የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ነገ​ሥት ካልእ 12

12
የይ​ሁዳ ንጉሥ ኢዮ​አስ
1ኢዩ በነ​ገሠ በሰ​ባ​ተ​ኛው ዓመት ኢዮ​አስ ነገሠ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም አርባ ዓመት ነገሠ፤ እና​ቱም ሳቢያ የተ​ባ​ለች የቤ​ር​ሳ​ቤህ ሴት ነበ​ረች።#ምዕ. 11 ቍ. 21 በዕብ. እና በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. ምዕ. 12 ቍ. 1 ነው። 2ካህኑ ዮዳሄ ያስ​ተ​ም​ረው በነ​በረ ዘመን ሁሉ ኢዮ​አስ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቅን ነገር አደ​ረገ። 3ነገር ግን በኮ​ረ​ብ​ቶቹ ላይ ያሉ የጣ​ዖት መስ​ገ​ጃ​ዎ​ችን አላ​ስ​ወ​ገ​ደም፤ ሕዝ​ቡም ገና በኮ​ረ​ብ​ቶቹ ላይ ባሉት የጣ​ዖት መስ​ገ​ጃ​ዎች ይሠ​ዋና ያጥን ነበር።
4ኢዮ​አ​ስም ካህ​ና​ቱን፥ “ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የሚ​ገ​ባ​ውን የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውን ገን​ዘብ ሁሉ፥ ስለ ነፍ​ሱም ዋጋ የሚ​ያ​ቀ​ር​በ​ውን ገን​ዘብ፥ በል​ባ​ቸ​ውም ፈቃድ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የሚ​ያ​መ​ጡ​ትን ገን​ዘብ ሁሉና፥ 5እያ​ን​ዳ​ንዱ ሰው ከሚ​ያ​መ​ጣው ካህ​ናቱ ለራ​ሳ​ቸው ይው​ሰዱ፤ በመ​ቅ​ደ​ስም ውስጥ የተ​ና​ዱ​ትን ይጠ​ግ​ኑ​በት” አላ​ቸው። 6ነገር ግን እስከ ንጉሡ እስከ ኢዮ​አስ እስከ ሃያ ሦስ​ተ​ኛው ዓመት ድረስ ከመ​ቅ​ደሱ ውስጥ የተ​ና​ዱ​ትን ካህ​ናቱ አል​ጠ​ገ​ኑ​ትም ነበር። 7ኢዮ​አ​ስም ካህ​ኑን ዮዳ​ሄ​ንና ካህ​ና​ቱን ጠርቶ፥ “በመ​ቅ​ደሱ ውስጥ የተ​ና​ዱ​ትን ስፍ​ራ​ዎች ስለ ምን አል​ጠ​ገ​ና​ች​ሁም? ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲያ ገን​ዘቡ ለቤቱ መጠ​ገኛ ይሰጥ እንጂ ከሚ​ያ​መ​ጡት ሰዎች አት​ቀ​በሉ” አላ​ቸው። 8ካህ​ና​ቱም “ከሕ​ዝቡ ገን​ዘ​ቡን አን​ወ​ስ​ድም፤ በቤ​ቱም ውስጥ የተ​ና​ዱ​ትን አን​ጠ​ግ​ንም፥” ብለው ተስ​ማሙ።
9ካህኑ ዮዳሄ ግን አንድ ሣጥን ወስዶ መክ​ደ​ኛ​ውን ነደ​ለው፤ በመ​ሠ​ዊ​ያ​ውም አጠ​ገብ ሰው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በሚ​ገ​ባ​በት መግ​ቢያ በስ​ተ​ቀኝ አኖ​ረው፤ ደጁ​ንም የሚ​ጠ​ብቁ ካህ​ናት ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የሚ​መ​ጣ​ውን ገን​ዘብ ሁሉ በሚ​ዛን አስ​ገቡ።
10በሣ​ጥ​ኑም ውስጥ የተ​ገ​ኘው ወርቅ ብዙ እንደ ሆነ ባዩ ጊዜ የን​ጉሡ ጸሓ​ፊና የካ​ህ​ናቱ አለቃ ይመጡ ነበር፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት የተ​ገ​ኘ​ውን ገን​ዘብ ሁሉ ቈጥ​ረው በከ​ረ​ጢት ውስጥ ያኖ​ሩት ነበር። 11የተ​ሰ​በ​ሰ​በ​ው​ንም ገን​ዘብ ሥራ​ውን በሚ​ሠ​ሩና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት በሚ​ጠ​ብ​ቁት እጅ ይሰጡ ነበር። እነ​ር​ሱም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ለሚ​ሠሩ ግን​በ​ኞ​ችና አና​ጢ​ዎች ይሰጡ ነበር። 12የተ​ና​ደ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ለመ​ጠ​ገን መክ​ፈል ለሚ​ያ​ሻው ሁሉ ድን​ጋ​ይ​ንና እን​ጨ​ትን ይገዙ ዘንድ፥ ለግ​ን​በ​ኞ​ችና ለድ​ን​ጋይ ወቃ​ሪ​ዎች ይሰ​ጡት ነበር። 13ነገር ግን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ከሚ​መ​ጣው ገን​ዘብ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የሚ​ሆኑ የብር መዝ​ጊ​ያ​ዎች፥ ጽዋ​ዎ​ችና ጕጠ​ቶች፥ ድስ​ቶ​ችም፥ መለ​ከ​ቶ​ችም፥ የወ​ር​ቅና የብር ዕቃ​ዎ​ችም አል​ተ​ሠ​ሩም ነበር። 14ነገር ግን ለሚ​ሠ​ሩት ይሰ​ጡት ነበር፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቤት ጠገ​ኑ​በት። 15ለሠ​ራ​ተ​ኞ​ችም ይከ​ፍሉ ዘንድ ገን​ዘ​ቡን የሚ​ወ​ስ​ዱ​ትን ሰዎች አይ​ቈ​ጣ​ጠ​ሩ​አ​ቸ​ውም ነበር፤ በታ​ማ​ኝ​ነት ይሠሩ ነበ​ርና። 16ስለ በደ​ልና ስለ ኀጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የሚ​ያ​መ​ጡት ገን​ዘ​ብም ለካ​ህ​ናት ነበር።
17በዚ​ያም ወራት የሶ​ርያ ንጉሥ አዛ​ሄል ዘመተ፤ ጌት​ንም ወግቶ ያዛት፤ አዛ​ሄ​ልም ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ለመ​ው​ጣት ፊቱን አቀና። 18የይ​ሁ​ዳም ንጉሥ ኢዮ​አስ አባ​ቶቹ የይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥና ኢዮ​ራም፥ አካ​ዝ​ያ​ስም የቀ​ደ​ሱ​ትን ቅዱስ ነገር፥ እር​ሱም የቀ​ደ​ሰ​ውን፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤትና በን​ጉ​ሡም ቤተ መዛ​ግ​ብት የተ​ገ​ኘ​ውን ወርቅ ሁሉ ወሰደ፤ ወደ ሶር​ያም ንጉሥ ወደ አዛ​ሄል ላከው። እር​ሱም ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ተመ​ለሰ።
19የቀ​ረ​ውም የኢ​ዮ​አስ ነገር፥ የሠ​ራ​ውም ሥራ ሁሉ፥ እነሆ፥ በይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት ታሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን? 20አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹም ተነ​ሥ​ተው ዐመ​ፁ​በት፥ ወደ ሲላ በሚ​ወ​ር​ደ​ውም መን​ገድ በመ​ሀሎ ቤት ኢዮ​አ​ስን ገደ​ሉት። 21አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹም የኢ​ያ​ሙ​ሃት#ዕብ. “ሰም​ዓት” ይላል። ልጅ ኢያ​ዜ​ክ​ርና የሳ​ሜር ልጅ ኢያ​ዛ​ብድ መቱት፤ ሞተም፤ በዳ​ዊ​ትም ከተማ ከአ​ባ​ቶቹ ጋር ቀበ​ሩት፤ ልጁም አሜ​ስ​ያስ በፋ​ን​ታው ነገሠ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ