የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ነገ​ሥት ቀዳ​ማዊ 5

5
ሰሎ​ሞን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤተ መቅ​ደ​ስን ለመ​ሥ​ራት ያደ​ረ​ገው ዝግ​ጅት
(2ዜ.መ. 2፥1-18)
1የጢ​ሮስ ንጉሥ ኪራም ለአ​ባቱ ለዳ​ዊት በዘ​መኑ ሁሉ ወዳጁ ስለ ነበረ፥ ሰሎ​ሞን በአ​ባቱ ፋንታ ንጉሥ ለመ​ሆን እንደ ተቀባ ሰምቶ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ሊቀ​ቡት ላከ” ይላል። አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹን ወደ ሰሎ​ሞን ላከ። 2ሰሎ​ሞ​ንም ወደ ኪራም እን​ዲህ ብሎ ላከ፦ 3“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ግሩ በታች እስ​ኪ​ጥ​ል​ለት ድረስ በዙ​ሪ​ያው ስለ ነበረ ጦር​ነት አባቴ ዳዊት ለአ​ም​ላኩ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ለአ​ም​ላኬ” ይላል። ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ቤት መሥ​ራት እን​ዳ​ል​ቻለ አንተ ታው​ቃ​ለህ። 4አሁ​ንም አም​ላኬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዙ​ሪ​ያዬ ካሉት ዕረ​ፍት ሰጥ​ቶ​ኛል፤ ክፉም ነገር የሚ​ያ​ደ​ርግ ጠላት የለ​ብ​ኝም። 5እነ​ሆም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ባቴ ለዳ​ዊት፦ በአ​ንተ ፋንታ በዙ​ፋ​ንህ ላይ የማ​ስ​ቀ​ም​ጠው ልጅህ እርሱ ለስሜ ቤት ይሠ​ራል ብሎ እንደ ነገ​ረው፥ ለአ​ም​ላኬ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ቤት እሠራ ዘንድ አስ​ባ​ለሁ። 6አሁ​ንም ከወ​ገኔ እንደ ሲዶ​ና​ው​ያን እን​ጨት መቍ​ረጥ የሚ​ያ​ውቅ እን​ደ​ሌለ ታው​ቃ​ለ​ህና የዝ​ግባ ዛፍ ከሊ​ባ​ኖስ ይቈ​ር​ጡ​ልኝ ዘንድ አገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ህን እዘዝ፤ አገ​ል​ጋ​ዮቼም ከአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ጋር ይሁኑ፤ የአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ህ​ንም ዋጋ እንደ ተና​ገ​ር​ኸው ሁሉ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ።”
7ኪራ​ምም የሰ​ሎ​ሞ​ንን ቃል ሰምቶ እጅግ ደስ አለ​ውና፥ “በዚህ ታላቅ ሕዝብ ላይ ጥበ​በኛ ልጅ ለዳ​ዊት የሰጠ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዛሬ ይመ​ስ​ገን” አለ። 8ኪራ​ምም እን​ዲህ ሲል ወደ ሰሎ​ሞን ላከ፥ “የላ​ክ​ህ​ብ​ኝን ሁሉ ሰማሁ፤ ስለ ዝግ​ባ​ውና ስለ ጥዱ እን​ጨት ፈቃ​ድ​ህን ሁሉ አደ​ር​ጋ​ለሁ። 9አገ​ል​ጋ​ዮቼ ከሊ​ባ​ኖስ ወደ ባሕር ያወ​ር​ዱ​ል​ሃል፤ እኔም በመ​ር​ከብ አድ​ርጌ በባ​ሕር ላይ እያ​ን​ሳ​ፈ​ፍሁ አንተ እስከ ወሰ​ን​ኸው ስፍራ ድረስ አደ​ር​ስ​ል​ሃ​ለሁ፤ በዚ​ያም እፈ​ታ​ዋ​ለሁ፤ አን​ተም ከዚያ ታስ​ወ​ስ​ደ​ዋ​ለህ፤ አን​ተም ፈቃ​ዴን ታደ​ር​ጋ​ለህ፤ ለቤተ ሰቦ​ቼም ቀለብ የሚ​ሆ​ነ​ውን ትሰ​ጠ​ኛ​ለህ።” 10እን​ዲ​ሁም ኪራም የዝ​ግ​ባ​ው​ንና የጥ​ዱን እን​ጨት፥ የሚ​ሻ​ው​ንም ሁሉ ለሰ​ሎ​ሞን ሰጠው። 11ሰሎ​ሞ​ንም ለኪ​ራም ስለ ቤቱ ቀለብ ሃያ ሺህ የቆ​ሮስ መስ​ፈ​ሪያ ስንዴ፥ ሃያ ሺህም በቤት መስ​ፈ​ሪያ ጥሩ ዘይት ይሰ​ጠው ነበር፤ ሰሎ​ሞ​ንም ለኪ​ራም በየ​ዓ​መቱ ይህን ይሰጥ ነበር። 12እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ነገ​ረው ለሰ​ሎ​ሞን ጥበ​ብን ሰጠው፤ በኪ​ራ​ምና በሰ​ሎ​ሞ​ንም መካ​ከል ሰላም ነበረ፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም ቃል ኪዳን አደ​ረጉ።
13ሰሎ​ሞ​ንም ከእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ገባ​ሮ​ቹን መርጦ አወጣ፤ የገ​ባ​ሮ​ቹም ቍጥር ሠላሳ ሺህ ሰዎች ነበረ። 14በየ​ወ​ሩም እያ​ፈ​ራ​ረቀ ወደ ሊባ​ኖስ ዐሥር ዐሥር ሺህ ይልክ ነበር፤ አንድ ወርም በሊ​ባ​ኖስ፥ ሁለት ወርም በቤ​ታ​ቸው ይቀ​መጡ ነበር። አዶ​ኒ​ራ​ምም የገ​ባ​ሪ​ዎች አለቃ ነበረ። 15ለሰ​ሎ​ሞ​ንም ሰባ ሺህ ተሸ​ካ​ሚ​ዎች፥ ሰማ​ንያ ሺህም በተ​ራ​ራው ላይ ድን​ጋይ የሚ​ጠ​ርቡ ጠራ​ቢ​ዎች ነበ​ሩት። 16ይኸ​ውም በሰ​ሎ​ሞን ሥራ ላይ ከተ​ሾ​ሙት ከሦ​ስት ሺህ ስድ​ስት መቶ#ዕብ. “ሦስት ሺህ ሦስት መቶ” ይላል። የሠ​ራ​ተ​ኞች አለ​ቆች ሌላ ነው። 17ንጉ​ሡም የለ​ዘቡ ታላ​ላቅ ድን​ጋ​ዮ​ች​ንና ለቤ​ቱም መሠ​ረት ያል​ተ​ጠ​ረ​በ​ውን ድን​ጋይ ያመጡ ዘንድ አዘዘ። 18የሰ​ሎ​ሞ​ንና የኪ​ራም አና​ጢ​ዎች፥ ጌባ​ላ​ው​ያ​ንም ወቀ​ሩ​አ​ቸው፤ ለመ​ሠ​ረ​ትም አኖ​ሩ​አ​ቸው፤ ቤቱ​ንም ለመ​ሥ​ራት እን​ጨ​ቱ​ንና ድን​ጋ​ዮ​ቹን ሦስት ዓመት አዘ​ጋጁ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ