መጽ​ሐፈ ነገ​ሥት ካልእ 22

22
የኢ​ዮ​ስ​ያስ ዘመነ መን​ግ​ሥት
(2ዜ.መ. 34፥1-2)
1ኢዮ​ስ​ያ​ስም መን​ገሥ በጀ​መረ ጊዜ የስ​ም​ንት ዓመት ልጅ ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ሠላሳ አንድ ዓመት ነገሠ፤ እና​ቱም ከባ​ሱ​ሮት የሆነ የአ​ዳያ ልጅ ይዲያ ነበ​ረች። 2በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ቅን ነገ​ርን አደ​ረገ፤ በአ​ባ​ቱም በዳ​ዊት መን​ገድ ሁሉ ሄደ፤ ቀኝም ግራም አላ​ለም።
3በን​ጉ​ሡም በኢ​ዮ​ስ​ያስ በዐ​ሥራ ስም​ን​ተ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት በስ​ም​ን​ተ​ኛው ወር ንጉሡ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ጸሓፊ የሜ​ሱ​ላ​ምን ልጅ የኤ​ሴ​ል​ዩን ልጅ ሳፋ​ንን እን​ዲህ ሲል ላከው፦ 4“ወደ ታላቁ ካህን ወደ ኬል​ቅዩ ወጥ​ተህ ደጃ​ፉን የሚ​ጠ​ብቁ ከሕ​ዝቡ የሰ​በ​ሰ​ቡ​ትን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የገ​ባ​ውን ወርቅ ቍጠር። 5በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ላሉት ሠራ​ተ​ኞች አለ​ቆች ይስ​ጡት፤ እነ​ር​ሱም የተ​ና​ደ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ለሚ​ጠ​ግ​ኑት ሠራ​ተ​ኞች፥ 6ለአ​ና​ጢ​ዎ​ችና ለጠ​ራ​ቢ​ዎች፥ ለድ​ን​ጋ​ይም ወቃ​ሪ​ዎች፥ መቅ​ደ​ሱ​ንም ለመ​ጠ​ገን እን​ጨ​ት​ንና የተ​ወ​ቀ​ረ​ውን ድን​ጋይ ለሚ​ገዙ ይክ​ፈ​ሉት።” 7ነገር ግን እነ​ርሱ በእ​ም​ነት ይሠሩ ነበ​ርና የሰ​ጡ​አ​ቸ​ውን ገን​ዘብ አይ​ቈ​ጣ​ጠ​ሩ​አ​ቸ​ውም ነበር።
የሕጉ መጽ​ሐፍ መገ​ኘት
8ታላቁ ካህ​ንም ኬል​ቅ​ያስ ጸሓ​ፊ​ውን ሳፋ​ንን፥ “የሕ​ጉን መጽ​ሐፍ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አግ​ኝ​ቻ​ለሁ” አለው፤ ኬል​ቅ​ያ​ስም መጽ​ሐ​ፉን ለሳ​ፋን ሰጠው፥ እር​ሱም አነ​በ​በው። 9ጸሓ​ፊ​ውም ሳፋን ወደ ንጉሡ መጣ፤ ለን​ጉ​ሡም፥ “በመ​ቅ​ደሱ የተ​ገ​ኘ​ውን ገን​ዘብ አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ አፈ​ሰ​ሱት፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቤት ሥራ ለመ​ሥ​ራት ለተ​መ​ደ​ቡት ሰዎች ሰጡት” ብሎ ነገ​ረው። 10ጸሓ​ፊው ሳፋ​ንም ለን​ጉሡ፥ “ካህኑ ኬል​ቅ​ያስ የሕግ መጽ​ሐፍ ሰጥ​ቶ​ኛል” ብሎ ነገ​ረው። ሳፋ​ንም በን​ጉሡ ፊት አነ​በ​በው። 11ንጉ​ሡም የሕ​ጉን መጽ​ሐፍ ቃል በሰማ ጊዜ ልብ​ሱን ቀደደ። 12ንጉ​ሡም ካህ​ኑን ኬል​ቅ​ያ​ስን፥ የሳ​ፋ​ን​ንም ልጅ አኪ​ቃ​ምን፥ የሚ​ክ​ዩ​ንም ልጅ ዓክ​ቦ​ርን፥ ጸሓ​ፊ​ው​ንም ሳፋ​ንን፥ የን​ጉ​ሡ​ንም ብላ​ቴና ዓስ​ያን እን​ዲህ ብሎ አዘ​ዛ​ቸው፦ 13“አባ​ቶ​ቻ​ችን በእ​ር​ስዋ የተ​ጻ​ፈ​ውን ሁሉ ይሠሩ ዘንድ የዚ​ህ​ችን መጽ​ሐፍ ቃል ስላ​ል​ሰሙ በላ​ያ​ችን የነ​ደደ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ እጅግ ነውና ሄዳ​ችሁ ስለ እኔና ስለ ሕዝቡ ስለ ይሁ​ዳም ሁሉ ስለ​ዚ​ችም ስለ​ተ​ገ​ኘ​ችው መጽ​ሐፍ ቃል ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጠይቁ።
14እን​ዲ​ሁም ካህኑ ኬል​ቅ​ያ​ስና አኪ​ቃም ዓክ​ቦ​ርም ሳፋ​ንና ዓሳ​ያም ወደ ልብስ ጠባ​ቂው ወደ ሓስራ ልጅ ወደ ቴቁዋ ልጅ ወደ ሴሌም ሚስት#አን​ዳ​ንድ የግ​ሪክ ሰባ. ሊ. ዘርዕ “እናት” ይላል። ወደ ነቢ​ዪቱ ወደ ሕል​ዳና ሄዱ፤ እር​ስ​ዋም በዚያ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በሁ​ለ​ተ​ኛው ክፍል ተቀ​ምጣ ነበር፤ ለእ​ር​ስ​ዋም ነገ​ሩ​አት። 15እር​ስ​ዋም አለ​ቻ​ቸው፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ወደ እኔ ለላ​ካ​ችሁ ሰው እን​ዲህ ብላ​ችሁ ንገ​ሩት፦ 16እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ፥ የይ​ሁዳ ንጉሥ እን​ዳ​ነ​በ​በው እን​ደ​ዚህ መጽ​ሐፍ ቃል ሁሉ በዚህ ስፍ​ራና በሚ​ኖ​ሩ​በት ላይ ክፉ ነገር አመ​ጣ​ለሁ። 17በእ​ጃ​ችሁ ሥራ ሁሉ ታስ​ቈ​ጡኝ ዘንድ ትታ​ች​ሁ​ኛ​ልና፥ ለሌ​ሎች አማ​ል​ክ​ትም ዐጥ​ና​ች​ኋ​ልና ቍጣዬ በዚህ ስፍራ ላይ ይነ​ድ​ዳል፥ አይ​ጠ​ፋ​ምም። 18እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ለመ​ጠ​የቅ ለላ​ካ​ችሁ ለይ​ሁዳ ንጉሥ ግን እን​ዲህ በሉት፦ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ስለ ሰማ​ኸው ቃል፥ 19ልብ​ህን አላ​ደ​ነ​ደ​ን​ህ​ምና፥ እነ​ር​ሱም ለጥ​ፋ​ትና ለመ​ር​ገም እን​ዲ​ሆኑ በዚህ ስፍ​ራና በሚ​ኖ​ሩ​በት ላይ የተ​ና​ገ​ር​ሁ​ትን ሰም​ተህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ተዋ​ር​ደ​ሃ​ልና፥ ልብ​ስ​ህን ቀድ​ደ​ሃ​ልና፥ በፊ​ቴም አል​ቅ​ሰ​ሃ​ልና እኔ ደግሞ ሰም​ቼ​ሃ​ለሁ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። 20ነገሩ እን​ደ​ዚህ አይ​ደ​ለም፤ ወደ አባ​ቶ​ችህ እሰ​በ​ስ​ብ​ሃ​ለሁ፥ በሰ​ላ​ምም ወደ መቃ​ብ​ርህ ትሰ​በ​ሰ​ባ​ለህ፤ በዚ​ህም ስፍ​ራና በሚ​ኖ​ሩ​በት ላይ የማ​መ​ጣ​ውን ክፉ ነገር ዐይ​ኖ​ችህ አያ​ዩም።” ይህ​ንም ለን​ጉሡ ነገ​ሩት።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ

YouVersion የእርስዎን ተሞክሮ ግላዊ ለማድረግ ኩኪዎችን ይጠቀማል። የእኛን ድረ ገጽ በመጠቀም፣ በግለሰብነት መመሪያችን ላይ እንደተገለጸው የእኛን የኩኪዎች አጠቃቀም ተቀብለዋል