የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ነገ​ሥት ቀዳ​ማዊ 6

6
ሰሎ​ሞን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤተ መቅ​ደስ እንደ ሠራ
1የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከግ​ብፅ ምድር ከወጡ አራት መቶ ሰማ​ንያ አራት#ግሪክ ሰባ. ሊ. “አራት መቶ አርባ” ይላል። ዓመት በሆነ ጊዜ፥ ሰሎ​ሞን በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ በነ​ገሠ በአ​ራ​ተ​ኛው ዓመት፥ ዚፍ በሚ​ባ​ለው በሁ​ለ​ተ​ኛው ወር የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት መሥ​ራት ጀመረ። 2ንጉሡ ሰሎ​ሞ​ንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሠ​ራው ቤት ርዝ​መቱ ስድሳ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “አርባ” ይላል። ክንድ፥ ወር​ዱም ሃያ ክንድ፥ ቁመ​ቱም ሠላሳ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ሃያ አም​ስት” ይላል። ክንድ ነበረ። 3በመ​ቅ​ደ​ሱም ፊት ወለል ነበረ፤ ርዝ​መ​ቱም እንደ መቅ​ደሱ ወርድ ሃያ ክንድ፥ ወር​ዱም ከቤቱ ወደ ፊት ዐሥር ክንድ ነበረ፤ ቤቱ​ንም ሠርቶ ጨረሰ። 4ለቤ​ቱም በዐ​ይነ ርግብ የተ​ዘጉ መስ​ኮ​ቶ​ችን አደ​ረገ። 5በቤ​ቱም ግንብ ዙሪያ፥ በመ​ቅ​ደ​ሱና በቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳኑ ግንብ ዙሪያ ደርብ ሠራ፤ በዙ​ሪ​ያ​ውም ጓዳ​ዎች አደ​ረገ። 6የታ​ች​ኛ​ውም ደርብ ወርዱ አም​ስት ክንድ፥ የመ​ካ​ከ​ለ​ኛ​ውም ደርብ ወርዱ ስድ​ስት ክንድ፥ የሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ደርብ ወርዱ ሰባት ክንድ ነበረ። ሰረ​ገ​ሎቹ በቤቱ ግንብ ውስጥ እን​ዳ​ይ​ገቡ ከቤቱ ግንብ ውጭ አረ​ፍ​ቶ​ችን አደ​ረገ። 7ቤቱም በተ​ሠራ ጊዜ ፈጽ​መው በተ​ወ​ቀሩ ድን​ጋ​ዮች ተሠራ፤ ሲሠ​ሩ​ትም መራ​ጃና መጥ​ረ​ቢያ፥ የብ​ረ​ትም ዕቃ ሁሉ በቤቱ ውስጥ አል​ተ​ሰ​ማም። 8የታ​ች​ኛ​ውም ደርብ ጓዳ​ዎች በር በቤቱ ቀኝ አጠ​ገብ ነበረ። ከዚ​ያም ወደ መካ​ከ​ለ​ኛው ደርብ፥ ከመ​ካ​ከ​ለ​ኛ​ውም ወደ ሦስ​ተ​ኛው ደርብ የሚ​ወ​ጡ​በት መውጫ ነበ​ረው። 9ቤቱ​ንም ሠርቶ ፈጸ​መው፤ የቤ​ቱ​ንም ጠፈር በዝ​ግባ ሳን​ቃ​ዎች አደ​ረገ። 10በቤ​ቱም ዙሪያ ሁሉ ቁመ​ታ​ቸው አም​ስት አም​ስት ክንድ የሆኑ ደር​ቦ​ችን ሠራ፤ ከቤ​ቱም ጋር በዝ​ግባ እን​ጨት አጋ​ጠ​ማ​ቸው።
11የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ ሰሎ​ሞን እን​ዲህ ሲል መጣ፦ 12“ስለ​ዚህ ስለ​ም​ት​ሠ​ራ​ልኝ ቤት በሥ​ር​ዐቴ ብት​ሄድ፥ ፍር​ዴ​ንም ብታ​ደ​ርግ፥ ትመ​ላ​ለ​ስ​ባ​ቸ​ውም ዘንድ ትእ​ዛ​ዞቼን ሁሉ ብት​ጠ​ብቅ፥ ለአ​ባ​ትህ ለዳ​ዊት የነ​ገ​ር​ሁ​ትን ቃል ከአ​ንተ ጋር አጸ​ና​ለሁ። 13በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች መካ​ከል እኖ​ራ​ለሁ፤ ሕዝ​ቤ​ንም እስ​ራ​ኤ​ልን አል​ጥ​ልም።”
14ሰሎ​ሞ​ንም ቤቱን ሠራው፤ ፈጸ​መ​ውም። 15የቤ​ቱ​ንም ግንብ ውስ​ጡን በዝ​ግባ ሳንቃ ለበጠ፤ ከቤ​ቱም መሠ​ረት ጀምሮ እስከ ጣራው ድረስ የው​ስ​ጡን ግንብ በእ​ን​ጨት ለበ​ጠው፤ ደግ​ሞም የቤ​ቱን ወለል በጥድ እን​ጨት አነ​ጠ​ፈው። 16ከቤተ መቅ​ደሱ አያ​ይዞ ከመ​ሠ​ረቱ ጀምሮ እስከ ጣራው ድረስ ሃያ​ውን ክንድ በዝ​ግባ ጠርብ ሠራ፤ ከመ​ቅ​ደ​ሱም ከፍሎ ቅድ​ስተ ቅዱ​ሳ​ኑን አደ​ረገ። 17በቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳኑ ፊት ያለ​ውም መቅ​ደስ ርዝ​መቱ አርባ ክንድ ነበረ። 18የቤ​ቱ​ንም ውስጥ በተ​ጐ​በ​ጐ​በና በፈ​ነዳ አበባ፥ በተ​ቀ​ረጸ ዝግባ ለበ​ጠው፤ ሁሉም ዝግባ ነበረ፤ ድን​ጋ​ዩም አል​ታ​የም ነበር። 19በዚ​ያም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ኪዳን ታቦት ያኖር ዘንድ በቤቱ ውስጥ ቅድ​ስተ ቅዱ​ሳ​ኑን አበጀ። 20የቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳ​ኑም ርዝ​መት ሃያ ክንድ፥ ስፋ​ቱም ሃያ ክንድ፥ ቁመ​ቱም ሃያ ክንድ ነበረ፤ በጥ​ሩም ወርቅ ለበ​ጠው። 21በቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳ​ኑም ፊት ከዝ​ግባ መሠ​ዊ​ያን ሠራ፤ በጥሩ ወር​ቅም ለበ​ጠው። 22የሠ​ራው ቤት ሁሉ እስከ ተፈ​ጸመ ድረስ ቤቱን ሁሉ በወ​ርቅ ለበ​ጠው፤ በቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳ​ኑም ፊት የነ​በ​ረ​ውን መሠ​ዊያ ሁሉ በወ​ርቅ ለበ​ጠው።
23በቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳ​ኑም ውስጥ ቁመ​ታ​ቸው ዐሥር ክንድ የሆነ ከወ​ይራ እን​ጨት#“ከወ​ይራ እን​ጨት” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ሁለት ኪሩ​ቤ​ልን ሠራ። 24የኪ​ሩ​ብም አን​ደ​ኛው ክንፍ አም​ስት ክንድ፥ የኪ​ሩ​ብም ሁለ​ተ​ኛው ክንፍ አም​ስት ክንድ ነበረ፤ ከአ​ን​ደ​ኛው ክንፍ ጫፍ ጀምሮ እስከ ሁለ​ተ​ኛው ክንፍ ጫፍ ድረስ ዐሥር ክንድ ነበረ። 25እን​ደ​ዚ​ሁም ሁለ​ተ​ኛው ኪሩብ ዐሥር ክንድ ነበረ፤ ሁለ​ቱም ኪሩ​ቤል አንድ ልክና አንድ መልክ ነበሩ። 26የአ​ንዱ ኪሩብ ቁመት ዐሥር ክንድ ነበረ፤ የሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ኪሩብ እን​ዲሁ ነበረ። 27ሁለ​ቱም ኪሩ​ቤል በው​ስ​ጠ​ኛው ቤት መካ​ከል ነበሩ። የኪ​ሩ​ቤ​ልም ክን​ፎ​ቻ​ቸው ተዘ​ር​ግ​ተው ነበር፤ የአ​ን​ዱም ኪሩብ ክንፍ አን​ደ​ኛ​ውን ግንብ ይነካ ነበር፤ የሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ኪሩብ ክንፍ ሁለ​ተ​ኛ​ውን ግንብ ይነካ ነበር፤ የሁ​ለ​ቱም ክን​ፎች በቤቱ መካ​ከል እርስ በር​ሳ​ቸው ይነ​ካኩ ነበር። 28ኪሩ​ቤ​ል​ንም በወ​ርቅ ለበ​ጣ​ቸው።
29በቤ​ቱም ግንብ ሁሉ ዙሪያ በው​ስ​ጥና በውጭ የኪ​ሩ​ቤ​ልና የዘ​ን​ባባ ዛፍ፥ የፈ​ነ​ዳም አበባ ሥዕል ቀረጸ። 30የቤ​ቱ​ንም ወለል በው​ስ​ጥና በውጭ በወ​ርቅ ለበጠ። 31ለቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳ​ኑም መግ​ቢያ ከወ​ይራ እን​ጨት ሳን​ቃ​ዎ​ችን ሠራ፤ መድ​ረ​ኩ​ንና መቃ​ኖ​ቹን፥ ደፉ​ንም አም​ስት ማዕ​ዘን አደ​ረገ። 32ሁለ​ቱ​ንም ሣን​ቃ​ዎች ከወ​ይራ እን​ጨት ሠራ፤ የኪ​ሩ​ቤ​ል​ንና የዘ​ን​ባባ ዛፍ፥ የፈ​ነ​ዳም አበባ ሥዕል ቀረ​ጸ​ባ​ቸው፤ በወ​ር​ቅም ለበ​ጣ​ቸው፤ ኪሩ​ቤ​ል​ንና የዘ​ን​ባ​ባ​ውን ዛፍ በወ​ርቅ ለበጠ። 33እን​ዲ​ሁም ለመ​ቅ​ደሱ መግ​ቢያ ከወ​ይራ እን​ጨት አራት ማዕ​ዘን መቃን አደ​ረገ። 34ሁለ​ቱ​ንም ደጆች ከጥድ እን​ጨት ሠራ፤ አንዱ ደጅ በማ​ጠ​ፊያ ከተ​ያ​ያዙ ከሁ​ለት ሣን​ቃ​ዎች ተሠራ፤ ሁለ​ተ​ኛ​ውም ደጅ በማ​ጠ​ፊያ ከተ​ያ​ያዙ ከሁ​ለት ሣን​ቃ​ዎች ተሠራ። 35የኪ​ሩ​ቤ​ል​ንና የዘ​ን​ባባ ዛፍ፥ የፈ​ነ​ዳም አበባ ሥዕል ቀረ​ጸ​ባ​ቸው፤ በተ​ቀ​ረ​ጸ​ውም ሥራ ላይ በወ​ርቅ ለበ​ጣ​ቸው፤ እስከ መድ​ረ​ካ​ቸ​ውም የተ​ያ​ያዙ ነበሩ። 36የው​ስ​ጠ​ኛ​ው​ንም አደ​ባ​ባይ ቅጥር ሦስ​ቱን ተራ በተ​ጠ​ረበ ድን​ጋይ፥ አን​ዱ​ንም ተራ በዝ​ግባ ሣንቃ ሠራው፤ በመ​ቅ​ደሱ ፊት ለፊት ላለው ቤት ወለ​ልም መጋ​ረጃ ሠራ።#“በመ​ቅ​ደሱ ፊት ለፊት ላለው ቤት ወለ​ልም መጋ​ረጃ ሠራ” የሚ​ለው በዕብ. የለም።
37በአ​ራ​ተ​ኛው ዓመት ከሚ​ያ​ዝያ በሁ​ለ​ተ​ኛው ወር#ዕብ. “ዚፍ” ይላል። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት መሠ​ረተ። 38በዐ​ሥራ አን​ደ​ኛ​ውም ዓመት ቡል በሚ​ባል በስ​ም​ን​ተ​ኛው ወር ቤቱ እንደ ክፍ​ሎ​ቹና እንደ ሥር​ዐቱ ሁሉ ተጨ​ረሰ። በሰ​ባት ዓመ​ትም ሠራው።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ