጅ መን​ሻ​ንም ወደደ። 10ስለ​ዚህ ለአ​ሕ​ዛብ አል​ፈው ይሰ​ጣሉ፤ እኔም አሁን እቀ​በ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ንጉ​ሥ​ንና አለ​ቆ​ች​ንም ይቀቡ ዘንድ ፈጽ​መው ያን​ሣሉ።
11ኤፍ​ሬም መሠ​ዊ​ያን አብ​ዝ​ቶ​አ​ልና የወ​ደ​ደው መሠ​ዊያ ለኀ​ጢ​አት ሆነ​በት። 12ብዙ ሕጎ​ችን እጽ​ፍ​ለ​ታ​ለሁ፤ ነገር ግን ሥር​ዐ​ቱና የተ​ወ​ደ​ደው መሠ​ዊ​ያው እንደ እን​ግዳ ነገር ተቈ​ጠሩ። 13መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንም ቢሠዉ፥ ሥጋ​ንም ቢበሉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አይ​ቀ​በ​ላ​ቸ​ውም፤ አሁ​ንም በደ​ላ​ቸ​ውን ያስ​ባል፤ በኀ​ጢ​አ​ታ​ቸ​ውም ይበ​ቀ​ላ​ቸ​ዋል፤ እነ​ር​ሱም ወደ ግብፅ ይመ​ለ​ሳሉ፤ በአ​ሦ​ርም ርኩስ ነገ​ርን ይበ​ላሉ። 14እስ​ራ​ኤል ፈጣ​ሪ​ውን ረስ​ቶ​አል፤ መስ​ገ​ጃ​ዎ​ች​ንም ሠር​ቶ​አል፤ ይሁ​ዳም የተ​መ​ሸ​ጉ​ትን ከተ​ሞች አብ​ዝ​ቶ​አል፤ እኔ ግን በከ​ተ​ሞች ላይ እሳ​ትን እሰ​ድ​ዳ​ለሁ፤ መሠ​ረ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ትበ​ላ​ለች።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ