መጽ​ሐፈ ነገ​ሥት ካልእ 6:15-23

መጽ​ሐፈ ነገ​ሥት ካልእ 6:15-23 አማ2000

የኤ​ል​ሳ​ዕም ሎሌ ማለዳ ነቃ፤ ተነ​ሥ​ቶም በወጣ ጊዜ፥ እነሆ፥ በከ​ተ​ማ​ዪቱ ዙሪያ ጭፍ​ሮች ከተ​ማ​ዋን ከብ​በ​ዋት አየ። ፈረ​ሶ​ችና ሰረ​ገ​ሎ​ችም ነበሩ። ሎሌ​ውም፥ “ጌታዬ ሆይ፥ ወዮ! ምን እና​ድ​ርግ?” አለው። እር​ሱም፥ “ከእኛ ጋር ያሉት ከእ​ነ​ርሱ ጋር ካሉት ይበ​ል​ጣ​ሉና አት​ፍራ” አለው። ኤል​ሳ​ዕም፥ “አቤቱ፥ ያይ ዘንድ ዐይ​ኖ​ቹን፥ እባ​ክህ፥ ግለጥ” ብሎ ጸለየ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የብ​ላ​ቴ​ና​ውን ዐይ​ኖች ገለጠ፤ እነ​ሆም፥ የእ​ሳት ፈረ​ሶ​ችና ሰረ​ገ​ሎች በኤ​ል​ሳዕ ዙሪያ ተራ​ራ​ውን ሞል​ተ​ውት አየ። ወደ እር​ሱም በወ​ረዱ ጊዜ ኤል​ሳዕ፥ “አቤቱ፥ እነ​ዚ​ህን ሰዎች አሳ​ው​ራ​ቸው” ብሎ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸለየ። ኤል​ሳ​ዕም እንደ ተና​ገ​ረው ቃል አሳ​ወ​ራ​ቸው። ኤል​ሳ​ዕም፥ “መን​ገዱ በዚህ አይ​ደ​ለም፥ ከተ​ማ​ዪ​ቱም ይህች አይ​ደ​ለ​ችም፤ የም​ት​ሹ​ትን ሰው አሳ​ያ​ችሁ ዘንድ ተከ​ተ​ሉኝ” አላ​ቸው፤ ወደ ሰማ​ር​ያም ወሰ​ዳ​ቸው። ወደ ሰማ​ር​ያም በገቡ ጊዜ ኤል​ሳዕ፥ “አቤቱ፥ ያዩ ዘንድ የእ​ነ​ዚ​ህን ሰዎች ዐይ​ኖች ግለጥ” አለ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዐይ​ኖ​ቻ​ቸ​ውን ገለጠ፤ እነ​ር​ሱም አዩ። እነ​ሆም፥ በሰ​ማ​ርያ መካ​ከል እን​ዳሉ ዐወቁ። የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ባያ​ቸው ጊዜ ኤል​ሳ​ዕን፥ “አባቴ ሆይ፥ ልግ​ደ​ላ​ቸ​ውን?” አለው። እር​ሱም፥ “በሰ​ይ​ፍ​ህና በቀ​ስ​ትህ የማ​ረ​ክ​ሃ​ቸ​ውን ግደል እንጂ በሰ​ይ​ፍ​ህና በቀ​ስ​ትህ የማ​ረ​ክ​ሃ​ቸው አይ​ደ​ሉ​ምና አት​ግ​ደ​ላ​ቸው። ይል​ቁ​ንስ እን​ጀ​ራና ውኃ በፊ​ታ​ቸው አቅ​ር​ብ​ላ​ቸው፤ በል​ተ​ውና ጠጥ​ተ​ውም ወደ ጌታ​ቸው ይመ​ለሱ” አለው። ብዙም መብል አዘ​ጋ​ጀ​ላ​ቸው፤ በበ​ሉና በጠጡ ጊዜም አሰ​ና​በ​ታ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም ወደ ጌታ​ቸው ሄዱ። ከዚ​ያም በኋላ የሶ​ር​ያ​ው​ያን አደጋ ጣዮች ዳግ​መኛ ወደ እስ​ራ​ኤል ሀገር አል​መ​ጡም።