የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ነገ​ሥት ካልእ 24

24
1በእ​ር​ሱም ዘመን የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ወጣ፤ ኢዮ​አ​ቄ​ምም ሦስት ዓመት ተገ​ዛ​ለት፤ ከዚ​ያም በኋላ ዘወር አለና ዐመ​ፀ​በት። 2እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንን አደጋ ጣዮች፥ የሶ​ር​ያ​ው​ያ​ን​ንም አደጋ ጣዮች፥ የሞ​ዓ​ባ​ው​ያ​ን​ንም አደጋ ጣዮች፥ የአ​ሞ​ን​ንም ልጆች አደጋ ጣዮች ሰደ​ደ​በት፤ በባ​ሪ​ያ​ዎቹ በነ​ቢ​ያት ቃል እንደ ተና​ገ​ረው እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ያጠ​ፉት ዘንድ በይ​ሁዳ ላይ ሰደ​ዳ​ቸው። 3ምና​ሴም ስላ​ደ​ረ​ገው ኀጢ​አት ሁሉ ከፊቱ ያር​ቀው ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ በይ​ሁዳ ላይ ሆነ፤ 4ጻድ​ቁ​ንም ስለ ገደለ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም በን​ጹሕ ደም ስለ ሞላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይራራ ዘንድ አል​ወ​ደ​ደም።
5የቀ​ረ​ውም የኢ​ዮ​አ​ቄም ነገር፥ የሠ​ራ​ውም ሥራ ሁሉ፥ እነሆ፥ በይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን? 6ኢዮ​አ​ቄ​ምም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፤ በኦ​ዛም የአ​ት​ክ​ልት ቦታ ተቀ​በረ#“በኦ​ዛም የአ​ት​ክ​ልት ቦታ ተቀ​በረ” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. እና በዕብ. የለም። ልጁም ዮአ​ኪን በእ​ርሱ ፋንታ ነገሠ። 7የባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ ለግ​ብፅ ንጉሥ የነ​በ​ረ​ውን ሁሉ ከግ​ብፅ ወንዝ ጀምሮ እስከ ኤፍ​ራ​ጥስ ወንዝ ድረስ ወስዶ ነበ​ርና የግ​ብፅ ንጉሥ ከዚያ ወዲህ ከሀ​ገሩ አል​ወ​ጣም።
የይ​ሁዳ ንጉሥ የዮ​አ​ኪን ዘመነ መን​ግ​ሥት
(2ዜ.መ. 36፥9-10)
8ዮአ​ኪ​ንም በነ​ገሠ ጊዜ ዐሥራ ስም​ንት ዓመት ሆኖት ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ሦስት ወር ነገሠ፤ እና​ቱም ኒስታ ትባል ነበር፤ እር​ስ​ዋም የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ሰው የኤ​ል​ና​ታን ልጅ ነበ​ረች። 9አባ​ቶ​ቹም እን​ዳ​ደ​ረጉ ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ አደ​ረገ።
10በዚ​ያም ወራት የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ የና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ሠራ​ዊት ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወጡ፤ ከተ​ማ​ዪ​ቱም ተከ​በ​በች። 11የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆ​ርም ወደ ከተ​ማ​ዪቱ መጣ። ሠራ​ዊ​ቱም ከበ​ቡ​አት። 12የይ​ሁ​ዳም ንጉሥ ዮአ​ኪን ከእ​ናቱ፥ ከብ​ላ​ቴ​ኖ​ቹም፥ ከአ​ለ​ቆ​ቹም፥ ከጃ​ን​ደ​ረ​ቦ​ቹም ጋር ወደ ባቢ​ሎን ንጉሥ ወጣ፤ የባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ በነ​ገሠ በስ​ም​ን​ተ​ኛው ዓመት ያዘው። 13የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤተ መዛ​ግ​ብት ሁሉ የን​ጉ​ሡ​ንም ቤተ መዛ​ግ​ብት ከዚያ አወጣ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ተና​ገ​ረው የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ሰሎ​ሞን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ደስ የሠ​ራ​ውን የወ​ር​ቁን ዕቃ ሁሉ ሰባ​በረ። 14ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም አጠ​ፋት፥ አለ​ቆ​ቹ​ንም ሁሉ፥ ጽኑ​ዓ​ኑ​ንና ኀያ​ላ​ኑን ሁሉ፥ ጠራ​ቢ​ዎ​ቹ​ንም ሁሉ፥ ብረት ሠራ​ተ​ኞ​ቹ​ንም ሁሉ ዐሥር ሺህ ምር​ኮ​ኞ​ችን ሁሉ አፈ​ለሰ፤ ከሀ​ገሩ ድሆች በቀር ማንም አል​ቀ​ረም። 15ዮአ​ኪ​ን​ንም ወደ ባቢ​ሎን አፈ​ለሰ፤ የን​ጉ​ሡ​ንም እናት፥ የን​ጉ​ሡ​ንም ሚስ​ቶች፥ ጃን​ደ​ረ​ቦ​ቹ​ንም፥ የሀ​ገ​ሩ​ንም ታላ​ላ​ቆች ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ ባቢ​ሎን ማረከ። 16የባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ ሰባት ሺህ ያህል፥ ብር​ቱ​ዎ​ች​ንና ሰልፍ የሚ​ች​ሉ​ትን ሁሉ፥ ኀያ​ላ​ኑን ሁሉ አንድ ሺህ የሚ​ሆኑ ጠራ​ቢ​ዎ​ች​ንና ብረት ሠራ​ተ​ኞ​ች​ንም ወደ ባቢ​ሎን ማረከ። 17የባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ የዮ​አ​ኪ​ንን አጎት#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ልጁን” ይላል። ማታ​ን​ያን በእ​ርሱ ፋንታ አነ​ገሠ፤ ስሙ​ንም ሴዴ​ቅ​ያስ ብሎ ለወ​ጠው።
የይ​ሁዳ ንጉሥ የሴ​ዴ​ቅ​ያስ ዘመነ መን​ግ​ሥት
(2ዜ.መ. 36፥11-12ኤር. 52፥1-3)
18ሴዴ​ቅ​ያ​ስም በነ​ገሠ ጊዜ ሃያ አንድ ዓመት ሆኖት ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ዐሥራ አንድ ዓመት ነገሠ፤ እና​ቱም አሚ​ጣል የተ​ባ​ለች የሎ​ብና ሰው የኤ​ር​ም​ያስ ልጅ ነበ​ረች። 19ኢዮ​አ​ቄ​ምም እን​ዳ​ደ​ረ​ገው ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ አደ​ረገ። 20ከፊቱ አው​ጥቶ እስ​ኪ​ጥ​ላ​ቸው ድረስ ይህ ነገር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምና በይ​ሁዳ ላይ ሆኖ​አ​ልና፤ ሴዴ​ቅ​ያ​ስም በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ላይ ዐመፀ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ