የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ዜና መዋ​ዕል ቀዳ​ማዊ 4

4
የይ​ሁዳ ትው​ልድ
1የይ​ሁዳ ልጆች ፋሬስ፥ ኤስ​ሮም ከርሚ፥ ሆርና ሱባል ናቸው። 2የሱ​ባ​ልም ልጅ ራያ ኢኤ​ትን ወለደ፤ ኢኤ​ትም አሑ​ማ​ይ​ንና ላሃ​ድን ወለደ። እነ​ዚህ የሰ​ራ​አ​ው​ያን ትው​ል​ዶች ናቸው። 3እነ​ዚ​ህም የኤ​ጣም ልጆች#ዕብ. “የኤ​ጣም አባት ልጆች” ይላል። ናቸው፤ ኢይ​ዝ​ራ​ኤል፥ ይሰማ፥ ኤጋ​ቢስ፥ እኅ​ታ​ቸ​ውም ኤሴ​ል​ፎን። 4የጌ​ዶ​ርም አባት ፋኑ​ኤል፥ የአ​ሶን አባት አዜር፤ እነ​ዚህ የቤተ ልሔም አባት የኤ​ፍ​ራታ የበ​ኵሩ የሆር ልጆች ናቸው። 5ለቴ​ቁ​ሄም አባት ለአ​ስ​ሑር ሔላና ነዓራ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ኦዳና ቶዳ” ይላል። የተ​ባሉ ሁለት ሚስ​ቶች ነበ​ሩት። 6ነዓ​ራም አሑ​ዛ​ምን፥ ኦፌ​ርን፥ ቴማ​ን​ንና አስ​ት​ራን ወለ​ደ​ች​ለት። እነ​ዚህ የነ​ዓራ ልጆች ናቸው። 7የሔ​ላም ልጆች ሴሬት፥ ይጽ​ሐ​ርና ኢት​ናን ናቸው። 8ቆስ፥ ኢኖ​ብን፥ ሲባ​ባን፥ የሃ​ሩ​ም​ንም ልጅ የሬ​ካ​ብን ወን​ድም ወገ​ኖች ወለደ። 9ያግ​ቤ​ጽም ከወ​ን​ድ​ሞቹ ይልቅ የተ​ከ​በረ ነበረ፤ እና​ቱም፦ በጣር ወል​ጄ​ዋ​ለ​ሁና ብላ ስሙን፦ ያግ​ቤጽ ብላ ጠራ​ችው። 10ያግ​ቤ​ጽም፥ “እባ​ክህ፥ መባ​ረ​ክን ባር​ከኝ፥ ሀገ​ሬ​ንም አስ​ፋው፤ እጅ​ህም ከእኔ ጋር ትሁን፤ እን​ዳ​ያ​ሳ​ዝ​ነ​ኝም ምል​ክት አድ​ር​ግ​ልኝ” ብሎ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አም​ላክ ጠራ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የለ​መ​ነ​ውን ሰጠው።
11የሱ​ሃም ወን​ድም#ግሪክ ሰባ. ሊ. “አባት” ይላል። ካሌብ የኤ​ስ​ቶ​ንን አባት ማኪ​ርን ወለደ። 12ኤስ​ቶ​ንም ቤቶ​ራ​ፋ​ንና ፋሲ​ሓን፥ የቄ​ኔ​ዛ​ዊው የኤ​ሴ​ሎ​ምን ወን​ድም የነ​ዓስ ከተማ አባት ታሒ​ናን ወለደ፤ እነ​ዚህ የራፋ ሰዎች ናቸው። 13የቄ​ኔ​ዝም ልጆች ጎቶ​ን​ያ​ልና ሠራ​ኢያ ነበሩ። የጎ​ቶ​ን​ያ​ልም ልጅ አታት ነበረ። 14መና​ቲም ጎፍ​ራን ወለደ። ሠራ​ኢ​ያም የጌ​ራ​ሲ​ምን አባት ኢዮ​አ​ብን ወለደ፤ እነ​ር​ሱም ጠራ​ቢ​ዎች ነበሩ። 15የዮ​ፎ​ኒም ልጅ የካ​ሌብ ልጆች ዔሩ፥ ኤላ፥ ነዓም ነበሩ። የኤ​ላም ልጅ ቄኔዝ ነበረ። 16የኢ​ያ​ል​ኤል ልጆች ዜፍ፥ ዚፋ፥ ቲርያ፥ አሣ​ር​ኤል ነበሩ። 17የኤ​ዜ​ራ​ስም ልጆች፤ ኢያ​ቴር፥ ሞራድ፥ ጋፌር፥ ኢያ​ሎን ነበሩ፤ ኢያ​ቴ​ርም ማሮ​ንን፥ ሰማ​ዒን፥ የኢ​ስ​ቲ​ሞ​ንን አባት ይስ​ባ​ኤ​ልን ወለደ። 18ሚስቱ አይ​ሂ​ዳም የጌ​ዶ​ርን አባት ያሬ​ድን፥ የሦ​ኮ​ንም አባት ሔቤ​ርን፥ የዛ​ኖ​ዋ​ንም አባት ይቁ​ቲ​ኤ​ልን ወለ​ደች። እነ​ዚህ ሞሬድ ያገ​ባት የፈ​ር​ዖን ልጅ የቢ​ትያ ልጆች ናቸው። 19የሆ​ድያ ሚስት የነ​ሐም እኅት ልጆች የገ​ር​ሜው የቅ​ዔላ አባ​ትና ማዕ​ካ​ታ​ዊው ኤሲ​ት​ሞዓ ነበሩ። 20የሴ​ሞ​ንም ልጆች አም​ኖን፥ የአ​ናን ልጆች ሬኖ​ንና ቲሎን ነበሩ፤ የይ​ስ​ቴም ልጆች ዘካ​ትና የዘ​ካት ልጆች ነበሩ። 21የይ​ሁ​ዳም ልጅ የሴ​ሎም ልጆች የሌካ አባት ዔር፥ የመ​ሪሳ አባት ለዓዳ፥ ከአ​ስ​ቤዓ ቤት የሚ​ሆኑ ጥሩ በፍታ የሚ​ሠሩ#“ጥሩ በፍታ የሚ​ሠሩ” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ወገ​ኖች፥ 22ኢዮ​አ​ቄም፥ የካ​ዚባ ሰዎች፥ ኢዮ​አስ፥ በሞ​ዓብ አድሮ ስማ​ቸ​ውን፥ አብ​ዶ​ራ​ንና ተቂ​ኤም ብሎ የመ​ለሰ ሣራፍ ነበሩ። 23እነ​ዚህ በነ​ጣ​ዔ​ምና በጋ​ዲራ ከን​ጉሡ ጋር የሚ​ቀ​መጡ ሸክላ ሠራ​ተ​ኞች ነበሩ። እነ​ር​ሱም በመ​ን​ግ​ሥቱ ጸን​ተው በዚያ ይኖሩ ነበር።
24የስ​ም​ዖ​ንም ልጆች፤ ነሙ​ኤል፥ ያሚን፥ ያሪብ፥ ዛራ፥ ሳኡል፤ 25ልጁ ሳሌም፥ ልጁ መብ​ሳም፥ ልጁ ማስ​ማዕ። 26የማ​ስ​ማ​ዕም ልጆች፤ ልጁ ሃሙ​ኤል፥ ልጁ ሳባድ፥#“ሳባድ” የሚ​ለው በዕብ. የለም። ልጁ ዝኩር፥ ልጁ ሰሜኢ። 27ለሰ​ሜ​ኢም ዐሥራ ስድ​ስት ወን​ዶ​ችና ስድ​ስት#“ሶስት” የሚል ዘርም ይገ​ኛል። ሴቶች ልጆች ነበ​ሩት፤ ለወ​ን​ድ​ሞቹ ግን ብዙ ልጆች አል​ነ​በ​ሩ​አ​ቸ​ውም፥ ወገ​ና​ቸ​ውም ሁሉ እንደ ይሁዳ ልጆች አል​ተ​ባ​ዙም። 28በቤ​ር​ሳ​ቤ​ህም፥ በሰ​ም​ዓም፥ በሞ​ላዳ፥ በሐ​ጸ​ር​ሱ​ዓል፥ 29በቤ​ልሃ፥ በዔ​ጼም፥ በቶ​ላድ፤ 30በቤ​ቱ​ኤል፥ በሔ​ርማ፥ በሤ​ቄ​ላቅ፤ 31በቤ​ት​ማ​ር​ካ​ቦት፥ በሐ​ጸ​ር​ሱ​ሲም፥ በቤ​ት​ቢሪ፥ በሰ​ዓ​ራ​ይም ይቀ​መጡ ነበር። እስከ ዳዊ​ትም መን​ግ​ሥት ድረስ ከተ​ሞ​ቻ​ቸው እነ​ዚህ ነበሩ። 32መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸ​ውም ኤጣም፥ ዓይን፥ ሬሞን፥ ቶኪን፥ ዓሻን፥ አም​ስቱ ከተ​ሞች፤ 33መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸ​ውም ሁሉ እስከ በኣል ድረስ በእ​ነ​ዚህ ከተ​ሞች ዙሪያ ነበሩ። መቀ​መ​ጫ​ቸ​ውና ድር​ሻ​ቸ​ውም ይህ ነበረ። 34መሶ​ባብ፥ የም​ሌክ፥ የአ​ሚ​ስ​ያስ ልጅ ኢዮ​ስያ፤ 35ኢዮ​ኤል፥ የዮ​ስ​ብያ ልጅ፥ የሠ​ራያ ልጅ የአ​ሣ​ኤል ልጅ ኢዩ፤ 36ኤል​ዮ​ዔ​ናይ፥ ያዕ​ቀባ፥ የሰ​ሐያ፥ ዓሣያ፥ ዓዲ​ዔል፥ ይስ​ማ​ኤል፥ በና​ያስ፤ 37የሳ​ፋኤ ልጅ ዙዛ፥ የአ​ሎን ልጅ የይ​ዳያ ልጅ የሰ​ማሪ ልጅ የሰ​ማያ ልጅ፤ 38እነ​ዚህ በስ​ማ​ቸው የተ​ጠሩ በወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው ላይ አለ​ቆች ነበሩ፤ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ቤቶች በዝ​ተው ነበር። 39ለመ​ን​ጎ​ቻ​ቸው መሰ​ማ​ርያ ይሹ ዘንድ ወደ ጌራራ እስ​ኪ​ደ​ርሱ ድረስ ወደ ጋይ ምሥ​ራቅ ሄዱ። 40ብዙና እጅግ ያማረ መሰ​ማ​ር​ያም አገኙ፤ ምድ​ሪ​ቱም በፊ​ታ​ቸው ሰፊና ጸጥ​ተኛ ሰላም ያላ​ትም ነበ​ረች፤ በቀ​ድ​ሞም ጊዜ በዚያ ተቀ​ም​ጠው የነ​በሩ ከካም ወገን ነበሩ። 41በስ​ማ​ቸው የተ​ጻፉ እነ​ዚ​ህም በይ​ሁዳ ንጉሥ በሕ​ዝ​ቅ​ያስ ዘመን መጥ​ተው ድን​ኳ​ኖ​ቻ​ቸ​ው​ንና በዚያ የተ​ገ​ኙ​ትን ምዑ​ና​ው​ያ​ንን መቱ፥ እስከ ዛሬም ድረስ ፈጽ​መው አጠ​ፉ​አ​ቸው፤ በዚ​ያም ለመ​ን​ጎ​ቻ​ቸው መሰ​ማ​ሪያ ነበ​ርና በስ​ፍ​ራ​ቸው ተቀ​መጡ። 42ከስ​ም​ዖ​ንም ልጆች አም​ስት መቶ ሰዎች ወደ ሴይር ተራራ ሄዱ፤ አለ​ቆ​ቻ​ቸ​ውም የይ​ሰዔ ልጆች ፥ ፈላ​ጥያ፥ ነዓ​ርያ፥ ረፋያ፥ ዑዝ​ኤል ነበሩ። 43ያመ​ለ​ጡ​ት​ንም የአ​ማ​ሌ​ቃ​ው​ያ​ንን ቅሬታ መቱ፥ በዚ​ያም እስከ ዛሬ ድረስ ተቀ​ም​ጠ​ዋል።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ