ከጻድቅ ጋር ጻድቅ ትሆናለህ፤ ከንጹሕ ሰውም ጋር ንጹሕ ትሆናለህ፤ ከተመረጠም ጋር የተመረጠ ትሆናለህ፤ ከጠማማ ጋርም ጠማማ ትሆናለህ። አንተ የተዋረደውን ሕዝብ ታድናለህና፤ የትዕቢተኞችን ዐይኖች ግን ታዋርዳለህ። አቤቱ! አንተ መብራቴ ነህና፤ እግዚአብሔርም ጨለማዬን ያበራልኛልና። በአንተ ብቻዬን እሮጣለሁና፤ በአምላኬም ቅጥሩን እዘልላለሁና። የኀያል አምላክ መንገድ ንጹሕ ነው፤ የእግዚአብሔር ቃል ጽኑዕ ነው፤ በእሳትም የጋለ ነው፤ በእርሱም ለሚታመኑት ጠባቂያቸው ነው። ከእግዚአብሔር በቀር ጽኑዕ ማን ነው? ከአምላካችንስ በቀር ፈጣሪ ማን ነው? በኀይል የሚያጸናኝ ኀያል እርሱ ነው፤ መንገዴንም ንጹሕ አድርጎ አዘጋጀ፤ እግሮቼን እንደ ዋልያ እግሮች አጸና፤ በኮረብቶችም አቆመኝ። ለእጆቼ ጦርነትን ያስተምራል፤ ለክንዴም የናስ ቀስት አዘዘ። የመድኀኒቴንም ጋሻ ሰጠኸኝ፤ መልስህም አበዛችኝ፤ በሜዳም አረማመዴን በበታቼ አሰፋህ፤ እግሮቼም አልተንሸራተቱም። ጠላቶቼን አሳድዳቸዋለሁ፤ አጠፋቸውማለሁ፤ እስካጠፋቸውም ድረስ አልመለስም። እቀጠቅጣቸዋለሁ፤ መቆምም አይችሉም፤ ከእግሬም በታች ይወድቃሉ። በጦርነትም ጊዜ በኀይል ታጸናኛለህ፤ በላዬ የቆሙትንም በበታቼ ታስገዛቸዋለህ። የጠላቶቼን ጀርባ ሰጠኸኝ፤ የሚጠሉኝንም አጠፋሃቸው። ጮኹ፤ የሚረዳቸውም አልነበረም፤ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ አልሰማቸውምም። በነፋስ ፊት እንዳለ እንደ ምድር ትቢያ ፈጨኋቸው፤ እንደ ጎዳናም ጭቃ ረገጥኋቸው፤ ደቀደቅኋቸውም። ከአሕዛብ ጠብ አድነኝ፤ የአሕዛብም ራስ አድርገህ ትሾመኛለህ፤ የማላውቀው ሕዝብ ተገዛልኝ። የባዕድ ልጆች ዋሹኝ፤ በጆሮ ሰምተው መለሱልኝ። የባዕድ ልጆች አረጁ፤ ከማንከሳቸውም የተነሣ ተሰናከሉ። እግዚአብሔር ሕያው ነው፤ ጠባቂዬም ቡሩክ ነው፤ የሕይወቴ ጠባቂ አምላኬ ከፍ ከፍ ይበል፤ በቀሌን የሚመልስልኝ አምላክ ጽኑዕ ነው። አሕዛብን በበታቼ ያስገዛልኛል፤ ከጠላቶቼ የሚያወጣኝ እርሱ ነው፤ በእኔም ላይ ከቆሙ ከፍ ከፍ ታደርገኛለህ፤ ከግፈኛም ሰው ታድነኛለህ። አቤቱ፥ ስለዚህ በአሕዛብ ዘንድ አመሰግንሃለሁ፥ ለስምህም እዘምራለሁ። የንጉሡን መድኀኒት ታላቅ ያደርጋል፤ ቸርነቱንም ለቀባው ለዳዊትና ለዘሩ፥ ለዘለዓለም ያደርጋል።”
መጽሐፈ ሳሙኤል ካልእ 22 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መጽሐፈ ሳሙኤል ካልእ 22:26-51
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos