የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፀ​አት 12

12
ፋሲካ
1እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በግ​ብፅ ሀገር ሙሴ​ንና አሮ​ንን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው፦ 2“ይህ ወር የወ​ሮች መጀ​መ​ሪያ ይሁ​ና​ችሁ፤ የዓ​መ​ቱም መጀ​መ​ሪያ ወር ይሁ​ና​ችሁ። 3ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ማኅ​በር ሁሉ ተና​ገሩ፤ በሉ​አ​ቸ​ውም፦ በዚህ ወር በዐ​ሥ​ረ​ኛው ቀን ሰው ሁሉ ለአ​ባቱ ቤተ ሰቦች ቤቶች አንድ አንድ ጠቦት፥ እያ​ን​ዳ​ንዱ ሰውም ለራሱ ቤተ ሰብእ አንድ ጠቦት ይው​ሰድ። 4በቤት ያሉት ሰዎች ጥቂት ቢሆኑ፥ አንድ በግም የማ​ይ​ጨ​ርሱ ቢሆኑ በጉን ሊጨ​ርሱ በሚ​በቁ በሰ​ዎች ቍጥር እያ​ን​ዳ​ንዱ በአ​ጠ​ገቡ የሚ​ኖ​ረ​ውን ጎረ​ቤ​ቱን ይው​ሰድ። 5ነውር የሌ​ለ​በት የአ​ንድ ዓመት ተባት ጠቦት ለእ​ና​ንተ ይሁን፤ ከበ​ጎች ወይም ከፍ​የ​ሎች ውሰዱ። 6በዚ​ህም ወር እስከ ዐሥራ አራ​ተኛ ቀን ድረስ ጠብ​ቁት፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ማኅ​በር ሁሉ ሲመሽ ይረ​ዱት። 7ከደ​ሙም ወስ​ደው በሚ​በ​ሉ​በት ቤት ሁለ​ቱን መቃ​ንና ጉበ​ኑን ይቅ​ቡት። 8በእ​ሳ​ትም የተ​ጠ​በ​ሰ​ውን ሥጋ​ውን በዚ​ያች ሌሊት ይብሉ፤ ቂጣ​ውን እን​ጀ​ራም ከመ​ራራ ቅጠል ጋር ይብ​ሉት። 9ጥሬ​ው​ንም፥ በው​ኃም የበ​ሰ​ለ​ውን አት​ብሉ፤ ነገር ግን በእ​ሳት የተ​ጠ​በ​ሰ​ውን ራሱን፥ እግ​ሩ​ንና ሆድ ዕቃ​ውን ብሉት። 10ከእ​ር​ሱም እስከ ጥዋት አን​ዳች አታ​ስ​ቀሩ፤ አጥ​ን​ቱ​ንም ከእ​ርሱ አት​ስ​በሩ፤ ከእ​ር​ሱም እስከ ጥዋት የተ​ረፈ ቢኖር በእ​ሳት አቃ​ጥ​ሉት። 11ወገ​ቦ​ቻ​ች​ሁን ታጥ​ቃ​ችሁ፥ ጫማ​ች​ሁን በእ​ግ​ራ​ችሁ ተጫ​ም​ታ​ችሁ፥ በት​ራ​ች​ሁ​ንም በእ​ጃ​ችሁ ይዛ​ችሁ እን​ዲህ ብሉት፦ እየ​ቸ​ኰ​ላ​ች​ሁም ትበ​ሉ​ታ​ላ​ችሁ፤ እርሱ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፋሲካ ነውና። 12እኔም በዚ​ያች ሌሊት በግ​ብፅ ሀገር አል​ፋ​ለሁ፤ በግ​ብ​ፅም ሀገር ከሰው እስከ እን​ስሳ ድረስ በኵ​ርን ሁሉ እገ​ድ​ላ​ለሁ፤ በግ​ብ​ፅም አማ​ል​ክት ሁሉ ላይ በቀ​ልን አደ​ር​ግ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ። 13ደሙም ባላ​ች​ሁ​ባ​ቸው ቤቶች ምል​ክት ይሆ​ን​ላ​ች​ኋል፤ ደሙ​ንም አያ​ለሁ፤ እና​ን​ተ​ንም እሰ​ው​ራ​ች​ኋ​ለሁ፤ እኔም የግ​ብ​ፅን ሀገር በመ​ታሁ ጊዜ የጥ​ፋት መቅ​ሠ​ፍት አይ​መ​ጣ​ባ​ች​ሁም። 14ይህም ቀን መታ​ሰ​ቢያ ይሁ​ና​ችሁ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዓል ታደ​ር​ጉ​ታ​ላ​ችሁ፤ ለልጅ ልጃ​ች​ሁም ሥር​ዐት ሆኖ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ታደ​ር​ጉ​ታ​ላ​ችሁ።
የቂጣ በዓል
15“ሰባት ቀን ቂጣ ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤ በመ​ጀ​መ​ሪ​ያም ቀን እር​ሾ​ውን ከቤ​ታ​ችሁ ታወ​ጣ​ላ​ችሁ፤ ከመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ውም ቀን አን​ሥቶ እስከ ሰባ​ተ​ኛው ቀን እርሾ ያለ​በ​ትን እን​ጀራ የሚ​በላ ነፍስ ከእ​ስ​ራ​ኤል ተለ​ይቶ ይጥፋ። 16የመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ዪቱ ቀን ቅድ​ስት ትባ​ላ​ላች፤ እን​ዲ​ሁም ሰባ​ተ​ኛዋ ቀን ቅድ​ስት ትሁ​ን​ላ​ችሁ፤ ለነ​ፍስ ከሚ​ሠ​ራው ሥራ ሁሉ በቀር ማና​ቸ​ው​ንም ሥራ ሁሉ አት​ሥሩ#ግእዙ “የእ​ርሻ ሥራ አት​ሥሩ” ይላል። 17በዚ​ህም ቀን ሠራ​ዊ​ታ​ች​ሁን ከግ​ብፅ ሀገር አወ​ጣ​ዋ​ለ​ሁና ይህን ትእ​ዛዝ ጠብ​ቁት፤ እን​ግ​ዲህ ይህን ቀን ለልጅ ልጃ​ችሁ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት አድ​ር​ጋ​ችሁ ትጠ​ብ​ቃ​ላ​ችሁ። 18ከመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ውም ወር በዐ​ሥራ አራ​ተ​ኛው ቀን ሠርክ ጀም​ራ​ችሁ እስ​ከ​ዚሁ ወር ሃያ አን​ደኛ ቀን ሠርክ ድረስ ቂጣ ትበ​ላ​ላ​ችሁ። 19ሰባት ቀን በቤ​ታ​ችሁ እርሾ አይ​ገኝ፤ እርሾ ያለ​በ​ት​ንም እን​ጀራ የሚ​በላ ሁሉ ያ ሰው ከመ​ጻ​ተ​ኛው ጀምሮ እስከ ሀገር ልጁ ድረስ፥ ከእ​ስ​ራ​ኤል ማኅ​በር ተለ​ይቶ ይጥፋ። 20እርሾ ያለ​በ​ትን ምንም አት​ብሉ፤ በቤ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ሁሉ ውስጥ ቂጣ ብሉ።”
የመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ፋሲካ
21ሙሴም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ጠርቶ አላ​ቸው፥ “ሂዱና በየ​ወ​ገ​ና​ችሁ ጠቦት ውሰዱ፤ ለፋ​ሲ​ካም እረ​ዱት። 22ከሂ​ሶጵ ቅጠ​ልም ጭብጥ ውሰዱ፤ በዕቃ ውስጥ ባለ​ውም ደም ንከ​ሩት፤ በዕ​ቃ​ውም ውስጥ ከአ​ለው ደም ሁለ​ቱን መቃ​ኖ​ችና ጉበ​ኑን እርጩ፤ ከእ​ና​ን​ተም አንድ ሰው እስ​ኪ​ነጋ ድረስ ከቤቱ ደጅ አይ​ውጣ። 23እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግብ​ፃ​ው​ያ​ንን ይመታ ዘንድ ያል​ፋ​ልና፤ ደሙ​ንም በጉ​በ​ኑና በሁ​ለቱ መቃ​ኖች ላይ በአየ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሩን ያል​ፋል፤ አጥ​ፊ​ውም ይመ​ታ​ችሁ ዘንድ ወደ ቤታ​ችሁ እን​ዲ​ገባ አይ​ተ​ወ​ውም። 24ለእ​ና​ንተ ለል​ጆ​ቻ​ች​ሁም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይሆ​ና​ችሁ ዘንድ ይህን ሕግ ጠብቁ። 25እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ተና​ገረ ወደ​ሚ​ሰ​ጣ​ችሁ ሀገር በገ​ባ​ችሁ ጊዜ ይህን አም​ልኮ ጠብ​ቁት። 26ልጆ​ቻ​ችሁ፦ ‘ይህ ሥር​ዐት ለእ​ና​ንተ ምን​ድር ነው?’ ባሉ​አ​ችሁ ጊዜ እና​ንተ፦ 27‘ይህ በግ​ብፅ ሀገር የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ቤቶች ሰውሮ ግብ​ፃ​ው​ያ​ንን በመታ ጊዜ፥ ቤቶ​ቻ​ች​ንን የአ​ዳነ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የፋ​ሲ​ካው መሥ​ዋ​ዕት ነው’ ትሉ​አ​ቸ​ዋ​ላ​ችሁ።” ሕዝ​ቡም ተጐ​ነ​በሱ፤ ሰገ​ዱም። 28የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሄዱ፤ እን​ዲ​ህም አደ​ረጉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴ​ንና አሮ​ንን እንደ አዘ​ዛ​ቸው እን​ዲሁ አደ​ረጉ።
10፥ የግ​ብ​ፃ​ው​ያን የበ​ኵር ልጆች ሞት
29እን​ዲ​ህም ሆነ፤ እኩለ ሌሊት በሆነ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዙ​ፋን ከተ​ቀ​መ​ጠው ከፈ​ር​ዖን በኵር ጀምሮ እስከ ውኃ ቀጅዋ ምር​ኮኛ በኵር ድረስ፥ በግ​ብፅ ምድር በኵ​ሩን ሁሉ፥ የእ​ን​ስ​ሳ​ው​ንም በኵር ሁሉ መታ። 30ፈር​ዖ​ንም፥ ሹሞ​ቹም ሁሉ፥ ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም ሁሉ በሌ​ሊት ተነሡ፤ የሞተ የሌ​ለ​በት ቤት አል​ነ​በ​ረ​ምና በግ​ብፅ ምድር ሁሉ ታላቅ ልቅሶ ሆነ። 31ፈር​ዖ​ንም ሙሴ​ንና አሮ​ንን በሌ​ሊት ጠርቶ አላ​ቸው፥ “እና​ንተ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ተነሡ፤ ከሕ​ዝቤ መካ​ከል ውጡ፤ ሂዱም፤ እን​ዳ​ላ​ች​ሁም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አም​ል​ኩት፤ 32በጎ​ቻ​ች​ሁ​ንም፥ ላሞ​ቻ​ች​ሁ​ንም ውሰዱ፤ ሂዱም፤ እኔ​ንም ደግሞ ባር​ኩኝ።”
33ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም ፈጥ​ነው ከም​ድሩ ይወጡ ዘንድ ሕዝ​ቡን ያስ​ቸ​ኩ​ሉ​አ​ቸው ነበር፥ “ሁላ​ች​ንም እን​ሞ​ታ​ለን” ብለ​ዋ​ልና። 34ሕዝ​ቡም ሊጡን ሳይ​ቦካ ተሸ​ከሙ፤ ቡሃ​ቃ​ው​ንም በል​ብ​ሳ​ቸው ጠቅ​ል​ለው በት​ከ​ሻ​ቸው ተሸ​ከ​ሙት። 35የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሙሴ እን​ዳ​ዘዘ አደ​ረጉ። ከግ​ብ​ፃ​ው​ያ​ንም የብ​ር​ንና የወ​ር​ቅን ዕቃ፥ ልብ​ስ​ንም ተዋሱ። 36እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለሕ​ዝቡ በግ​ብ​ፃ​ው​ያን ፊት ሞገ​ስን ሰጠ፤ እነ​ር​ሱም አዋ​ሱ​አ​ቸው። እነ​ር​ሱም ግብ​ፃ​ው​ያ​ንን በዘ​በ​ዙ​አ​ቸው።
እስ​ራ​ኤ​ላ​ው​ያን ከግ​ብፅ እንደ ወጡ
37የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ከራ​ምሴ ተነ​ሥ​ተው ወደ ሱኮት ሄዱ፤ ከጓዝ ጋር ካሉት ሌላ ስድ​ስት መቶ ሺህ ሰው የሚ​ያ​ህል እግ​ረኛ ነበረ። 38ደግ​ሞም ሌላ ብዙ ድብ​ልቅ ሕዝብ፥ መን​ጎ​ችና ላሞ​ችም እጅግ ብዙም ከብ​ቶች ከእ​ነ​ርሱ ጋር ወጡ። 39ከግ​ብ​ፅም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ያወ​ጡ​ትን ሊጥ ቂጣ እን​ጎቻ አድ​ር​ገው ጋገ​ሩት። አል​ቦ​ካም ነበ​ርና፤ ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም ስለ አስ​ወ​ጡ​አ​ቸው ይቈዩ ዘንድ አል​ተ​ቻ​ላ​ቸ​ው​ምና፤ ለመ​ን​ገ​ድም ስንቅ አላ​ሰ​ና​ዱም ነበ​ርና። 40የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በግ​ብፅ ምድ​ርና በከ​ነ​ዓን ምድር እነ​ር​ሱና አባ​ቶ​ቻ​ቸው የተ​ቀ​መ​ጡት ዘመን አራት መቶ ሠላሳ ዓመት ነው። 41እን​ዲ​ህም ሆነ፤ አራት መቶ ሠላሳ ዓመት ከተ​ፈ​ጸመ በኋላ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሠራ​ዊት ሁሉ በሌ​ሊት ከግ​ብፅ ምድር ወጣ። 42ይህች ሌሊት ከግ​ብፅ ምድር ስላ​ወ​ጣ​ቸው ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ጠ​በ​ቀች ናት፤ ይህች ሌሊት በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ ዘንድ እስከ ልጅ ልጃ​ቸው ድረስ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ጠ​በ​ቀች ናት።
የፋ​ሲካ ሕግ
43እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴ​ንና አሮ​ንን አላ​ቸው፥ “ይህ የፋ​ሲካ ሕግ ነው፤ ከእ​ርሱ ባዕድ ሰው አይ​ብላ። 44አገ​ል​ጋይ ወይም በብር የተ​ገዛ ቢኖር ከተ​ገ​ረዘ በኋላ ያን ጊዜ ከእ​ርሱ ይብላ። 45ጥገ​ኛና ሞያ​ተኛ ግን ከእ​ርሱ አይ​ብሉ። 46በአ​ንድ ቤትም ይበላ፤ ከሥ​ጋ​ውም አን​ዳች ከቤት ወደ ሜዳ አታ​ውጡ፤ አጥ​ን​ቱ​ንም አት​ስ​በሩ። 47የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ማኅ​በር ሁሉ ያድ​ር​ጉት። 48የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፋሲካ ያደ​ርግ ዘንድ ወደ እና​ንተ የመጣ መጻ​ተኛ ቢኖር ወን​ዱን ሁሉ ትገ​ር​ዛ​ለህ፤ ያን ጊዜም ፋሲካ ያደ​ርግ ዘንድ ይገ​ባል፤ እንደ ሀገር ልጅም ይሆ​ን​ላ​ች​ኋል፤ ያል​ተ​ገ​ረዘ ሁሉ ግን ከእ​ርሱ አይ​ብላ። 49ለሀ​ገር ልጅ፥ በእ​ና​ንተ መካ​ከ​ልም ለሚ​ቀ​መጡ መጻ​ተ​ኞች አንድ ሥር​ዐት ይሆ​ናል።” 50የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሁሉ እን​ዲህ አደ​ረጉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴ​ንና አሮ​ንን እንደ አዘዘ እን​ዲሁ አደ​ረጉ። 51በዚ​ያም ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ከሠ​ራ​ዊ​ታ​ቸው ጋር ከግ​ብፅ ምድር አወ​ጣ​ቸው።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ