መጽ​ሐፈ ዕዝራ ሱቱ​ኤል 3

3
የዓ​ለም ፍጻሜ ምል​ክት
1“ምል​ክ​ቱም እነሆ፥ ወራት ይመ​ጣል፤ በም​ድር የሚ​ኖ​ሩ​ት​ንም ሰዎች ታላቅ ድን​ጋፄ ይይ​ዛ​ቸ​ዋል፤ የጽ​ድቅ መን​ገ​ድም ትሰ​ወ​ራ​ለች፤ ሃይ​ማ​ኖ​ትም ከሀ​ገር ትጠ​ፋ​ለች። 2በደ​ልም አንተ ከአ​የ​ኸ​ውና ከሰ​ማ​ኸው ይልቅ ይበ​ዛል። 3ዛሬ የጠ​ፋና የፈ​ረሰ ሆኖ የም​ታ​የ​ውም ሀገር ይጠ​ፋል፤ ምድ​ርም ምድረ በዳ ትሆ​ና​ለች። 4ልዑ​ልም ሕይ​ወ​ት​ህን ከሰ​ጠህ ከሦ​ስት ወራት በኋላ ምድ​ርን ስት​ታ​ወክ ታያ​ታ​ለህ፤ ፀሐ​ይም ድን​ገት በሌ​ሊት ያበ​ራል፤ ጨረ​ቃም ድን​ገት በቀን ያበ​ራል። 5ከእ​ን​ጨ​ቶ​ችም ደም ይፈ​ስ​ሳል፤ ድን​ጋ​ይም ትጮ​ኻ​ለች፤ ሕዝ​ቡም ይታ​ወ​ካሉ፤ ከዋ​ክ​ብ​ትም ይረ​ግ​ፋሉ።
6“ብዙ​ዎች ያል​ጠ​ረ​ጠ​ሩት ይነ​ግ​ሣል። 7ሁሉም ቃሉን ይሰ​ማል። 8በብዙ ሀገ​ሮች ሽብር ይሆ​ናል፤ ጥቅል እሳ​ትም ይላ​ካል፤ የም​ድረ በዳ አው​ሬ​ዎ​ችም ከቦ​ታ​ቸው ይፈ​ል​ሳሉ። ከሴ​ቶ​ችም ባለ ምል​ክት ይወ​ለ​ዳል። 9የሚ​ጣ​ፍ​ጠ​ውም ውኃ መራራ ይሆ​ናል፤ ወዳ​ጆ​ችም እንደ ጠላት በድ​ን​ገት እርስ በር​ሳ​ቸው ይጋ​ደ​ላሉ፤ ያን​ጊ​ዜም ጥበብ ትሰ​ወ​ራ​ለች፤ ምክ​ርም ወደ ማደ​ሪ​ያዋ ትመ​ለ​ሳ​ለች። 10ብዙ ሰዎች ይፈ​ል​ጓ​ታል፤ ነገር ግን አያ​ገ​ኙ​አ​ትም፤ በም​ድ​ርም ላይ ኀጢ​አት፥ ዐመ​ፅም፥ ስን​ፍ​ናም ትበ​ዛ​ለች። 11አን​ዲቱ ሀገር አቅ​ራ​ቢ​ያ​ዋን ሀገር ‘በውኑ በአ​ንቺ ዘንድ የተ​ደ​ረገ ጽድቅ አለን? ወይስ ጽድ​ቅን የሚ​ያ​ደ​ርግ ሰው አለን?’ ብላ ትጠ​ይ​ቃ​ታ​ለች። ያችም ‘የለም’ ትላ​ታ​ለች። 12በእ​ነ​ዚ​ያም ወራ​ቶች#“ሰዎች ብዙ ይመ​ኛሉ ነገር ግን አያ​ገ​ኙም ...” የሚል ዘርዕ ይገ​ኛል። ሰው ሞትን ይመ​ኛል፤ ነገር ግን አያ​ገ​ኝም፤ ሚስ​ትም ያገ​ባል፤ ደስም አይ​ለ​ውም፤ ይደ​ክ​ማል፤ ሥራ​ው​ንም ይሠ​ራል፤ መን​ገዱ ግን አይ​ከ​ና​ወ​ን​ለ​ትም። 13ይኽ​ንም ምል​ክት እነ​ግ​ርህ ዘንድ ተላ​ክሁ፤ ዛሬ እንደ ጾም​ህም ዳግ​መኛ ሰባት ቀን ብት​ጸ​ል​ይና ብታ​ለ​ቅስ ከዚህ የሚ​በ​ልጥ ትሰ​ማ​ለህ።”
14ዳግ​መ​ኛም ከእ​ን​ቅ​ልፌ ነቃሁ፤ ሰው​ነ​ቴም እጅግ ስቅ​ጥጥ አለ​ች​ብኝ፤ ሰው​ነ​ቴም እስ​ክ​ት​ዝል ድረስ ደከ​መች። 15ወደ እኔ የመ​ጣ​ውና የተ​ና​ገ​ረኝ መል​አ​ኩም እጄን ያዘኝ፤ በእ​ግ​ሬም አቁሞ አጸ​ናኝ።
16ከዚ​ህም በኋላ በሁ​ለ​ተ​ኛ​ዪቱ ሌሊት የሕ​ዝቡ ያለ​ቆ​ቻ​ቸው አለቃ ፍል​ስ​ጥ​ያል ወደ እኔ መጣ፤ እን​ዲ​ህም አለኝ፥ “አንተ ዕዝራ! ወዴት ነበ​ርህ? ፊት​ህስ ስለ ምን አዝ​ኗል? 17በም​ርኮ ሀገር ያሉ እስ​ራ​ኤል ሁሉ ለአ​ንተ አደራ እንደ ተሰ​ጡህ አታ​ው​ቅ​ምን? 18እን​ግ​ዲ​ህስ እስ​ራ​ኤ​ልን እን​ዳ​ት​ጥ​ላ​ቸው፥ መን​ጋ​ዎ​ች​ንም በክ​ፉ​ዎች ተኵ​ላ​ዎች አፍ እንደ ጣለ እረኛ እን​ዳ​ት​ሆን ተነ​ሥ​ተህ እህ​ልን ቅመስ።”
19እን​ዲ​ህም አል​ሁት፥ “ከእኔ ዘንድ ሂድ፤ ዳግ​መ​ኛም እስከ ሰባት ቀን ድረስ ወደ እኔ አት​ምጣ፤ ከዚ​ህም በኋላ ወደ እኔ ና፤ እኔም ነገ​ርን እነ​ግ​ር​ሃ​ለሁ፥”#“እኔም ነገ​ርን እነ​ግ​ር​ሃ​ለሁ” የሚ​ለው ከግ​እዙ በቀር በሌ​ሎች ቅጂ​ዎች የለም። ከእ​ኔም ዘንድ ሄደ።
ሁለ​ተ​ኛው ራእይ
20እኔም መል​አኩ ዑር​ኤል እን​ዳ​ዘ​ዘኝ አዝኜ እያ​ለ​ቀ​ስሁ ሰባት ቀን ጾምሁ። 21ከሰ​ባት ቀን በኋ​ላም የል​ቡ​ናዬ አሳብ እጅግ አደ​ከ​መኝ። 22የጥ​በ​ብም መን​ፈስ ሰው​ነ​ቴን አነ​ሣ​ሣ​ቻት፤ ዳግ​መ​ኛም በል​ዑል ፊት እና​ገር ጀመ​ርሁ። 23እን​ዲ​ህም አልሁ፥ “አቤቱ ጌታዬ፥ ከም​ድር ዛፎ​ችና እን​ጨ​ቶች ሁሉ አንድ የወ​ይን ሐረ​ግን ለአ​ንተ መረ​ጥህ። 24ከዓ​ለሙ ጥል​ቆች ሁሉ አንድ ወን​ዝን ለአ​ንተ መላህ። 25ከሀ​ገ​ሮ​ችም ሁሉ አንድ ሀገ​ርን መረ​ጥህ፤#ሌሎች ዘሮች “ከአ​በ​ቦ​ችም ሁሉ አን​ዲ​ት​ዋን የሱ​ሳን አበባ ለአ​ንተ መረ​ጥህ” የሚል ይጨ​ም​ራሉ። ከተ​ሠ​ሩት ከተ​ሞ​ችም ሁሉ ጽዮ​ንን ለአ​ንተ ቀደ​ስህ። 26ከተ​ፈ​ጠሩ ወፎ​ችም ሁሉ አንድ ርግ​ብን ለአ​ንተ ለየህ፤ ከተ​ፈ​ጠ​ሩት እን​ስ​ሳ​ትም ሁሉ አንድ በግን መረ​ጥህ። 27ከም​ድር አሕ​ዛብ ሁሉ አንድ ሕዝ​ብን ለራ​ስህ መረ​ጥህ፤ ለዚህ ለመ​ረ​ጥ​ኸው ሕዝ​ብ​ህም በሁሉ ዘንድ የተ​ፈ​ተነ ሕግ​ህን ሰጠ​ኸው።
28“አሁ​ንም አቤቱ፥ ይህን አን​ዱን ለብ​ዙ​ዎች አሳ​ል​ፈህ ለምን ሰጠ​ኸው? ከሌ​ሎ​ችም ሥሮች ለይ​ተህ አን​ዱን ሥር ለምን አጐ​ሳ​ቈ​ል​ኸው? አንድ ሕዝ​ብ​ንስ በብ​ዙ​ዎች መካ​ከል ለምን በተ​ን​ኸው? 29የተ​ስ​ፋህ ባላ​ጋ​ራ​ዎ​ችዋ በሕ​ግህ የታ​መ​ኑ​ትን ረገ​ጧ​ቸው። 30ወገ​ኖ​ች​ህ​ንስ ከጠ​ላ​ሃ​ቸው አንተ በእ​ጅህ ብት​ቀ​ጣ​ቸው ይሻ​ላል።”
31ይኽ​ንም ቃል ከተ​ና​ገ​ርሁ በኋላ ባለ​ፈ​ችው በዚ​ያች ሌሊት አስ​ቀ​ድሞ ወደ እኔ የመ​ጣው መል​አክ ወደ እኔ ተላከ። 32እን​ዲ​ህም አለኝ፥ “ስማኝ ልን​ገ​ርህ፤ አድ​ም​ጠኝ ብዙም እነ​ግ​ር​ሃ​ለሁ።” 33እኔም አል​ሁት፥ “አቤቱ ተና​ገር።” እር​ሱም አለኝ፥ “ይህ ለእ​ስ​ራ​ኤል እጅግ ድንቅ ነውን? ወይስ ከፈ​ጣ​ሪው ይልቅ እስ​ራ​ኤ​ልን አንተ እጅግ ትወ​ድ​ደ​ዋ​ለ​ህን?” 34እኔም አል​ሁት፥ “አቤቱ፥ አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን ስለ አሳ​ሰ​በኝ ተና​ገ​ርሁ፤ አቤቱ፥ ሁል​ጊ​ዜም የል​ዑ​ልን መን​ገድ አገኝ ዘንድ፥ የፍ​ር​ዱ​ንም ፍለጋ አውቅ ዘንድ ስመ​ራ​መር ኵላ​ሊ​ቴን አስ​ጨ​ነ​ቀኝ።” 35እር​ሱም አለኝ፥ “አት​ች​ልም።” እኔም አል​ሁት፥ “አቤቱ፥ ስለ ምን​ድን ነው? ስለ ምንስ ተወ​ለ​ድሁ? የያ​ዕ​ቆ​ብን መከራ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ወገ​ኖች ድካ​ማ​ቸ​ውን እን​ዳ​ላይ የእ​ናቴ ማኅ​ፀን ስለ​ምን መቃ​ብር አል​ሆ​ነ​ኝም?” 36እን​ዲ​ህም አለኝ፥ “ገና ያል​መጡ ቀኖ​ችን ቍጠር፥#“የተ​በ​ተ​ኑ​ትን የዝ​ናም ነጠ​ብ​ጣ​ቦች ሰብ​ስ​ብ​ልኝ” የሚል ዘርዕ ይገ​ኛል። የተ​በ​ተ​ኑ​ት​ንም አበ​ባ​ዎች ሰብ​ስ​ብ​ልኝ፤ የደ​ረ​ቀ​ው​ንም ሣር አለ​ም​ል​ም​ልኝ። 37የተ​ዘ​ጉ​ት​ንም ቤቶች ክፈ​ት​ልኝ፤ በው​ስ​ጣ​ቸ​ውም የተ​ዘጉ ነፋ​ሳ​ትን አም​ጣ​ልኝ፤ ፈጽሞ ያላ​የ​ኋ​ቸ​ው​ንም ፊታ​ቸ​ውን አሳ​የኝ፤ ቃላ​ቸ​ው​ንም አሰ​ማኝ፤ የዚ​ያን ጊዜም በሚ​ገባ ያገ​ኛ​ቸ​ውን መከራ እነ​ግ​ር​ሃ​ለሁ።”
38እኔም መልሼ አል​ሁት፥ “አቤቱ ጌታዬ፥ አነ​ዋ​ወሩ ከሰው የተ​ለየ ካል​ሆነ በቀር ይህን ማወቅ የሚ​ችል ማን​ነው? 39እኔ ዐላ​ዋ​ቂና የተ​ዋ​ረ​ድሁ ነኝ፤ ይህ​ንም የም​ት​ጠ​ይ​ቀ​ኝን ነገር እን​ዴት ልነ​ግ​ርህ እች​ላ​ለሁ?” 40እር​ሱም እን​ዲህ አለኝ፥ “እኔ ከም​ነ​ግ​ርህ ከእ​ኒህ አን​ዱን መና​ገር እን​ደ​ማ​ት​ችል እን​ደ​ዚሁ ፍር​ዴ​ንና ስለ ወገ​ኖች የም​ታ​ገ​ሠ​ውን የፍ​ቅ​ሬን መጨ​ረሻ ማግ​ኘት አት​ች​ልም።” 41እን​ዲ​ህም አል​ሁት፥ “አቤቱ፥ እነሆ፥ አንተ ስለ እነ​ርሱ ታገ​ሥህ፤ ከእኛ አስ​ቀ​ድሞ የነ​በሩ እን​ግ​ዲህ ምን ያደ​ር​ጋሉ? እኛና ከእኛ በኋላ የሚ​ነ​ሡ​ትስ?” 42እር​ሱም አለኝ፥ “ወደ ኋላ ያሉት እን​ዳ​ይ​ዘ​ገዩ፥ የቀ​ደ​ሙ​ትም እን​ዳ​ይ​ፈ​ጥኑ ፍር​ዴን እንደ ቀለ​በት አደ​ረ​ግ​ኋት።” 43እኔም አል​ሁት፥ “ፍር​ድ​ህን ፈጥ​ነህ ታሳይ ዘንድ የቀ​ደ​ሙ​ት​ንና ወደ ኋላ ያሉ​ትን አሁ​ንም ያሉ​ትን፥ ባንድ ጊዜ አንድ አድ​ር​ገህ መፍ​ጠር አት​ች​ልም ነበ​ርን?” ። 44እን​ዲ​ህም አለኝ፥ “ሥራ ከሠ​ሪው ፈጽሞ የሚ​ቸ​ኩል አይ​ደ​ለም፤ ዓለ​ምም በው​ስጧ የተ​ፈ​ጠ​ሩ​ትን ባል​ቻ​ለ​ቻ​ቸ​ውም ነበር።” 45እን​ዲ​ህም አል​ሁት፥ “አቤቱ የፈ​ጠ​ር​ሃ​ቸ​ውን በአ​ንድ ጊዜ በአ​ን​ድ​ነት እን​ደ​ም​ታ​ስ​ነ​ሣ​ቸው ለእኔ ለባ​ሪ​ያህ እን​ዴት ነገ​ር​ኸኝ? የፈ​ጠ​ር​ሃ​ቸ​ው​ንም በአ​ንድ ጊዜ ፈጥ​ነህ የም​ታ​ስ​ነ​ሣ​ቸው ከሆነ ዓለም ይጨ​ነ​ቃል፤#በአ​ን​ዳ​ንድ ዘርዕ “ይህ እን​ዴት ሊሆን ይች​ላል?” የሚል ይገ​ኛል። ይህም ባይ​ሆን ዛሬ ካሉት ጋራ አንድ ጊዜ ሊሸ​ከ​ማ​ቸው በቻለ ነበር።” 46እር​ሱም እን​ዲህ አለኝ፥ “እስኪ የሴት ማኅ​ፀ​ንን እሺ አሰ​ኛት፤ ዐሥር ልጆ​ች​ንም ስት​ወ​ልጂ ለምን በየ​ዓ​መቱ ትወ​ል​ጃ​ለሽ? በላት። እን​ግ​ዲህ ዐሥ​ሩን በአ​ንድ ጊዜ ትሰጥ እንደ ሆነ ጠይ​ቃት። 47በየ​ዓ​መቱ ካል​ሆነ በቀር በአ​ንድ ጊዜ የማ​ት​ችል አይ​ደ​ለ​ምን? 48ሕፃን ሴት መው​ለድ እን​ደ​ማ​ት​ችል፥ ያረ​ጀ​ችም እን​ደ​ማ​ት​ችል፥ እን​ዲሁ እኔም ለፈ​ጠ​ር​ሁት ዓለም በየ​ጊ​ዜው ሥር​ዐት ሠራ​ሁ​ለት።”#አን​ዳ​ንድ ዘሮች “በም​ድር ላይ ማኅ​ፀን በየ​ዓ​መቱ ካል​ሆነ በቀር በአ​ንድ ጊዜ ብዙ ልጆ​ችን እን​ደ​ማ​ት​ወ​ልድ ሥር​ዐት ሠር​ቻ​ለሁ” የሚል ይጨ​ም​ራል።
49እኔም ጠየ​ቅ​ሁት፤ እን​ዲ​ህም አል​ሁት፥ “በፊ​ትህ እና​ገር ዘንድ መን​ገድ ሰጥ​ተ​ኸ​ኛ​ልና እነሆ፥ በእ​ው​ነት አንተ አል​ኸኝ፤ ወጣት የነ​በ​ረች እና​ታ​ችሁ ፈጽማ አረ​ጀች፤ ኀይ​ላ​ች​ንስ እንደ ቀደ​ሙን ሰዎች ኀይል ለምን አል​ሆ​ነ​ል​ንም?” 50እር​ሱም መለ​ሰ​ልኝ፤ እን​ዲ​ህም አለኝ፥ “ልጅ የወ​ለ​ደች ሴትን ጠይ​ቃት፤ ትነ​ግ​ር​ሃ​ለ​ችም። 51በጥ​ን​ካሬ ያን​ሳሉ እንጂ ዛሬ የወ​ለ​ድ​ሻ​ቸው ቀድሞ እንደ ወለ​ድ​ሻ​ቸው ለምን አል​ሆ​ኑም? በላት። 52እር​ሷም እን​ዲህ ትል​ሃ​ለች፥ “በወ​ጣ​ት​ነት የተ​ወ​ለደ ልጅ ልዩ ኀያል ነው፤ በእ​ር​ጅና የተ​ወ​ለ​ደ​ውም ልዩ ደካማ ነው። 53ነገር ግን ከቀ​ደ​ሙት ሰዎች እና​ንተ በኀ​ይል እን​ደ​ም​ታ​ንሱ አንተ ራስህ ታው​ቀ​ዋ​ለህ። 54ከእ​ና​ን​ተም በኋላ የሚ​ወ​ለዱ ከእ​ና​ንተ ያን​ሣሉ፤ የተ​ፈ​ጠ​ረ​ውና ያለ​ውም የሕ​ፃ​ን​ነቱ ኀይል ዘመን ካለፈ እን​ዲሁ ነው።” 55እኔም አል​ሁት፥ “አቤቱ ጌታዬ እሺ በለኝ፤ በዐ​ይ​ኖ​ችህ ፊት ባለ​ሟ​ል​ነ​ትን ካገ​ኘሁ ለባ​ሪ​ያህ ንገ​ረው፤ ዓለ​ም​ህን በማን ትጐ​በ​ኛ​ለህ?”

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ