የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ዜና መዋ​ዕል ካልእ 34

34
የኢ​ዮ​ስ​ያስ ዘመነ መን​ግ​ሥት
(2ነገ. 22፥1-2)
1ኢዮ​ስ​ያ​ስም መን​ገሥ በጀ​መረ ጊዜ የስ​ም​ንት ዓመት ልጅ ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ሠላሳ አንድ ዓመት ነገሠ። 2በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ቅን ነገር አደ​ረገ፤ በአ​ባ​ቱም በዳ​ዊት መን​ገድ ሄደ፤ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አላ​ለም። 3በነ​ገ​ሠም በስ​ም​ን​ተ​ኛው ዓመት ገና ብላ​ቴና ሳለ የአ​ባ​ቱን የዳ​ዊ​ትን አም​ላክ ይፈ​ልግ ጀመረ፤ በዐ​ሥራ ሁለ​ተ​ኛ​ውም ዓመት ይሁ​ዳ​ንና ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ከኮ​ረ​ብ​ታ​ውና ከዐ​ፀ​ዶቹ፥ ከተ​ቀ​ረ​ጹ​ትና ቀል​ጠው ከተ​ሠ​ሩት ምስ​ሎች ያነጻ ጀመር። 4የበ​ዓ​ሊ​ም​ንም መሠ​ዊ​ያ​ዎች በፊቱ አፈ​ረሰ፤ በላ​ዩም የነ​በ​ሩ​ትን ኮረ​ብ​ታ​ዎ​ችን ዐፀ​ዶ​ቹ​ንም ቈረጠ፤ የተ​ቀ​ረ​ጹ​ት​ንና ቀል​ጠው የተ​ሠ​ሩ​ት​ንም ምስ​ሎች ሰባ​በረ፤ አደ​ቀ​ቃ​ቸ​ውም፤ ይሠ​ዉ​ላ​ቸው በነ​በ​ሩት ሰዎች መቃ​ብ​ርም ላይ በተ​ና​ቸው። 5የካ​ህ​ኖ​ቻ​ቸ​ው​ንም አጥ​ንት በመ​ሠ​ዊ​ያ​ቸው ላይ አቃ​ጠለ። ይሁ​ዳ​ንና ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም አነጻ። 6የም​ና​ሴ​ንና የኤ​ፍ​ሬ​ም​ንም፥ የስ​ም​ዖ​ንና የን​ፍ​ታ​ሌ​ም​ንም ከተ​ሞች፥ በዙ​ሪ​ያ​ቸ​ውም ያለ​ውን ቦታ እን​ዲሁ አነጻ። 7መሠ​ዊ​ያ​ዎ​ቹ​ንም አፈ​ረሰ፤ የማ​ም​ለ​ኪያ#“የማ​ም​ለ​ኪያ” የሚ​ለው በዕብ. ብቻ። ዐፀ​ዶ​ቹ​ንና የተ​ቀ​ረ​ጹ​ትን ምስ​ሎ​ችም አደ​ቀቀ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሀገር ሁሉ የኮ​ረ​ብ​ታ​ዎ​ችን መስ​ገ​ጃ​ዎ​ች​አ​ጠፋ።#ዕብ. “የፀ​ሐ​ይን ምስ​ሎች ሁሉ ቈራ​ረጠ” ይላል። ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ተመ​ለሰ።
8በነ​ገ​ሠም በዐ​ሥራ ስም​ን​ተ​ኛው ዓመት ምድ​ሪ​ቱ​ንና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ካነጻ በኋላ፥ የሴ​ልያ ልጅ ሳፋን፥ የከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም አለቃ መዕ​ሴያ፥ ታሪክ ጸሓ​ፊ​ውም የኢ​ዮ​አ​ካዝ ልጅ ኢዮ​አክ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የአ​ም​ላ​ኩን ቤት ይጠ​ግኑ ዘንድ ሰደ​ዳ​ቸው። 9ወደ ታላ​ቁም ካህን ወደ ኬል​ቅ​ያስ መጡ፤ ሌዋ​ው​ያ​ኑም በረ​ኞች ከም​ና​ሴና ከኤ​ፍ​ሬም፥ ከአ​ለ​ቆ​ችም፥ ከቀ​ረ​ውም ከእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ፥ ከይ​ሁ​ዳና ከብ​ን​ያም ሁሉ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ከሚ​ኖ​ሩት የሰ​በ​ሰ​ቡ​ትን፥ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የቀ​ረ​በ​ውን ገን​ዘብ ሰጡት። 10የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቤት በሚ​ሠ​ሩት ላይ ለተ​ሾ​ሙት ሰጡ፤ እነ​ር​ሱም ይጠ​ግ​ኑና ያድሱ ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ለሚ​ሠሩ ሠራ​ተ​ኞች ሰጡ​አ​ቸው። 11የይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት ላፈ​ረ​ሱት ቤት ሰረ​ገ​ሎች ያደ​ርጉ ዘንድ፥ ለማ​ጋ​ጠ​ሚ​ያም እን​ጨት፥ የተ​ጠ​ረ​በ​ው​ንም ድን​ጋይ ይገዙ ዘንድ ለአ​ና​ጢ​ዎ​ችና ለጠ​ራ​ቢ​ዎች ሰጡ።
12ሰዎ​ቹም ሥራ​ውን በመ​ታ​መን አደ​ረጉ፤ በእ​ነ​ር​ሱም ላይ የተ​ሾ​ሙት፥ ሥራ​ው​ንም የሚ​ያ​ሠ​ሩት ሌዋ​ው​ያን ከሜ​ራሪ ልጆች ይኤ​ትና አብ​ድ​ያስ፥ ከቀ​ዓ​ትም ልጆች ዘካ​ር​ያ​ስና ሜሱ​ላም ነበሩ። ከሌ​ዋ​ው​ያ​ንም ወገን በዜማ ዕቃ ዐዋ​ቂ​ዎች፥ የነ​በሩ ሁሉ፥ 13በተ​ሸ​ካ​ሚ​ዎ​ችና ልዩ ልዩ ሥራ በሚ​ሠሩ ላይ ተሾ​መው ነበር፤ ጸሓ​ፊ​ዎ​ቹና አለ​ቆ​ቹም በረ​ኞ​ቹም ከሌ​ዋ​ው​ያን ወገን ነበሩ።
ካህኑ ኬል​ቅ​ያስ የሕ​ጉን መጽ​ሐፍ እንደ አገኘ
(2ነገ. 22፥3-20)
14ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት የቀ​ረ​በ​ውን ገን​ዘብ ባመጡ ጊዜ ካህኑ ኬል​ቅ​ያስ በሙሴ እጅ የተ​ሰ​ጠ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሕግ መጽ​ሐፍ አገኘ። 15ኬል​ቅ​ያ​ስም ጸሓ​ፊ​ውን ሳፋ​ንን፥ “የሕ​ጉን መጽ​ሐፍ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አግ​ኝ​ቼ​አ​ለሁ” ብሎ ነገ​ረው። ኬል​ቅ​ያ​ስም መጽ​ሐ​ፉን ለሳ​ፋን ሰጠው። 16ሳፋ​ንም መጽ​ሐ​ፉን ወደ ንጉሡ አመጣ፤ ለን​ጉ​ሡም ዳግ​መኛ እን​ዲህ አለው፥ “ወር​ቁ​ንና ብሩን፥ መባ​ው​ንም ሁሉ#“ወር​ቁ​ንና ብሩን፥ መባ​ው​ንም ሁሉ” የሚ​ለው በዕብ. የለም “ወር​ቅና መባ” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። የቤተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን#“የቤተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን” የሚ​ለው በግ​እዝ ብቻ። ሥራ ለሚ​ሠሩ ለአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ በእ​ጃ​ቸው ሰጧ​ቸው። 17በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት የተ​ገ​ኘ​ውን ገን​ዘብ አፈ​ሰሱ፤ በሥ​ራው ላይ ለተ​ሾ​ሙ​ትና ለሠ​ራ​ተ​ኞ​ቹም በእ​ጃ​ቸው ሰጡ።” 18ጸሓ​ፊ​ውም ሳፋን ለን​ጉሡ፥ “ካህኑ ኬል​ቅ​ያስ መጽ​ሐፍ ሰጠኝ” ብሎ ነገ​ረው። ሳፋ​ንም በን​ጉሡ ፊት አነ​በ​በው። 19ንጉ​ሡም የሕ​ጉን ቃል በሰማ ጊዜ ልብ​ሱን ቀደደ። 20ንጉ​ሡም ኬል​ቅ​ያ​ስን፥ የሳ​ፋ​ን​ንም ልጅ አኪ​ቃ​ምን፥ የሚ​ክ​ያ​ስ​ንም ልጅ አብ​ዶ​ንን፥ ጸሓ​ፊ​ው​ንም ሳፋ​ንን፥ የን​ጉ​ሡ​ንም ብላ​ቴና ዔሴ​ኢ​ያን፦ 21“በዚህ መጽ​ሐፍ የተ​ጻ​ፈ​ውን ሁሉ ያደ​ርጉ ዘንድ አባ​ቶ​ቻ​ችን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስላ​ል​ጠ​በቁ፥ በላ​ያ​ችን የነ​ደደ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ እጅግ ነውና ሄዳ​ችሁ ስለ ተገ​ኘው የመ​ጽ​ሐፍ ቃል ስለ​እኔ፥ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልና በይ​ሁዳ ስለ​ቀ​ሩ​ትም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጠይቁ” ብሎ አዘ​ዛ​ቸው።
22ኬል​ቅ​ያ​ስና እነ​ዚያ ንጉሡ ያዘ​ዛ​ቸው ወደ ልብስ ጠባ​ቂው ወደ ሐስራ ልጅ ወደ ቴቁዋ ልጅ ወደ ሴሌም ሚስት ወደ ነቢ​ይቱ ወደ ሕል​ዳና ሄዱ፤ እር​ስ​ዋም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በከ​ተ​ማ​ዪቱ በሁ​ለ​ተ​ኛው ክፍል ተቀ​ምጣ ነበር፤ ይህ​ንም ነገር ነገ​ሩ​አት። 23እር​ስ​ዋም አለ​ቻ​ቸው፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ወደ እኔ ለላ​ካ​ችሁ ሰው እን​ዲህ ብላ​ችሁ ንገ​ሩት፦ 24እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በዚህ ስፍ​ራና በሚ​ኖ​ሩ​በት ላይ በይ​ሁዳ ንጉሥ ፊት በተ​ነ​በ​በው መጽ​ሐፍ የተ​ጻ​ፉ​ትን ቃላት ሁሉ፥ ማለት ክፉ ነገ​ርን አመ​ጣ​ለሁ፥ 25በእ​ጃ​ቸው ሥራ ሁሉ ሊያ​ስ​ቈ​ጡኝ ትተ​ው​ኛ​ልና፥ ለሌ​ሎ​ችም አማ​ል​ክት አጥ​ነ​ዋ​ልና ቍጣዬ በዚህ ስፍራ ላይ ይነ​ድ​ዳል፤ አይ​ጠ​ፋ​ምም። 26እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ለመ​ጠ​የቅ ለላ​ካ​ችሁ ለይ​ሁዳ ንጉሥ እን​ዲህ በሉት፦ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ስለ ሰማ​ኸው ቃል ልብህ ደን​ግ​ጦ​አ​ልና፥ 27በፊ​ቴም ራስ​ህን አዋ​ር​ደ​ሃ​ልና፥ በዚ​ህም ስፍራ በሚ​ኖ​ሩ​በት ላይ ቃሌን በሰ​ማህ ጊዜ ራስ​ህን አዋ​ር​ደ​ሃ​ልና፥ ልብ​ስ​ህ​ንም ቀድ​ደህ በፊቴ አል​ቅ​ሰ​ሃ​ልና እኔ ደግሞ ሰም​ቼ​ሃ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። 28እነሆ፥ ወደ አባ​ቶ​ችህ እሰ​በ​ስ​ብ​ሃ​ለሁ፤ በሰ​ላ​ምም ወደ መቃ​ብ​ርህ ትሰ​በ​ሰ​ባ​ለህ፤ በዚ​ህም ስፍ​ራና በሚ​ኖ​ሩ​በት ላይ የማ​መ​ጣ​ውን ክፉ ነገር ሁሉ ዐይ​ኖ​ችህ አያ​ዩም” ያለ​ቻ​ቸ​ው​ንም ነገር ለን​ጉሡ አስ​ረ​ዱት።
29ንጉ​ሡም ላከ፤ የይ​ሁ​ዳ​ንና የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ሁሉ ሰበ​ሰበ። 30ንጉ​ሡም፥ የይ​ሁ​ዳም ሰዎች ሁሉ፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም የሚ​ኖ​ሩና ካህ​ናቱ፥ ሌዋ​ው​ያ​ኑም፥ ሕዝ​ቡም ሁሉ ከታ​ናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ወጡ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት የተ​ገ​ኘ​ውን የቃል ኪዳ​ኑን መጽ​ሐፍ ቃል ሁሉ በጆ​ሮ​አ​ቸው አነ​በበ። 31ንጉ​ሡም በዐ​ምዱ ቆሞ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተከ​ትሎ እን​ዲ​ሄድ፥ ትእ​ዛ​ዙ​ንና ምስ​ክ​ሩን፥ ሥር​ዐ​ቱ​ንም በፍ​ጹም ልቡና በፍ​ጹም ነፍሱ እን​ዲ​ጠ​ብቅ፥ በዚ​ህም መጽ​ሐፍ የተ​ጻ​ፈ​ውን የቃል ኪዳን ቃል እን​ዲ​ያ​ደ​ርግ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቃል ኪዳን አደ​ረገ። 32በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምና በብ​ን​ያ​ምም ሀገር የተ​ገ​ኙ​ትን ሁሉ በዚህ ነገር አማለ። በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም የሚ​ኖሩ እንደ አባ​ቶ​ቻ​ቸው አም​ላክ እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ቃል ኪዳን አደ​ረጉ። 33ኢዮ​ስ​ያ​ስም ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ምድር ሁሉ ርኩ​ሱን ሁሉ አስ​ወ​ገደ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም የተ​ገ​ኙ​ትን ሁሉ አም​ላ​ካ​ቸ​ውን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ዲ​ያ​መ​ልኩ አደ​ረገ። በዘ​መኑ ሁሉ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ከመ​ከ​ተል አል​ራ​ቁም።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ