መጽ​ሐፈ ባሮክ 3

3
1“አቤቱ! ነግ​ሠህ የም​ት​ኖር የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ሆይ! የተ​ራ​በች ነፍስ፥ ያዘ​ነ​ችም ነፍስ ወደ አንተ ጮኸች። 2አቤቱ! ሰም​ተህ ይቅር በላት፤ በፊ​ትህ በድ​ለ​ና​ልና። 3አንተ ለዘ​ለ​ዓ​ለሙ የም​ት​ኖር ነህና፥ እኛ ግን ለዘ​ለ​ዓ​ለሙ እን​ጠ​ፋ​ለ​ንና።
4በሁሉ ላይ የም​ት​ነ​ግሥ#“በሁሉ ላይ የም​ት​ነ​ግሥ” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ አቤቱ! የሙ​ታን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን፥ በፊ​ት​ህም የበ​ደሉ፥ የአ​ም​ላ​ካ​ቸ​ው​ንም ቃል ያል​ሰሙ የል​ጆ​ቻ​ቸ​ውን ጸሎት ስማ። 5ክፉ ነገ​ርም ተከ​ተ​ለን፤ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ን​ንም ኀጢ​አት አላ​ሰ​ብ​ንም፤ በዚ​ህም ወራት እጅ​ህ​ንና ስም​ህን ዐስብ። 6አንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችን ነህና አቤቱ! እና​መ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለን። 7ስለ​ዚ​ህም ስም​ህን እን​ጠራ ዘንድ፥ ባስ​ማ​ረ​ክ​ኸ​ንም ቦታ እና​መ​ሰ​ግ​ንህ ዘንድ መፈ​ራ​ት​ህን በል​ቡ​ና​ችን አሳ​ደ​ርህ። በፊ​ትህ የበ​ደሉ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ንን ክፋት ሁሉ ከል​ባ​ችን አር​ቀ​ና​ልና። 8አቤቱ አም​ላ​ካ​ችን! እነሆ ዛሬ፦ ከአ​ንተ እንደ ራቁ አባ​ቶ​ቻ​ችን ክፋት ሁሉ ለው​ር​ደት፥ ለር​ግ​ማ​ንና ለፍዳ በበ​ተ​ን​ኸን ምርኮ ውስጥ ነን።” 9እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ የሕ​ይ​ወ​ትን ትእ​ዛዝ ስማ፥ የጥ​በ​ብ​ንም ምክር አድ​ምጥ። 10እስ​ራ​ኤል ምን​ድን ነው? በጠ​ላ​ትስ ሀገር ለምን ይኖ​ራል? 11በባ​ዕድ ሀገ​ርስ ለምን ጠፋ? ከሬ​ሳ​ዎ​ችስ ጋር ለምን ረከሰ? ወደ መቃ​ብር ከወ​ረ​ዱት ጋርስ ለምን ተቈ​ጠረ? 12የሕ​ይ​ወ​ትን ምንጭ ተውህ? 13በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርስ መን​ገድ ብት​ሄድ ለዘ​ለ​ዓ​ለም በሰ​ላም በኖ​ርህ ነበር! 14ተማር፥ ጥበብ ከየት ነው? ኀይ​ልስ ከየት ነው? ምክ​ርና ዕው​ቀ​ትስ ከየት ናቸው? ለብዙ ዘመ​ናት መኖ​ርስ ከየት ነው? የዐ​ይ​ኖች ብር​ሃ​ንና ሰላም ከየት ናቸው? 15የጥ​በብ ሀገ​ሯን ማን አገኘ? ወደ መዛ​ግ​ብ​ት​ዋስ ማን ገባ? 16የም​ድረ በዳ አው​ሬ​ዎ​ችን የገዙ የአ​ሕ​ዛብ አለ​ቆች ወዴት ናቸው? 17በሰ​ማይ አዕ​ዋ​ፍም የሚ​ጫ​ወቱ ሰዎች የሚ​ታ​መ​ኑ​በት ብርና ወር​ቅን የሚ​ሰ​በ​ስቡ፤ ለመ​ሰ​ብ​ሰ​ባ​ቸ​ውም ወሰን የሌ​ላ​ቸው የአ​ሕ​ዛብ አለ​ቆች ወዴት ናቸው? 18ብርን የሚ​ያ​ነ​ጥሩ ይተ​ጋ​ሉና፥ ለሥ​ራ​ቸ​ውም ምር​መራ የለ​ውም። 19አለቁ፤ ወደ መቃ​ብ​ርም ወረዱ፤ ስለ እነ​ር​ሱም ሌሎች ተተኩ።
20ታና​ና​ሾች ብር​ሃ​ንን አዩ፤ በም​ድ​ራ​ቸ​ውም ኖሩ፤ የጥ​በ​ብን መን​ገድ ግን አላ​ወ​ቁም። 21ፍለ​ጋ​ው​ንም አላ​ገ​ኙም፤ አል​ተ​ቀ​በ​ሉ​አ​ትም፤ ልጆ​ቻ​ቸ​ውም ከመ​ን​ገ​ዳ​ቸው ራቁ። 22የከ​ነ​ዓን ሰዎች አል​ሰ​ሙም፤ የቴ​ም​ናም ሰዎች አላ​ዩም። 23በም​ድር ጥበ​ብን የሚ​ፈ​ል​ጓት የአ​ጋር ልጆ​ችም የሚ​ጫ​ወ​ቱ​ባት፥ ዕው​ቀ​ት​ንም የሚ​ፈ​ል​ጓት፥ የመ​ር​ያ​ንና የቴ​ምና ነጋ​ዴ​ዎ​ችም የጥ​በ​ብን ጐዳና አላ​ወ​ቁም፤ ፍለ​ጋ​ዋ​ንም አላ​ስ​ተ​ዋ​ሉም። 24እስ​ራ​ኤል ሆይ! የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት እን​ዴት ታላቅ ነው! ቦታ​ውም እን​ዴት ሰፊ ነው! ፍጻሜ የለ​ውም፤ መለ​ኪ​ያም የለ​ውም። 25ታላቅ ነው፤ ፍጻ​ሜም የለ​ውም፤ ላይ​ኛ​ውም መለ​ኪያ የለ​ውም። 26ከጥ​ንት ጀምሮ ቁመ​ታ​ቸው ረዥም የሆነ፥ ጦር​ነ​ት​ንም የሚ​ያ​ውቁ ረዐ​ይት የሚ​ባሉ በዚያ ነበሩ። 27እነ​ዚ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አል​መ​ረ​ጣ​ቸ​ውም፤ የዕ​ው​ቀት መን​ገ​ድ​ንም አል​ሰ​ጣ​ቸ​ውም። 28ጥበብ አል​ነ​በ​ራ​ቸ​ው​ምና ጠፉ፤ በድ​ፍ​ረ​ታ​ቸ​ውም ጠፉ። 29ወደ ሰማይ የወ​ጣና የያ​ዛት፤ ከደ​መ​ና​ትም ያወ​ረ​ዳት ማነው? 30ባሕ​ሩን ተሻ​ግሮ ያገ​ኛት፥ በቀይ ወር​ቅስ ያመ​ጣት ማነው? 31መን​ገ​ድ​ዋን የሚ​ያ​ውቅ፥ ፍለ​ጋ​ዋ​ንም የሚ​ያ​ስብ የለም። 32ሁሉን የሚ​ያ​ውቅ ያው​ቃ​ታል፤ በጥ​በ​ቡም አገ​ኛት። ምድ​ርን የፈ​ጠረ ለዘ​ለ​ዓ​ለም በእ​ን​ስ​ሳት ሞላት። 33ብር​ሃ​ኑን ይል​ካል፤ እር​ሱም ይሄ​ዳል፤ እንደ ገናም ይጠ​ራ​ዋል፤ በፍ​ር​ሃ​ትም ይታ​ዘ​ዘ​ዋል። 34ከዋ​ክ​ብ​ትም በየ​ጊ​ዜ​ያ​ቸው ያበ​ራሉ፤ ደስም ይላ​ቸ​ዋል። 35ይጠ​ራ​ቸ​ዋል፤ እነ​ር​ሱም፦ መጣን ይላሉ። ለፈ​ጠ​ራ​ቸ​ውም በደ​ስታ ያበ​ራሉ። 36እር​ሱን የሚ​መ​ስል ሌላ የለ​ምና አም​ላ​ካ​ችን ነው ይላሉ። 37የጥ​በ​ብን መን​ገድ ሁሉ እርሱ አገ​ኛት፤ ለባ​ለ​ሟሉ ለያ​ዕ​ቆብ፥ ለወ​ዳ​ጁም ለእ​ስ​ራ​ኤል ሰጠው። 38ከዚህ በኋላ በም​ድር ተገ​ለጠ፤ እንደ ሰውም ሆነ።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ