መጽ​ሐፈ ዕዝራ 9

9
1ይህም ከተ​ፈ​ጸመ በኋላ የሕ​ዝቡ አለ​ቆች ወደ እኔ ቀር​በው፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል ሕዝብ ካህ​ና​ቱም፥ ሌዋ​ው​ያ​ኑም፥ እንደ ከነ​ዓ​ና​ው​ያን፥ እንደ ኬጤ​ዎ​ና​ው​ያን፥ እንደ ፌር​ዜ​ዎ​ና​ው​ያን፦ እንደ ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያን፥ እንደ አሞ​ና​ው​ያን፥ እንደ ሞዓ​ባ​ው​ያን፥ እንደ ግብ​ፃ​ው​ያ​ንና እንደ አሞ​ራ​ው​ያን ርኵ​ሰት ያደ​ር​ጋሉ እንጂ ከም​ድር አሕ​ዛብ አል​ተ​ለ​ዩም፤ 2ለራ​ሳ​ቸ​ውና ለል​ጆ​ቻ​ቸ​ውም ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ወስ​ደ​ዋል፤ የተ​ቀ​ደ​ሰ​ው​ንም ዘር ከም​ድር አሕ​ዛብ ጋር ደባ​ል​ቀ​ዋል፤ አስ​ቀ​ድ​ሞም አለ​ቆ​ቹና ሹሞቹ በዚህ መተ​ላ​ለፍ መጀ​መ​ሪያ ሆነ​ዋል” አሉኝ። 3ይህ​ንም ነገር በሰ​ማሁ ጊዜ ልብ​ሴ​ንና መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያ​ዬን ቀደ​ድሁ፤ አዘ​ን​ሁም፤ የራ​ሴ​ንና የጢ​ሜ​ንም ጠጕር ነጨሁ፤ ደን​ግ​ጬም ተቀ​መ​ጥሁ። 4ስለ ምር​ኮ​ኞ​ቹም መተ​ላ​ለፍ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አም​ላክ ቃል የሚ​ፈሩ ሁሉ ወደ እኔ ተሰ​በ​ሰቡ፤ እኔም እስከ ሠርክ መሥ​ዋ​ዕት ድረስ ዐዝኜ ተቀ​መ​ጥሁ።
5በሠ​ር​ክም መሥ​ዋ​ዕት ጊዜ ልብ​ሴና መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያዬ እንደ ተቀ​ደደ ሆኖ ከመ​ዋ​ረዴ ተነ​ሣሁ፤ በጕ​ል​በ​ቴም ተን​በ​ር​ክኬ ወደ አም​ላኬ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጄን ዘረ​ጋሁ። 6እን​ዲ​ህም አልሁ፥ “አም​ላኬ ሆይ፥ ኀጢ​አ​ታ​ችን በራ​ሳ​ችን ላይ በዝ​ቶ​አ​ልና፥ በደ​ላ​ች​ንም ወደ ሰማይ ከፍ ብሎ​አ​ልና አም​ላኬ ሆይ፥ ፊቴን ወደ አንተ አነሣ ዘንድ አፍ​ራ​ለሁ፤ እፈ​ራ​ማ​ለሁ። 7ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን ዘመን ጀም​ረን እስከ ዛሬ ድረስ እጅግ በድ​ለ​ናል፤ ስለ ኀጢ​አ​ታ​ችን እኛና ልጆ​ቻ​ችን#“ልጆ​ቻ​ችን” የሚ​ለው በዕብ. የለም። ንጉ​ሦ​ቻ​ችን፥ ካህ​ና​ቶ​ቻ​ች​ንም ለሰ​ይ​ፍና ለም​ርኮ፥ ለብ​ዝ​በ​ዛና ለዕ​ፍ​ረት በአ​ሕ​ዛብ ነገ​ሥ​ታት እጅ ተጣ​ልን፤ እስከ ዛሬም ድረስ በፊ​ታ​ችን እፍ​ረት እን​ኖ​ራ​ለን። 8አሁ​ንም ቅሬታ ይተ​ዉ​ልን ዘንድ፥ በተ​ቀ​ደ​ሰ​ውም ስፍ​ራው ኀይ​ልን#ዕብ. “ችን​ካር” ይላል። ይሰ​ጠን ዘንድ፥ አም​ላ​ካ​ች​ንም ዐይ​ና​ች​ንን ያበራ ዘንድ፥ በባ​ር​ነ​ትም ሳለን ጥቂት የሕ​ይ​ወት መታ​ደ​ስን ይሰ​ጠን ዘንድ ለጥ​ቂት ጊዜ ከአ​ም​ላ​ካ​ችን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጥቂት ዕረ​ፍ​ትን አገ​ኘን። 9ባሪ​ያ​ዎቹ ነንና፥ አም​ላ​ካ​ችን ግን በባ​ር​ነ​ታ​ችን አል​ተ​ወ​ንም፤ ቀለ​ባ​ች​ንን ይሰ​ጡን ዘንድ፥ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ን​ንም ቤት ከፍ ከፍ ያደ​ርጉ ዘንድ፥ የተ​ፈ​ታ​ው​ንም ይጠ​ግኑ ዘንድ፥ በይ​ሁ​ዳና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ቅጥር ያደ​ር​ጉ​ልን ዘንድ በፋ​ርስ ነገ​ሥ​ታት ፊት ሞገ​ስን ሰጠን። 10አሁ​ንስ ከዚህ በኋላ ምን እን​ላ​ለን? አም​ላ​ካ​ችን ሆይ፥ ትእ​ዛ​ዝ​ህን ትተ​ና​ልና። 11በባ​ሮ​ችህ በነ​ቢ​ያት እጅ ያዘ​ዝ​ሃ​ትን እን​ዲህ ስትል፦ ትወ​ር​ሱ​አት ዘንድ የም​ት​ገ​ቡ​ባት ምድር በም​ድር አሕ​ዛብ ርኵ​ሰት የረ​ከ​ሰች ናት፤ በር​ኵ​ሰ​ታ​ቸ​ውም ከዳር እስከ ዳር​ቻዋ ድረስ መል​ተ​ዋ​ታል። 12አሁ​ንም ትበ​ረቱ ዘንድ፥ የም​ድ​ሩ​ንም ፍሬ ትበሉ ዘንድ፥ ልጆ​ቻ​ች​ሁም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይወ​ር​ሱ​አት ዘንድ፥ ሴቶ​ችን ልጆ​ቻ​ች​ሁን ለወ​ን​ዶች ልጆ​ቻ​ቸው አት​ስጡ፤ ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም ለወ​ን​ዶች ልጆ​ቻ​ችሁ አት​ው​ሰዱ፤ ሰላ​ማ​ቸ​ው​ንና ደኅ​ን​ነ​ታ​ቸ​ው​ንም ለዘ​ለ​ዓ​ለም አትሹ። 13ስለ ክፉ ሥራ​ች​ንና ስለ ታላቁ በደ​ላ​ችን ካገ​ኘን ነገር ሁሉ በኋላ፥ አንተ አም​ላ​ካ​ችን እንደ ኀጢ​አ​ታ​ችን ብዛት አል​ቀ​ሠ​ፍ​ኸ​ንም፤ ነገር ግን ድኅ​ነ​ትን ሰጠ​ኸን። 14ትእ​ዛ​ዝ​ህን እና​ፈ​ርስ ዘንድ ተመ​ል​ሰ​ና​ልና፥ ርኵስ ሥራ ከሚ​ሠሩ ከእ​ነ​ዚህ አሕ​ዛብ ጋርም ተጋ​ብ​ተ​ና​ልና ከእኛ ከሞት የሚ​ያ​መ​ልጥ እስ​ከ​ማ​ይ​ኖር ድረስ ፈጽ​መህ አት​ቈ​ጣን። 15አቤቱ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ሆይ፥ አንተ ጻድቅ ነህ፤ ዛሬም እንደ ሆነው እኛ አም​ል​ጠን ቀር​ተ​ናል፤ እነሆ በፊ​ትህ በበ​ደ​ላ​ችን አለን፤ ስለ​ዚህ በፊ​ትህ ሊቆም የሚ​ችል የለም።”

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ