መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ 6
6
የሌዊ ትውልድ
1የሌዊ ልጆች፤ ጌድሶን፥ ቀዓት ሜራሪ። 2የቀዓትም ልጆች፤ እንበረም፥ ይስዓር፥ ኬብሮን፥ ዑዝኤል። 3የእንበረምም ልጆች፤ አሮን፥ ሙሴ፥ ማርያም። የአሮንም ልጆች፤ ናዳብ፥ አብዩድ፥ አልዓዛር፥ ኢታምር። 4አልዓዛር ፊንሐስን ወለደ፤ ፊንሐስም አቢሱን ወለደ፤ 5አቢሱም ቡቂን ወለደ፤ ቡቂም ኦዚን ወለደ፤ 6ኦዚም ዘራእያን ወለደ፤ ዘራእያም መራዮትን ወለደ፤ 7መራዮትም አማርያን ወለደ፤ አማርያም አኪጦብን ወለደ፤ 8አኪጦብም ሳዶቅን ወለደ፤ ሳዶቅም አኪማኦስን ወለደ፤ 9አኪማኦስም ዓዛርያን ወለደ፤ አዛርያም ዮሐናንን ወለደ፤ 10ዮሐናንም ዓዛርያስን ወለደ፤ እርሱም ሰሎሞን በኢየሩሳሌም በሠራው ቤት ካህን ነበረ፤ 11ዓዛርያስም አማርያን ወለደ፤ አማርያም አኪጦብን ወለደ፤ 12አኪጦብም ሳዶቅን ወለደ፤ ሳዶቅም ሳሎምን ወለደ፤ 13ሳሎምም ኬልቅያስን ወለደ፤ ኬልቅያስም ዓዛርያስን ወለደ፤ 14ዓዛርያስም ሠራያን ወለደ፤ ሠራያም ኢዮሴዴቅን ወለደ፤ 15ኢዮሴዴቅም፥ ይሁዳና ኢየሩሳሌም በናቡከደነፆር እጅ በተማረኩ ጊዜ ተማርኮ ሄደ።
16የሌዊ ልጆች፤ ጌድሶን፥ ቀዓት፥ ሜራሪ። 17የጌድሶንም ልጆች ስም ይህ ነው፤ ሎቤኒ፥ ሰሜኢ። 18የቀዓትም ልጆች፤ እንበረም፥ ይስዓር፥ ኬብሮን፥ ዑዝኤል ነበሩ። 19የሜራሪም ልጆች፤ ሞሐሊ፥ ሙሲ፥ የሌዋውያን ወገኖች በየአባቶቻቸው ቤቶች እነዚህ ናቸው። 20ከጌድሶን፤ ልጁ ሎቤኒ፥ ልጁ ኢኤት፥ ልጁ ዛማት፤ 21ልጁ ዮአክ፥ ልጁ አዶ፥ ልጁ ዛራ፥ ልጁ ያትራይ። 22የቀዓት ልጆች፤ ልጁ አሚናዳብ፥ ልጁ ቆሬ፥ ልጁ አሴር፤ 23ልጁ ሕልቃና፥ ልጁ አቢሳፍ፥ ልጁ አሴር፤ 24ልጁ ተአት፥ ልጁ ኡርኤል፥ ልጁ ዖዝያ፥ ልጁ ሳውል። 25የሕልቃናም ልጆች፤ አማሤ፥ አኪሞት። 26ልጁ ሕልቃና፤ ልጁ ሱፌ፤ ልጁ ናሔት፤ 27ልጁ ኤልያብ፤ ልጁ ኢያሬምያል፤ ልጁ ሕልቃና፤ ልጁ ሳሙኤል። 28የሳሙኤልም ልጆች፤ በኵሩ ኢዮኤል፥#አንዳንድ የዕብ. እና የግሪክ ሰባ. ሊ. ዘርዕ “ሰኒ” ይላል። ሁለተኛውም አብያ። 29የሜራሪ ልጆች፤ ሞሓሊ፥ ልጁ ሎቤኒ፥ ልጁ ሰሜኢ፥ ልጁ ዖዛ፥ 30ልጁ ሳምዓ፥ ልጁ ሐግያ፥ ልጁ ዓሣያ።
31ዳዊትም ታቦቷ በምታርፍበት ጊዜ በእግዚአብሔር ቤት ያቆማቸው የመዘምራን አለቆች እነዚህ ናቸው። 32ሰሎሞንም የእግዚአብሔርን ቤት በኢየሩሳሌም እስኪሠራ ድረስ በምስክሩ ድንኳን ማደሪያ ፊት በበገና እያዜሙ ያገለግሉ ነበር፤ በየተራቸውም ለአገልግሎታቸው ይቆሙ ነበር። 33አገልጋዮቹና ልጆቹ እነዚህ ነበሩ፤ ከቀዓት ልጆች ዘማሪው ኤማን ነበረ፤ እርሱም የኢዩኤል ልጅ፥ የሳሙኤል ልጅ፤ 34የሕልቃና ልጅ፥ የይሮዓም ልጅ፥ የኤላኤል ልጅ፥ የቶዋ ልጅ፤ 35የሱፍ ልጅ፥ የሕልቃና ልጅ፥ የመሐት ልጅ፥ የአማሤ ልጅ፤ 36የሕልቃና ልጅ፥ የኢዩኤል ልጅ፥ የዓዛርያስ ልጅ፥ የሶፎንያስ ልጅ፤ 37የታሐት ልጅ፥ የአሴር ልጅ፥ የአብያሳፍ ልጅ፥ የቆሬ ልጅ፥ 38የይሰአር ልጅ፥ የቀዓት ልጅ፥ የሌዊ ልጅ፥ የእስራኤል ልጅ ነው። 39በቀኙም የሚቆመው ወንድሙ አሳፍ ነበረ፤ አሳፍም የበራክያ ልጅ፥ የሳምዓ ልጅ፤ 40የሚካኤል ልጅ፤ የበዓሣያ ልጅ፥ የመልክያ ልጅ፤ 41የኤትኒ ልጅ፥ የዛራ ልጅ፥ የዓዳያ ልጅ፤ 42የኤታን ልጅ፥ የዛማ ልጅ፥ የሰሜኢ ልጅ፤ 43የኢያኤት ልጅ፥ የጌድሶን ልጅ፥ የሌዊ ልጅ ነው። 44በግራቸውም በኩል የሚቆሙ ወንድሞቻቸው የሜራሪ ልጆች ነበሩ፤ ኤታን የቄሳ ልጅ፥ የአብዲ ልጅ፥ የማሎክ ልጅ፤ 45የአሳቢ ልጅ፥ የአሜስያስ ልጅ፥ የኬልቅያስ ልጅ፤ 46የአማሴ ልጅ፥ የባኒ ልጅ፥ የሴሜር ልጅ፤ 47የሞአሊ ልጅ፥ የሙሲ ልጅ፥ የሜራሪ ልጅ፥ የሌዊ ልጅ። 48ወንድሞቻቸውም ሌዋውያን እንደ እየባቶቻቸው ቤቶች ለእግዚአብሔር ቤት ሥራ አገልግሎት ሁሉ ተሰጡ።
49አሮንና ልጆቹ ግን የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ እንዳዘዘው ሁሉ ለቅድስተ ቅዱሳን ሥራ ሁሉ ስለ እስራኤልም ያስተሰርይ ዘንድ ለሚቃጠለው መሥዋዕት በሚሆነው መሠዊያ ላይ ይሠዉ ነበር፥ በዕጣኑም መሠዊያ ላይ ያጥኑ ነበር። 50የአሮንም ልጆች ስሞች እነዚህ ናቸው፤ ልጁ አልዓዛር፥ ልጁ ፊንሐስ፥ ልጁ አቢሱ፤ 51ልጁ ቡቂ፥ ልጁ ኦዚ፥ ልጁ ዘራእያ፤ 52ልጁ መራዮት፥ ልጁ አማርያ፥ ልጁ አኪጦብ፥ 53ልጁ ሳዶቅ፥ ልጁ አኪማኦስ።
54ማደሪያዎቻቸውም በየሰፈራቸው በየዳርቻቸው እነዚህ ናቸው፤ ለአሮን ልጆች ለቀዓት ወገኖች አንደኛው ዕጣ ነበረ። 55ለእነርሱ በይሁዳ ሀገር ያለችውን ኬብሮንን፥ በእርስዋም ዙሪያ የነበረውን መሰማሪያ ሰጡ፤ 56የከተማዪቱን እርሻ ግን መንደሮችዋንም ለዮፎኒ ልጅ ለካሌብ ሰጡ። 57ለአሮንም ልጆች የመማፀኛውን ከተሞች፥ ኬብሮንን፥ ልብናንና መሰማርያዋን፥ ሴልናንና መሰማሪያዋን፤ ኤስትሞዓንና መሰማሪያዋን ሰጡ። 58የኢያቴርን ከተማና መሰማሪያዋን፥ ዳቤርንና መሰማሪያዋን፤ 59ዓሳንንና መሰማሪያዋን፥ ቤትሳሚስንና መሰማሪያዋን፤ 60ከብንያምም ነገድ ጌባንና መሰማርያዋን፥ ጋሌማትንና መሰማሪያዋን፥ ዓናቶትንና መሰማሪያዋን ሰጡ። ከተሞቻቸው ሁሉ በየወገናቸው ዐሥራ ሦስት ነበሩ።
61ለቀሩትም ለቀዓት ልጆች ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ዐሥር ከተሞች በዕጣ ተሰጡ። 62ለጌድሶንም ልጆች በየወገናቸው ከይሳኮር ነገድ፥ ከአሴርም ነገድ፥ ከንፍታሌምም ነገድ፥ በባሳንም ካለው ከምናሴ ነገድ፥ ዐሥራ ሦስት ከተሞች ተሰጡ። 63ለሜራሪም ልጆች በየወገናቸው ከሮቤል ነገድ፥ ከጋድም ነገድ፥ ከዛብሎንም ነገድ፥ ዐሥራ ሁለት ከተሞች በዕጣ ተሰጡ። 64የእስራኤልም ልጆች ለሌዋውያን ከተሞችን ከመሰማሪያዎቻቸው ጋር ሰጡ። 65ከይሁዳም ልጆች ነገድ፥ ከስምዖንም ልጆች ነገድ፥ ከብንያምም ልጆች ነገድ፥ እነዚህን በስማቸው የተጠሩትን ከተሞች በዕጣ ሰጡ።
66ከቀዓትም ልጆች ወገኖች ለአንዳንዶቹ ከኤፍሬም ነገድ ከተሞች ድርሻ ነበራቸው። 67በተራራማው በኤፍሬም ሀገር ያሉትን የመማፀኛውን ከተሞች ሴኬምንና መሰማሪያዋን፥ ደግሞም ጋዜርንና መሰማሪያዋን፤ 68ዮቅምዓምንና መሰማሪያዋን፥ ቤትሖሮንንና መሰማሪያዋን፤ 69ኤሎንንና መሰማሪያዋን፥ ጋትሪሞንንና መሰማሪያዋን ሰጡአቸው። 70ከምናሴም ነገድ እኩሌታ ዓኔርንና መሰማሪያዋን፥ ቤልዓምንና መሰማሪያዋን፥ ከቀዓት ልጆች ወገን ለቀሩት ሰጡ።
71ለጌድሶን ልጆች ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ወገን በባሳን ያለችው ጋውሎንና መሰማሪያዋ፥ አስታሮትና መሰማሪያዋ፤ 72ከይሳኮርም ነገድ ቃዴስና መሰማሪያዋ፥ ዳብራትና መሰማሪያዋ፤ 73ራሞትና መሰማሪያዋ፥ ዓኔምና መሰማሪያዋ፤ 74ከአሴርም ነገድ መዓሳልና መሰማሪያዋ፥ ዓብዶንና መሰማሪያዋ፤ 75ሐቆቅና መሰማሪያዋ፥ ረዓብና መሰማሪያዋ፤ 76ከንፍታሌምም ነገድ በገሊላ ያለችው ቃዴስና መሰማሪያዋ፥ ሐሞንና መሰማሪያዋ፥ ቄርያታይምና መሰማሪያዋ ተሰጡ።
77ለቀሩትም ለሜራሪ ልጆች ከዛብሎን ነገድ ሬሞንና መሰማሪያዋ፥ ታቦርና መሰማሪያዋ፤ 78ከሮቤልም ነገድ በኢያሪኮ አንጻር በዮርዳኖስ ማዶ በምሥራቅ በኩል በምድረ በዳ ያለችው ቦሶርና መሰማሪያዋ፥ ያሶንና መሰማሪያዋ፤ 79ቅዴሞትና መሰማሪያዋ፥ ሜፍዓትና መሰማሪያዋ፤ 80ከጋድም ነገድ በገለዓድ ያለችው ሬማትና መሰማሪያዋ፥ መሃናይምና መሰማሪያዋ፤ 81ሐሴቦንና መሰማሪያዋ፥ ኢያዜርና መሰማሪያዋ ተሰጡ።#ምዕ. 6 ከቍ. 6 እስከ 81 ያለው የግእዙ ዘርዕ ከኢያሱ ምዕ. 21 ከቍ. 21 እስከ 42 ካለው እያመጣ ስለሚያስገባ አንዳንድ ልዩነት ያሳያል።
Currently Selected:
መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ 6: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ