የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ዕዝራ 8

8
1በን​ጉሡ በአ​ር​ተ​ሰ​ስታ#ዕብ. “አር​ጤ​ክ​ስስ” ይላል። መን​ግ​ሥት ከእኔ ጋር ከባ​ቢ​ሎን የወጡ የአ​ባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆች እነ​ዚህ ናቸው፤ ትው​ል​ዳ​ቸ​ውም ይህ ነው፤ 2ከፊ​ን​ሐስ ልጆች ጌር​ሶም፥ ከኢ​ታ​ምር ልጆች ዳን​ኤል፥ ከዳ​ዊት ልጆች ሐጡስ፥ 3ከሴ​ኬ​ንያ ልጆች፥ ከፋ​ሮስ ልጆች ዘካ​ር​ያስ፥ ከእ​ር​ሱም ጋር የተ​ቈ​ጠሩ መቶ አምሳ ወን​ዶች ናቸው። 4ከፋ​ሐት ሞዓብ ልጆች የዘ​ር​ህያ ልጅ ኤሊ​ሆ​ዔ​ናይ፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ሁለት መቶ ወን​ዶች። 5ከዘ​ቱ​ኤስ ልጆች የአ​ዚ​ኤል ልጅ ሴኬ​ንያ፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ሦስት መቶ ወን​ዶች። 6ከዓ​ዴን ልጆች የዮ​ና​ታን ልጅ ዔቤድ፥ ከእ​ር​ሱም ጋራ አምሳ ወን​ዶች። 7ከኤ​ሌም ልጆች የጎ​ቶ​ልያ ልጅ የሻያ፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ሰባ ወን​ዶች። 8ከሰ​ፋ​ጥ​ያስ ልጆች የሚ​ካ​ኤል ልጅ ዘብ​ድያ፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ሰማ​ንያ ወን​ዶች። 9ከኢ​ዮ​አብ ልጆች የያ​ሔ​ኤል ልጅ አብ​ድያ፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ሁለት መቶ ዐሥራ ስም​ንት ወን​ዶች። 10ከበ​ዐኛ ልጆች የዮ​ሴ​ፍያ ልጅ ሰሎ​ሚት፥ ከእ​ር​ሱም ጋር መቶ ስድሳ ወን​ዶች። 11ከቤ​ባይ ልጆች የቤ​ባይ ልጅ ዘካ​ር​ያስ፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ሃያ ስም​ንት ወን​ዶች። 12ከዓ​ዝ​ጋድ ልጆች የአ​ቃ​ጦን ልጅ፤ ዮሓ​ናን፥ ከእ​ር​ሱም ጋር መቶ ዐሥር ወን​ዶች። 13ከኋ​ለ​ኞቹ ከአ​ዶ​ኒ​ቃም ልጆች ስማ​ቸው ይህ ነው፤ ኤሊ​ፋ​ልጥ፥ ይኢ​ኤል፥ ሰማ​አያ፥ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ስድሳ ወን​ዶች። 14ከባ​ጎዊ ልጆች ውታ​ይና ዘቡድ፥ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ሰባ ወን​ዶች።
15ወደ አኅ​ዋም ወደ​ሚ​ፈ​ስስ ወንዝ ሰበ​ሰ​ብ​ኋ​ቸው፤ በዚ​ያም ሦስት ቀን ሰፈ​ርን፤ ሕዝ​ቡ​ንና ካህ​ና​ቱ​ንም ስቈ​ጥ​ራ​ቸው በዚያ ከሌዊ ልጆች ማን​ንም አላ​ገ​ኘ​ሁም። 16ወደ አለ​ቆ​ቹም ወደ አል​ዓ​ዛር፥ ወደ አር​ኤል፥ ወደ ሰማ​አያ፥ ወደ ሀሎ​ናም፥ ወደ ያሪብ፥ ወደ ሄል​ና​ታን፥ ወደ ናታን፥ ወደ ዘካ​ር​ያስ፥ ወደ ሜሱ​ላም፥ ደግ​ሞም ወደ ዐዋ​ቂ​ዎቹ ወደ ዮያ​ሪ​ብና ወደ ሄል​ና​ታን ላክሁ። 17በካ​ሲ​ፍያ ስፍራ ወደ ነበ​ረው ወደ አለ​ቃው ወደ አዶ ላክ​ኋ​ቸው፤ ለአ​ም​ላ​ካ​ችን ቤትም አገ​ል​ጋ​ዮ​ችን ያመ​ጡ​ልን ዘንድ በካ​ሲ​ፍያ ስፍራ ለሚ​ኖ​ሩት ለአ​ዶና ለወ​ን​ድ​ሞቹ ለና​ታ​ኒም የሚ​ነ​ግ​ሩ​አ​ቸ​ውን በአ​ፋ​ቸው አደ​ረ​ግሁ። 18በላ​ያ​ች​ንም መል​ካም በሆ​ነው በአ​ም​ላ​ካ​ችን እጅ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጅ ከሌዊ ልጅ ከሞ​ሐሊ ልጆች ወገን የነ​በ​ረ​ውን አስ​ተ​ዋይ ሰው ሰራ​ብ​ያን፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ዐሥራ ስም​ን​ቱን ልጆ​ቹ​ንና ወን​ድ​ሞ​ቹን አመ​ጡ​ልን። 19ደግ​ሞም አሴ​ብ​ያ​ስን፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ከሜ​ራሪ ልጆች ወገን የነ​በ​ረ​ውን ኢሳ​ይ​ያ​ስን፥ ሃያ​ውን ወን​ድ​ሞ​ቹ​ንና ልጆ​ቻ​ቸ​ውን። 20ሌዋ​ው​ያ​ን​ንም እን​ዲ​ያ​ገ​ለ​ግሉ ዳዊ​ትና አለ​ቆቹ ከሰ​ጡ​አ​ቸው ናታ​ኒም ውስጥ ሁለት መቶ ሃያ ናታ​ኒ​ምን አመጡ፤ እነ​ዚ​ህም ሁሉ በስም በስ​ማ​ቸው ተሰ​በ​ሰቡ።
21በአ​ም​ላ​ካ​ችን ፊት ራሳ​ች​ንን እና​ዋ​ርድ ዘንድ፥ ከእ​ር​ሱም የቀ​ና​ውን መን​ገድ ለእ​ኛና ለል​ጆ​ቻ​ችን፥ ለን​ብ​ረ​ታ​ች​ንም ሁሉ እን​ለ​ምን ዘንድ በዚያ በአ​ኅዋ ወንዝ አጠ​ገብ ጾምን አወ​ጅሁ። 22ንጉ​ሡ​ንም፥ “የአ​ም​ላ​ካ​ችን እጅ በሚ​ሹት ሁሉ ላይ ለመ​ል​ካም ነው፤ ኀይ​ሉና ቍጣው ግን እር​ሱን በሚ​ተዉ ሁሉ ላይ ነው” ብለን ተና​ግ​ረን ነበ​ርና፤ በመ​ን​ገድ ካለው ጠላት ያድ​ኑን ዘንድ ጭፍ​ራና ፈረ​ሰ​ኞች ከን​ጉሡ እለ​ምን ዘንድ አፍሬ ነበ​ርና። 23ስለ​ዚ​ህም ነገር ጾምን፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለመ​ንን፤ እር​ሱ​ም​ሰ​ማን።
24ከካ​ህ​ና​ቱም አለ​ቆች ዐሥራ ሁለት ሰዎ​ችን፥ ሰራ​ብ​ያ​ንና ሐሳ​ብ​ያን፥ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ዐሥር ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ውን ለየሁ፤ 25ንጉ​ሡና አማ​ካ​ሪ​ዎቹ፥ አለ​ቆ​ቹም፥ በዚ​ያም የተ​ገ​ኙት እስ​ራ​ኤል ሁሉ ያቀ​ረ​ቡ​ትን፥ ለአ​ም​ላ​ካ​ችን ቤት የቀ​ረ​በ​ውን ብሩ​ንና ወር​ቁን፥ ዕቃ​ው​ንም መዝኜ ሰጠ​ኋ​ቸው። 26ስድ​ስት መቶ አምሳ መክ​ሊት ብር፥ አንድ መቶም መክ​ሊት የብር ዕቃ​ዎች፥ አንድ መቶም መክ​ሊት ወርቅ፥ 27ሃያም ባለ ሺህ ዳሪክ የወ​ርቅ ጽዋ​ዎች፥ ሁለ​ትም እንደ ወርቅ የከ​በሩ ከጥ​ሩና ከሚ​ያ​ን​ጸ​በ​ርቅ ናስ የተ​ሠሩ ዕቃ​ዎ​ችን መዝኜ በእ​ጃ​ቸው ሰጠሁ። 28እኔም “እና​ንተ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተቀ​ድ​ሳ​ች​ኋል፤ ዕቃ​ዎ​ቹም ቅዱ​ሳን ናቸው፤ ብሩና ወር​ቁም ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን አም​ላክ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፈ​ቃድ የቀ​ረበ ነው፤ 29በካ​ህ​ና​ትና በሌ​ዋ​ው​ያን አለ​ቆች፥ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆች ፊት በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ጓዳ​ዎች ውስጥ እስ​ክ​ት​መ​ዝኑ ድረስ ተግ​ታ​ችሁ ጠብቁ” አል​ኋ​ቸው። 30ካህ​ና​ቱና ሌዋ​ው​ያ​ኑም ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ አም​ላ​ካ​ችን ቤት ይወ​ስ​ዱት ዘንድ ብሩ​ንና ወር​ቁን፥ ዕቃ​ዎ​ቹ​ንም በሚ​ዛን ተቀ​በሉ።
31በመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ውም ወር በዐ​ሥራ ሁለ​ተ​ኛው ቀን ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም እን​ሄድ ዘንድ ከአ​ኅዋ ወንዝ ተነ​ሣን፤ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ንም እጅ በላ​ያ​ችን ነበረ፤ በመ​ን​ገ​ድም ከጠ​ላ​ትና ከሚ​ሸ​ምቅ ሰው እጅ አዳ​ነን። 32ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ደረ​ስን፤ በዚ​ያም ሦስት ቀን ተቀ​መ​ጥን። 33በአ​ራ​ተ​ኛ​ውም ቀን ብሩና ወርቁ፥ ዕቃ​ዎ​ቹም በአ​ም​ላ​ካ​ችን ቤት በካ​ህኑ በኦ​ርያ ልጅ በሜ​ሪ​ሞት እጅ ተመ​ዘኑ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር የፊ​ን​ሐስ ልጅ አል​ዓ​ዛር ነበረ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ሌዋ​ው​ያን የኢ​ያሱ ልጅ ኢዮ​ዛ​ብ​ድና የቤ​ንዊ ልጅ ናሕ​ድያ ነበሩ። 34ሁሉም በቍ​ጥ​ርና በሚ​ዛን ተመ​ዘነ፤ ሚዛ​ኑም ሁሉ በዚያ ጊዜ ተጻፈ።
35ከም​ር​ኮም የወ​ጡት የም​ር​ኮ​ኞች ልጆች ለእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ስለ እስ​ራ​ኤል ሁሉ ዐሥራ ሁለት ወይ​ፈ​ኖች፥ ዘጠና ስድ​ስ​ትም አውራ በጎች፥ ሰባ ሰባ​ትም ጠቦ​ቶች፥ ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ዐሥራ ሁለት አውራ ፍየ​ሎ​ችን አቀ​ረቡ። ይህ ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ነበረ። 36የን​ጉ​ሡ​ንም ትእ​ዛዝ በወ​ንዙ ማዶ ላሉት ለን​ጉሡ ሹሞ​ችና ገዢ​ዎች ሰጡ፤ እነ​ር​ሱም ሕዝ​ቡ​ንና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት አከ​በሩ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ