የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ሆሴዕ 9

9
ሆሴዕ በእ​ስ​ራ​ኤል የሚ​ደ​ር​ሰ​ውን ቅጣት እንደ ተነ​በየ
1እስ​ራ​ኤል ሆይ! ከአ​ም​ላ​ክህ ርቀህ አመ​ን​ዝ​ረ​ሃ​ልና እንደ አሕ​ዛብ ደስ አይ​በ​ልህ፤ ሐሴ​ት​ንም አታ​ድ​ርግ፤ ከእ​ህ​ሉና ከወ​ይኑ አው​ድማ ሁሉ ይልቅ የግ​ል​ሙ​ትና ዋጋን ወድ​ደ​ሃል። 2የእ​ህሉ አው​ድ​ማና የወ​ይኑ መጭ​መ​ቂያ አላ​ወ​ቃ​ቸ​ውም፤ ወይ​ኑም ጐደ​ለ​ባ​ቸው። 3በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምድር ላይ አይ​ቀ​መ​ጡም፤ ኤፍ​ሬ​ምም በግ​ብፅ ይቀ​መ​ጣል፤#ዕብ. “ወደ ግብፅ ይመ​ለ​ሳል” ይላል። በአ​ሦ​ርም ርኩስ ነገ​ርን ይበ​ላሉ። 4ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የወ​ይን ጠጅን ቍር​ባን አያ​ቀ​ር​ቡም፤ መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸ​ውም ደስ አያ​ሰ​ኘ​ውም፤ እንደ ኀዘ​ንም እን​ጀራ ይሆ​ን​ባ​ቸ​ዋል፤ የሚ​በ​ላ​ውም ሁሉ ይረ​ክ​ሳል፤ እን​ጀ​ራ​ቸ​ውም ለሰ​ው​ነ​ታ​ቸው ይሆ​ናል እንጂ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አይ​ገ​ባም። 5በዓ​መት በዓል ቀንና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዓል ቀን ምን ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ? 6ስለ​ዚህ እነሆ ከግ​ብፅ ጕስ​ቍ​ልና የተ​ነሣ ሸሽ​ተው ይሄ​ዳሉ፤ ሜም​ፎ​ስም ትቀ​በ​ላ​ቸ​ዋ​ለች፤ በማ​ከ​ማ​ስም ይቀ​ብ​ሩ​አ​ቸ​ዋል፤ ጥፋ​ትም ወር​ቃ​ቸ​ውን#ዕብ. “ከጥ​ፋት ሸሽ​ተው ሄዱ፤ ግብ​ፅም ትሰ​በ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለች፤ ሜም​ፎ​ስም ትቀ​ብ​ራ​ቸ​ዋ​ለች ፤ ሳማም የብ​ራ​ቸ​ውን ጌጥ ይወ​ር​ሳል” ይላል። ይወ​ር​ሳል፥ እሾ​ህም በድ​ን​ኳ​ኖ​ቻ​ቸው ውስጥ ይበ​ቅ​ላል። 7የበ​ቀል ወራት መጥ​ቶ​አል፤ የፍ​ዳም ወራት ደር​ሶ​አል፤ እስ​ራ​ኤ​ልም እንደ አበደ ነቢ​ይና ርኩስ መን​ፈስ እንደ አለ​በት ሰው ይታ​መ​ማል፤ ከኀ​ጢ​አ​ት​ህና ከጠ​ላ​ት​ነ​ትህ ብዛት የተ​ነ​ሣም ቍጣ​ህን አበ​ዛህ። 8ኤፍ​ሬም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር ጉበኛ ነበረ፤ አሁን ግን ነቢዩ በመ​ን​ገዱ ሁሉ ላይ ክፉ ወጥ​መድ ሆነ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ርኵ​ሰ​ትን አደ​ረጉ። 9በጊ​ብዓ ዘመን እንደ ነበረ እጅግ ረከሱ፤ እር​ሱም በደ​ላ​ቸ​ውን ያስ​ባል፤ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ው​ንም ይበ​ቀ​ላል።
10እስ​ራ​ኤ​ልን በም​ድረ በዳ እንደ አለ ወይን ሆኖ አገ​ኘ​ሁት፤ አባ​ቶ​ቻ​ች​ሁ​ንም በመ​ጀ​መ​ሪ​ያዋ ዓመት እንደ በለስ በኵ​ራት ሆነው አየ​ኋ​ቸው፤ እነ​ርሱ ግን ወደ ብዔ​ል​ፌ​ጎር መጡ፤ ለነ​ው​ርም ተለዩ፤ እንደ ወደ​ዱ​ትም ርኩስ ሆኑ። 11ኤፍ​ሬ​ምም እንደ ወፍ በረረ፤ ክብ​ራ​ቸው ከመ​ፅ​ነ​ስና ከመ​ው​ለድ፥ ከማ​ማ​ጥም ነበር። 12ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም ቢያ​ሳ​ድጉ ከሰው ለይች ልጅ አልባ አደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ሥጋዬ ከእ​ነ​ርሱ ነውና#ዕብ. “ከእ​ነ​ርሱ በራ​ቅሁ ጊዜ” ይላል። ወዮ​ላ​ቸው! 13እኔ እንደ አየሁ የኤ​ፍ​ሬም ልጆች ለወ​ጥ​መድ ተሰ​ጥ​ተ​ዋል፤ ኤፍ​ሬ​ምም ልጆ​ቹን ወደ ገዳ​ዮች አወጣ። 14አቤቱ! ስጣ​ቸው፤ ምን ትሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለህ? መካን ማኅ​ፀ​ንን፥ የደ​ረ​ቁ​ት​ንም ጡቶች ስጣ​ቸው። 15ክፋ​ታ​ቸ​ውም ሁሉ በጌ​ል​ገላ አለ፤ በዚያ ጠል​ቻ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ስለ ሠሩት ክፋት ከቤቴ አሳ​ድ​ዳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲያ አል​ወ​ድ​ዳ​ቸ​ውም፤ አለ​ቆ​ቻ​ቸው ሁሉ ዐመ​ፀ​ኞች ናቸ​ውና። 16ኤፍ​ሬም ታመመ፤ ሥሩም ደረቀ፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲህ ፍሬ አያ​ፈ​ራም፤ ደግ​ሞም ቢወ​ልዱ የተ​ወ​ደ​ደ​ውን የማ​ኅ​ፀ​ና​ቸ​ውን ፍሬ እገ​ድ​ላ​ለሁ። 17አል​ሰ​ሙ​ት​ምና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይጥ​ላ​ቸ​ዋል፤ በአ​ሕ​ዛ​ብም መካ​ከል ተቅ​በ​ዝ​ባ​ዦች ይሆ​ናሉ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ