የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ዕዝራ 7

7
የዕ​ዝራ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም መው​ጣት
1ከዚ​ህም ነገር በኋላ በፋ​ርስ ንጉሥ በአ​ር​ተ​ሰ​ስታ#ዕብ. “በአ​ር​ጤ​ክ​ስስ” ይላል። መን​ግ​ሥት ዕዝራ የሠ​ራያ ልጅ፥ የዓ​ዛ​ር​ያስ ልጅ፥ የኬ​ል​ቅ​ያስ ልጅ፥ 2የሰ​ሎም ልጅ፥ የሳ​ዶቅ ልጅ፥ የአ​ኪ​ጦብ ልጅ፥ 3የአ​ማ​ርያ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ሳማ​ርያ” ይላል። ልጅ፥ የዓ​ዛ​ር​ያስ ልጅ፥ የመ​ራ​ዮት ልጅ፥ 4የዘ​ራ​እያ ልጅ፥ የኡዚ ልጅ፥ የቡቂ ልጅ፥ 5የአ​ቢሱ ልጅ፥ የፊ​ን​ሐስ ልጅ፥ የአ​ል​ዓ​ዛር ልጅ፥ የመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ካህን የአ​ሮን ልጅ፥ 6ይህም ዕዝራ ከባ​ቢ​ሎን ወጣ፤ እር​ሱም የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሙሴ የሰ​ጠ​ውን ሕግ ዐዋቂ ነበረ፤ የአ​ም​ላ​ኩም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ በእ​ርሱ ላይ ነበ​ረ​ችና ንጉሡ ያሻ​ውን ሁሉ ሰጠው። 7ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ከካ​ህ​ና​ቱም፥ ከሌ​ዋ​ው​ያ​ኑም፥ ከመ​ዘ​ም​ራ​ኑም፥ ከበ​ረ​ኞ​ቹም፥ ከና​ታ​ኒ​ምም በን​ጉሡ በአ​ር​ተ​ሰ​ስታ በሰ​ባ​ተ​ኛው ዓመት ዐያ​ሌ​ዎች ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወጡ። 8በን​ጉ​ሡም በሰ​ባ​ተ​ኛው ዓመት በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ወር ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ደረሱ። 9በመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ውም ወር በአ​ን​ደ​ኛው ቀን ከባ​ቢ​ሎን ሊወጡ ጀመሩ፤ መል​ካ​ሚ​ቱም የአ​ም​ላኩ እጅ በእ​ርሱ ላይ ነበ​ረ​ችና በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ወር በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ደረሱ። 10ዕዝ​ራም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሕግ ይፈ​ል​ግና ያደ​ርግ ዘንድ፥ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሥር​ዐ​ት​ንና ፍር​ድን ያስ​ተ​ምር ዘንድ ልቡን አዘ​ጋ​ጅቶ ነበር።
ከን​ጉሡ አር​ተ​ሰ​ስታ ለዕ​ዝራ የተ​ሰጠ ፈቃድ
11ንጉ​ሡም አር​ተ​ሰ​ስታ#ዕብ. “አር​ጤ​ክ​ስስ” ይላል። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ቃልና ለእ​ስ​ራ​ኤል የሆ​ነ​ውን ሥር​ዐት ይጽፍ ለነ​በ​ረው ለጸ​ሓ​ፊው ለካ​ህኑ ለዕ​ዝራ የሰ​ጠው የደ​ብ​ዳ​ቤው ቃል ይህ ነው፦ 12“ከን​ጉሠ ነገ​ሥት ከአ​ር​ተ​ሰ​ስታ ለሰ​ማይ አም​ላክ ሕግ ጸሓፊ ለካ​ህኑ ለዕ​ዝራ፥ ሰላም ይሁን፤ 13በመ​ን​ግ​ሥ​ቴም ውስጥ ካሉ ከእ​ስ​ራ​ኤል ሕዝብ ከካ​ህ​ና​ቱና ከሌ​ዋ​ው​ያኑ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ይሄድ ዘንድ የሚ​ወ​ድድ ሁሉ ከአ​ንተ ጋር እን​ዲ​ሄድ አዝ​ዣ​ለሁ። 14ንጉ​ሡና ሰባቱ አማ​ካ​ሪ​ዎቹ በእ​ጅህ እን​ዳ​ለ​ችው እንደ አም​ላ​ክህ ሕግ ይሁ​ዳ​ንና ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ትጐ​በኝ ዘንድ አዝ​ዘ​ዋል፤ 15ንጉ​ሡና አማ​ካ​ሪ​ዎ​ቹም መኖ​ሪ​ያው በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ለሆ​ነው ለእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ በፈ​ቃ​ዳ​ቸው ያቀ​ረ​ቡ​ትን ብርና ወርቅ፥ 16በባ​ቢ​ሎ​ንም አው​ራጃ ሁሉ የም​ታ​ገ​ኘ​ውን ብርና ወርቅ ሁሉ፥ ሕዝ​ቡና ካህ​ና​ቱም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላለው ለአ​ም​ላ​ካ​ቸው ቤት በፈ​ቃ​ዳ​ቸው የሚ​ያ​ቀ​ር​ቡ​ትን ትወ​ስድ ዘንድ አዝ​ዘ​ዋል፤ 17ስለ​ዚህ በዚህ መጽ​ሐፍ ያዘ​ዝ​ሁህ ትእ​ዛዝ ይህ ነው። በዚህ ገን​ዘብ ወይ​ፈ​ኖ​ች​ንና አውራ በጎ​ችን፥ ጠቦ​ቶ​ች​ንም፥ የእ​ህ​ላ​ቸ​ው​ንና የመ​ጠ​ጣ​ቸ​ውን ቍር​ባን ተግ​ተህ ግዛ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ባለው በአ​ም​ላ​ካ​ችሁ ቤት መሠ​ዊያ ላይ አቅ​ር​ባ​ቸው። 18ከቀ​ረ​ውም ብርና ወርቅ አን​ተና ወን​ድ​ሞ​ችህ ለማ​ድ​ረግ ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኛ​ች​ሁን ነገር እንደ አም​ላ​ካ​ችሁ ፈቃድ አድ​ርጉ። 19ስለ አም​ላ​ክ​ህም ቤት አገ​ል​ግ​ሎት የተ​ሰ​ጠ​ህን ዕቃ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አም​ላክ ፊት አሳ​ል​ፈህ ስጥ። 20ከዚ​ህም በላይ ለማ​ው​ጣት የሚ​ያ​ስ​ፈ​ል​ግ​ህን ለአ​ም​ላ​ክህ ቤት የሚ​ያ​ሻ​ውን ነገር ከን​ጉሡ ቤተ መዛ​ግ​ብት ስጥ። 21እኔም ንጉሡ አር​ተ​ሰ​ስታ በወ​ንዝ ማዶ ላሉት ግምጃ ቤቶች ሁሉ ይህን ትእ​ዛዝ ሰጥ​ቻ​ለሁ፦ የሰ​ማይ አም​ላክ ሕግ ጸሓፊ ካህኑ ዕዝራ ከእ​ና​ንተ የሚ​ፈ​ል​ገ​ውን ሁሉ አዘ​ጋ​ጁ​ለት፤ 22እስከ መቶ መክ​ሊት ብርም ቢሆን፥ እስከ መቶም የቆ​ሮስ መስ​ፈ​ሪያ ስንዴ፥ እስከ መቶም የባ​ዶስ መስ​ፈ​ሪያ የወ​ይን ጠጅ፥ እስከ መቶም የባ​ዶስ መስ​ፈ​ሪያ ዘይት ቢሆን፥ ጨውም ያለ ልክ ቢሆን፤ 23በን​ጉሡ መን​ግ​ሥ​ትና በል​ጆቹ ላይ ቍጣ እን​ዳ​ይ​ሆን፥ የሰ​ማይ አም​ላክ ያዘ​ዘው ሁሉ ይደ​ረግ፤ ለሰ​ማይ አም​ላክ ቤት የታ​ዘ​ዘ​ው​ንም እን​ዳ​ታ​ቋ​ርጡ ተጠ​ን​ቀቁ። 24ደግ​ሞም በካ​ህ​ና​ቱና በሌ​ዋ​ው​ያኑ፥ በመ​ዘ​ም​ራ​ኑም፥ በበ​ረ​ኞ​ቹም፥ በና​ታ​ኒ​ምም በዚ​ህም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በሚ​ሠሩ አገ​ል​ጋ​ዮች ላይ ግብ​ርና ቀረጥ እን​ዳ​ይ​ጣል፥ የም​ት​ገ​ዙ​አ​ቸ​ውም አገ​ዛዝ እን​ዳ​ይ​ኖር ብለን እና​ስ​ታ​ው​ቃ​ች​ኋ​ለን። 25አን​ተም ዕዝራ፥ በእ​ጅህ እን​ዳ​ለው እንደ አም​ላ​ክህ ጥበብ መጠን በወ​ንዝ ማዶ ባሉ ሕዝብ ሁሉ፥ የአ​ም​ላ​ክ​ህን ሕግ በሚ​ያ​ውቁ ሁሉ ላይ ይፈ​ርዱ ዘንድ ጻፎ​ች​ንና ፈራ​ጆ​ችን ሹም፤ የማ​ያ​ው​ቁ​ት​ንም አስ​ተ​ም​ሩ​አ​ቸው። 26የአ​ም​ላ​ክ​ህ​ንም ሕግ፥ የን​ጉ​ሡ​ንም ሕግ በማ​ያ​ደ​ርግ ሁሉ ላይ ሞት፥ ወይም ስደት፥ ወይም ገን​ዘብ መወ​ረስ፥ ወይም ግዞት በፍ​ጥ​ነት ይፈ​ረ​ድ​በት።”
27ያባ​ቶ​ቻ​ችን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ያለ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ያከ​ብር ዘንድ ይህን ነገር በን​ጉሡ ልብ ያኖረ፥ 28በን​ጉሡ ፊት በሚ​መ​ክ​ሩ​ትም፥ በኀ​ያ​ላ​ኑም፥ በን​ጉሡ አለ​ቆች ሁሉ ፊት በእኔ ላይ ምሕ​ረ​ቱን ላከ። እኔም በእኔ ላይ ባለ​ችው በአ​ም​ላኬ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ በረ​ታሁ፤ ከእ​ኔም ጋራ ይወጡ ዘንድ ከእ​ስ​ራ​ኤል አለ​ቆ​ቹን ሰበ​ሰ​ብሁ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ