ኦሪት ዘፀአት 11
11
ስለ መጨረሻው መቅሠፍት ማስጠንቀቂያ
1እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “በፈርዖንና በግብፅ ላይ ገና አንዲት መቅሠፍት አመጣለሁ፤ ከዚያም በኋላ ከዚያ ይለቅቃችኋል፤ ሲለቅቃችሁም ከመነሻ ገንዘብ ጋር ይሰድዳችኋል። 2ወንዱ ከወዳጁ፥ ሴቲቱም ከወዳጅዋ የብርና የወርቅ ዕቃ፥ ልብስም ይዋሱ ዘንድ በሕዝቡ ጆሮ በስውር ተናገር።” 3እግዚአብሔርም በግብፃውያን ፊት ለሕዝቡ ሞገስን ሰጠ፤ አዋሱአቸውም፤ ይህ ሙሴም በግብፃውያንና በፈርዖን፥ በሹሞቹም ፊት እጅግ የከበረ ሰው ነበረ።
4ሙሴም አለ፥ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በእኩለ ሌሊት እኔ በግብፅ መካከል እገባለሁ፤ 5በግብፅም ሀገር ያለ በኵር ሁሉ፥ በዙፋኑ ከሚቀመጠው ከፈርዖን በኵር ጀምሮ በወፍጮ እግር እስካለችው እስከ አገልጋዪቱ በኵር ድረስ፥ የከብቱም በኵር ሁሉ ይሞታል። 6በግብፅም ሀገር ሁሉ አስቀድሞ እንደ እርሱ ያልሆነ፥ ኋላም ደግሞ እንደ እርሱ የማይሆን ታላቅ ጩኸት ይሆናል። 7እግዚአብሔር ግን በግብፃውያንና በእስራኤል መካከል ታላቅ ልዩነትን እንደሚያደርግ እንድታውቁ በእስራኤል ልጆች መካከል ከሰው ጀምሮ እስከ እንስሳ ድረስ ውሻ ምላሱን አያንቀሳቅስባቸውም። 8እነዚህ አገልጋዮችህ ሁሉ፦ አንተ ውጣ፤ የሚከተሉህም ሕዝብ ሁሉ ከዚያች ምድር ይውጡ እያሉ ወደ እኔ ይወርዳሉ፤ ለእኔም ይሰግዳሉ፤ ከዚያም በኋላ እወጣለሁ።” ሙሴም በጽኑ ቍጣ ከፈርዖን ዘንድ ወጣ።
9እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “ተአምራቴና ድንቄ በግብፅ ሀገር ብዙ እንዲሆን ፈርዖን አይሰማችሁም።” 10ሙሴና አሮንም እነዚህን ተአምራቶችና ድንቆች ሁሉ በፈርዖን ፊት አደረጉ፤ እግዚአብሔርም የፈርዖንን ልብ አጸና፤ የእስራኤልንም ልጆች ከግብፅ ምድር ለመልቀቅ እንቢ አለ።
Currently Selected:
ኦሪት ዘፀአት 11: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ