የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ዜና መዋ​ዕል ቀዳ​ማዊ 5

5
የሮ​ቤል ትው​ልድ
1የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም በኵር የሮ​ቤል ልጆች እነ​ዚህ ናቸው። እርሱ የበ​ኵር ልጅ ነበረ፤ ነገር ግን ወደ አባቱ ምን​ጣፍ ስለ ወጣ አባቱ እስ​ራ​ኤል በረ​ከ​ቱን ለልጁ ለዮ​ሴፍ ሰጠ፤ ብኵ​ር​ናም አል​ተ​ቈ​ጠ​ረ​ለ​ትም። 2ይሁ​ዳም በወ​ን​ድ​ሞቹ መካ​ከል በረታ፥ አለ​ቃም ከእ​ርሱ ሆነ፤ በረ​ከት ግን ለዮ​ሴፍ ነበረ። 3የእ​ስ​ራ​ኤል በኵር የሮ​ቤል ልጆች፤ ሄኖኅ፥ ፍሎስ፥ አስ​ሮን፥ ከርሚ ነበሩ። 4የኢ​ዩ​ኤል ልጆች፤ ልጁ ሰማያ፥ ልጁ ጎግ፥ ልጁ ሰሜኢ፤ 5ልጁ ሚካ፥ ልጁ ሬካ፥ ልጁ ቤኤል፥ 6የአ​ሦር ንጉሥ ቴል​ጌ​ል​ቴ​ል​ፌ​ል​ሶር የማ​ረ​ከው ልጁ ብኤራ፤ እርሱ የሮ​ቤል ነገድ አለቃ ነበረ። 7ወን​ድ​ሞቹ በየ​ወ​ገ​ና​ቸው የት​ው​ል​ዶ​ቻ​ቸው መዝ​ገብ በተ​ቈ​ጠረ ጊዜ፥ አለ​ቆ​ቻ​ቸው ኢዩ​ኤ​ልና ዘካ​ር​ያስ ነበሩ። 8እስከ ናባ​ውና እስከ በኣ​ል​ሜ​ዎን ድረስ በአ​ሮ​ዔር የተ​ቀ​መ​ጠው የኢ​ዩ​ኤል ልጅ የሰ​ማዕ ልጅ የዖ​ዛዝ ልጅ ቤላ፤ 9በገ​ለ​ዓድ ምድር እን​ስ​ሶ​ቻ​ቸው በዝ​ተው ነበ​ርና በም​ሥ​ራቅ በኩል ከኤ​ፍ​ራ​ጥስ ወንዝ ጀምሮ እስከ ምድረ በዳው መግ​ቢያ ድረስ ተቀ​መጠ። 10በሳ​ኦ​ልም ዘመን ከስ​ደ​ተ​ኞች ጋር ተዋጉ፥ እነ​ር​ሱም በእ​ጃ​ቸው ተመ​ት​ተው ወደቁ፤ በገ​ለ​ዓድ ምሥ​ራቅ በኩል ባለው ሀገር ሁሉ በድ​ን​ኳ​ኖ​ቻ​ቸው ተቀ​መጡ።
የጋድ ትው​ልድ
11የጋ​ድም ልጆች በባ​ሳን ምድር እስከ ሰልካ ድረስ በአ​ፋ​ዛ​ዣ​ቸው ተቀ​መጡ። 12በኵሩ ኢዩ​ኤል፥ ሁለ​ተ​ኛው ሳፋም፥ ጸሓ​ፊው ያና​ይን፥ ሳፋ​ጥም በባ​ሳን ተቀ​መጡ። 13የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች ወን​ድ​ሞች ሚካ​ኤል፥ ሜሱ​ላም፥ ሳባ፥ ዮራይ፥ ያካን፥ ዙኢ፥ ኦቤድ እነ​ዚህ ሰባት ነበሩ። 14እነ​ዚ​ህም የቡዝ ልጅ የዮ​ዳይ ልጅ የኢ​ዮ​ሳይ ልጅ የሚ​ካ​ኤል ልጅ የገ​ለ​ዓድ ልጅ የኤ​ዳይ ልጅ የዑሪ ልጅ የአ​ቢ​ካ​ኤል ልጆች ነበሩ። 15የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ቤቶች አለቃ የጎኔ ልጅ የአ​ብ​ዲ​ኤል ልጅ ወን​ድም ነበር። 16በገ​ለ​ዓ​ድም ምድር በባ​ሳን በመ​ን​ደ​ሮ​ቹም በሳ​ሮ​ንም መሰ​ማ​ር​ያ​ዎች ሁሉ እስከ ዳር​ቻ​ቸው ድረስ ተቀ​ም​ጠው ነበር። 17እነ​ዚህ ሁሉ በት​ው​ል​ዶ​ቻ​ቸው በይ​ሁዳ ንጉሥ በኢ​ዮ​አ​ታም ዘመ​ንና በእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ዘመን ተቈ​ጠሩ።
የጋ​ድና የም​ናሴ ነገድ እኩ​ሌታ ትው​ልድ
18የሮ​ቤ​ልና የጋድ ልጆች የም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ፥ ጽኑ​ዓን ጋሻና ሰይፍ የሚ​ይዙ፥ ቀስ​ተ​ኞ​ችም፥ ሰልፍ የሚ​ያ​ውቁ ሰል​ፈ​ኞ​ችም፥ አርባ አራት ሺህ ሰባት መቶ ስድሳ ነበሩ። 19ከአ​ጋ​ራ​ው​ያ​ንና ከኢ​ጣ​ር​ዮን ከና​ፋ​ስ​ዮ​ንና ከና​ዳ​ብ​ዮን ጋር ተዋጉ። 20በሚ​ዋ​ጉ​በ​ትም ጊዜ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኸ​ዋ​ልና በእ​ር​ሱም ታም​ነ​ዋ​ልና አዳ​ና​ቸው፤ በላ​ያ​ቸ​ውም በረ​ቱ​ባ​ቸው፥ አጋ​ራ​ው​ያ​ንና ከእ​ነ​ርሱ ጋር የነ​በ​ሩ​ትም ሁሉ በእ​ጃ​ቸው ተሰጡ። 21ከከ​ብ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም አምሳ ሺህ ግመ​ሎች፥ ሁለት መቶ አምሳ ሺህም በጎች፥ ሁለት ሺህም አህ​ዮች፥ ከሰ​ዎ​ችም መቶ ሺህ ማረኩ። 22ሰልፉ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ነበ​ረና ብዙ ሰዎች ተገ​ድ​ለው ወደቁ፤ እስከ ምር​ኮም ዘመን ድረስ በስ​ፍ​ራ​ቸው ተቀ​መጡ።
23የም​ና​ሴም የነ​ገድ እኩ​ሌታ ልጆች፤ ከባ​ሳን ጀምሮ እስከ በኣ​ል​አ​ር​ሞ​ንና እስከ ሳኔር እስከ አር​ሞ​ን​ኤም ተራራ እስከ ሊባ​ኖስ ድረስ ተቀ​መጡ፤ እነ​ር​ሱም በዙ። 24የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ቤቶች አለ​ቆች እነ​ዚህ ነበሩ፤ ዔፌር፥ ይስዔ፥ ኤሊ​ኤል፥ ዓዝ​ር​ኤል፥ ኢይ​ር​ምያ፥ ሆዳ​ይዋ፥ ኢየ​ድ​ኤል፤ እነ​ርሱ ጽኑ​ዓን ኀያ​ላን የታ​ወቁ ሰዎች የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ቤቶች አለ​ቆች ነበሩ።
25የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም አም​ላክ በደሉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከፊ​ታ​ቸው ባጠ​ፋ​ቸው በም​ድሩ አሕ​ዛብ አማ​ል​ክት አመ​ነ​ዘሩ። 26የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ የአ​ሦ​ርን ንጉሥ የፋ​ሎ​ክን#ዕብ. “ፎሓን” ይላል። መን​ፈስ፥ የአ​ሦ​ር​ንም ንጉሥ የቴ​ል​ጌ​ል​ቴ​ል​ፌ​ል​ሶ​ርን መን​ፈስ አስ​ነሣ፤ የሮ​ቤ​ል​ንና የጋ​ድን ልጆች የም​ና​ሴ​ንም ነገድ እኩ​ሌታ አፈ​ለሰ፥ እስከ ዛሬም ወዳ​ሉ​በት ወደ አላ​ሔና ወደ ኦቦር፥ ወደ ሃራ​ንና ወደ ጎዛን ወንዝ አመ​ጣ​ቸው።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ