መጽ​ሐፈ ነገ​ሥት ቀዳ​ማዊ 3

3
ሰሎ​ሞን ጥበ​ብን እንደ ለመነ
(2ዜ.መ. 1፥3-12)
1ሰሎ​ሞ​ንም ለግ​ብፅ ንጉሥ ለፈ​ር​ዖን አማች ሆነ፤ የፈ​ር​ዖ​ን​ንም ልጅ አገባ፤ ቤቱ​ንና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቤት፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ዙሪያ ያለ​ውን ቅጥር ሠርቶ እስ​ኪ​ፈ​ጽም ድረስ ወደ ዳዊት ከተማ አም​ጥቶ አስ​ገ​ባት። 2እስ​ከ​ዚ​ያም ቀን ድረስ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አል​ተ​ሠ​ራም ነበ​ርና ሕዝቡ በኮ​ረ​ብታ ላይ ይሠ​ዉና ያጥኑ ነበር። 3ሰሎ​ሞ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ይወ​ድድ ነበር፤ በአ​ባ​ቱም በዳ​ዊት ሥር​ዐት ይሄድ ነበር፤ ነገር ግን በኮ​ረ​ብ​ታው ላይ ይሠ​ዋና ያጥን ነበር።
4ገባ​ዖን ፈጽማ ትሰፋ ነበ​ርና በዚያ መሥ​ዋ​ዕት ይሠዋ ዘንድ ተነ​ሥቶ ሄደ፤ ሰሎ​ሞ​ንም በዚያ መሠ​ዊያ ላይ በገ​ባ​ዖን አንድ ሺህ የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ሠዋ። 5እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በገ​ባ​ዖን ለሰ​ሎ​ሞን በሌ​ሊት በሕ​ልም ተገ​ለ​ጠ​ለት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰሎ​ሞ​ንን፥ “እን​ድ​ሰ​ጥህ የም​ት​ፈ​ል​ገ​ውን ለምን” አለው። 6ሰሎ​ሞ​ንም አለ፥ “እርሱ በፊ​ትህ በእ​ው​ነ​ትና በጽ​ድቅ፥ በል​ብም ቅን​ነት ከአ​ንተ ጋር እንደ ሄደ፥ ከአ​ባቴ ከባ​ሪ​ያህ ከዳ​ዊት ጋር ታላቅ ቸር​ነት አድ​ር​ገ​ሃል፤ ዛሬ እንደ ሆነም በዙ​ፋኑ ላይ የሚ​ቀ​መጥ ልጅ ሰጥ​ተህ ታላ​ቁን ቸር​ነ​ት​ህን አቈ​ይ​ተ​ህ​ለ​ታል። 7አሁ​ንም አቤቱ አም​ላኬ ሆይ፥ እኔን ባሪ​ያ​ህን በአ​ባቴ በዳ​ዊት ፋንታ አን​ግ​ሠ​ኸ​ኛል፤ እኔም መው​ጫ​ዬ​ንና መግ​ቢ​ያ​ዬን የማ​ላ​ውቅ ታናሽ ብላ​ቴና ነኝ። 8ባሪ​ያ​ህም ያለው አንተ በመ​ረ​ጥ​ኸው ሕዝ​ብህ፥ ስለ ብዛ​ቱም ይቈ​ጠር ዘንድ በማ​ይ​ቻል በታ​ላቅ ሕዝብ መካ​ከል ነው። 9ስለ​ዚ​ህም ሰምቶ በሕ​ዝ​ብህ ላይ መፍ​ረድ ይችል ዘንድ፥ መል​ካ​ሙ​ንና ክፉ​ው​ንም ይለይ ዘንድ ለባ​ሪ​ያህ አስ​ተ​ዋይ ልቡና ስጠው፤ አለ​ዚ​ያማ በዚህ በታ​ላቅ ሕዝብ ላይ ይፈ​ርድ ዘንድ ማን ይች​ላል?”
10ሰሎ​ሞ​ንም ይህን ነገር ስለ ለመነ፥ ነገሩ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ደስ አሰ​ኘው። 11እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለው፥ “ፍር​ድን ትለይ ዘንድ ለራ​ስህ ማስ​ተ​ዋ​ልን ለመ​ንህ እንጂ ለራ​ስህ ብዙ ዘመ​ና​ትን፥ ባለ​ጠ​ግ​ነ​ት​ንም፥ የጠ​ላ​ቶ​ች​ህ​ንም ነፍስ ሳት​ለ​ምን ይህን ነገር ለም​ነ​ሃ​ልና፥ 12እነሆ፥ እኔ እንደ ቃልህ አድ​ር​ጌ​ል​ሃ​ለሁ፤ እነ​ሆም፥ ማንም የሚ​መ​ስ​ልህ ከአ​ንተ በፊት እን​ደ​ሌለ፥ ከአ​ን​ተም በኋላ እን​ዳ​ይ​ነሣ አድ​ርጌ ጥበ​በ​ኛና አስ​ተ​ዋይ ልቡና ሰጥ​ቼ​ሃ​ለሁ። 13ደግ​ሞም ከነ​ገ​ሥ​ታት የሚ​መ​ስ​ልህ ማንም እን​ዳ​ይ​ኖር ያል​ለ​መ​ን​ኸ​ውን ባለ​ጠ​ግ​ነ​ትና ክብር ሰጥ​ቼ​ሃ​ለሁ። 14አባ​ት​ህም ዳዊት እንደ ሄደ፥ ሥር​ዐ​ቴ​ንና ትእ​ዛ​ዜን ትጠ​ብቅ ዘንድ በመ​ን​ገዴ የሄ​ድህ እንደ ሆነ፥ ዘመ​ን​ህን አበ​ዛ​ል​ሀ​ለሁ።” 15ሰሎ​ሞ​ንም ነቃ፤ እነ​ሆም፥ ሕልም ነበረ፤ ተነ​ሥ​ቶም ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሄደ፤ በጽ​ዮ​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ኪዳን ታቦት ፊት ቆመ፤ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት አሳ​ረገ፤ የደ​ኅ​ን​ነ​ት​ንም መሥ​ዋ​ዕት አቀ​ረበ፤ ለአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ቹም ሁሉ ታላቅ ግብዣ አደ​ረገ።
ጥበብ የሞ​ላ​በት የሰ​ሎ​ሞን ፍርድ
16በዚያ ጊዜም ሁለት ጋለ​ሞ​ታ​ዎች ሴቶች ወደ ንጉሡ መጥ​ተው ቆሙ። 17አን​ደ​ኛ​ዪ​ቱም ሴት አለች፥ “ጌታዬ ሆይ! ስማኝ፥ እኔና ይህች ሴት በአ​ንድ ቤት እን​ኖ​ራ​ለን፤ በአ​ንድ ቤትም ወለ​ድን። 18እኔም በወ​ለ​ድሁ በሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን ይህች ሴት ወለ​ደች፤ እኛ በቤት ውስጥ አብ​ረን ነበ​ርን፤ ከሁ​ለ​ታ​ች​ንም በቀር ማንም በቤት ውስጥ አል​ነ​በ​ረም። 19እር​ስ​ዋም በላዩ ስለ ተኛ​ች​በት የዚ​ህች ሴት ልጅ በሌ​ሊት ሞተ። 20እር​ስ​ዋም በእ​ኩለ ሌሊት ተነ​ሥታ፥ እኔ አገ​ል​ጋ​ይህ ተኝቼ ሳለሁ፥ ልጄን ከብ​ብቴ ወሰ​ደች፤ በብ​ብ​ቷም አስ​ተ​ኛ​ችው፤ የሞ​ተ​ው​ንም ልጅ​ዋን በእኔ ብብት አስ​ተ​ኛ​ችው። 21ልጄ​ንም አጠባ ዘንድ በማ​ለዳ ብነሣ፥ ያን የሞ​ተ​ውን ልጅ አገ​ኘሁ፤ ነገር ግን ብር​ሃን በሆነ ጊዜ ተመ​ለ​ከ​ት​ሁት፤ እነ​ሆም፥ የወ​ለ​ድ​ሁት ልጄ አል​ነ​በ​ረም።” 22ሁለ​ተ​ኛ​ዪ​ቱም ሴት፥ “አይ​ደ​ለም ደኅ​ነ​ኛው የእኔ ልጅ ነው፤ የሞ​ተው የአ​ንቺ ልጅ ነው እንጂ አለች።”#ዕብ. “ይህ​ችም የሞ​ተው የአ​ንቺ ልጅ ነው፤ ደኅ​ነ​ኛ​ውም የእኔ ልጅ ነው” አለች የሚል ይጨ​ም​ራል። እን​ዲ​ሁም በን​ጉሡ ፊት ይነ​ጋ​ገሩ ነበር።
23በዚያ ጊዜም ንጉሡ፥ “አንቺ፦ ደኅ​ነ​ኛው የእኔ ልጅ ነው፤ የሞ​ተ​ውም የአ​ንቺ ልጅ ነው ትያ​ለሽ፤ አን​ቺም፦ አይ​ደ​ለም የሞ​ተው የአ​ንቺ ልጅ ነው፤ ደኅ​ነ​ኛ​ውም የእኔ ልጅ ነው ትያ​ለሽ”። አላ​ቸው። 24ንጉ​ሡም፥ “ሰይፍ አም​ጡ​ልኝ” አለ፤ እነ​ር​ሱም ወደ ንጉሡ ሰይፍ አመጡ። 25ንጉ​ሡም፥ “ደኅ​ነ​ኛ​ውን ሕፃን ለሁ​ለት ቈር​ጣ​ችሁ ለአ​ን​ዲቱ አን​ዱን ክፍል፥ ለሁ​ለ​ተ​ኛ​ዪ​ቱም ሁለ​ተ​ኛ​ውን ክፍል ስጡ” አለ። 26ደኅ​ነ​ኛ​ውም ሕፃን የነ​በ​ራት ሴት አን​ጀ​ትዋ ስለ ልጅዋ ታው​ኳ​ልና፥ “ጌታዬ ሆይ! አይ​ደ​ለም፤ ደኅ​ነ​ኛ​ውን ለእ​ር​ስዋ ስጣት እንጂ መግ​ደ​ልስ አት​ግ​ደ​ሉት” ብላ ለን​ጉሡ ተና​ገ​ረች። ያች​ኛ​ዪቱ ግን፥ “አካ​ፍ​ሉን እንጂ ለእ​ኔም ለእ​ር​ስ​ዋም አይ​ሁን” አለች። 27ንጉ​ሡም መልሶ እን​ዲህ አለ፥ “ለእ​ር​ስዋ ስጧት እንጂ መግ​ደ​ልስ አት​ግ​ደ​ሉት ላለ​ችው ሴት ስጡ​አት፤ እናቱ እር​ስዋ ናትና።” 28ንጉ​ሡም የፈ​ረ​ደ​ውን ፍርድ እስ​ራ​ኤል ሁሉ ሰሙ፤ ፍር​ድን ለማ​ድ​ረግ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጥበብ በእ​ርሱ ላይ እንደ ነበረ አይ​ተ​ዋ​ልና ከን​ጉሡ ፊት የተ​ነሣ ፈሩ።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ