የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ዜና መዋ​ዕል ቀዳ​ማዊ 7

7
1የይ​ሳ​ኮ​ርም ልጆች፤ ቶላ፥ ፋዋ፥ ያሱብ፥ ሰም​ሮን፥ አራት ናቸው። 2የቶ​ላም ልጆች፤ ኦዚ፥ ረፋያ፥ ይሪ​ኤል፥ የሕ​ማይ፥ ይብ​ሣም፥ ሰሙ​ኤል፥ የአ​ባ​ታ​ቸው የቶላ ቤት አለ​ቆች፥ በት​ው​ል​ዳ​ቸው ጽኑ​ዓን ኀያ​ላን ሰዎች ነበሩ፤ በዳ​ዊት ዘመን ቍጥ​ራ​ቸው ሃያ ሁለት ሺህ ስድ​ስት መቶ ነበረ። 3የኦ​ዚም ልጆች ይዝ​ረ​ሕያ፤ የይ​ዝ​ረ​ሕ​ያም ልጆች ሚካ​ኤል፥ አብ​ድዩ፥ ኢዩ​ኤል፥ ይሴያ አም​ስት ናቸው፤ ሁሉም አለ​ቆች ነበሩ። 4ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር በየ​ት​ው​ል​ዳ​ቸው በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤት ለሰ​ልፍ የተ​ዘ​ጋጁ የሠ​ራ​ዊት ጭፍ​ሮች ነበሩ፤ ብዙም ሴቶ​ችና ልጆች ነበ​ሩ​አ​ቸ​ውና ሠላሳ ስድ​ስት ሺህ ነበሩ። 5ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም በይ​ሳ​ኮር ወገ​ኖች ሁሉ ጽኑ​ዓን ኀያ​ላን ሰዎች በት​ው​ል​ዳ​ቸው ሁሉ የተ​ቈ​ጠሩ ሰማ​ንያ ሰባት ሺህ ነበሩ።
6የብ​ን​ያም ልጆች ቤላ፥ ቤኬር፥ ይድ​ኤል ሦስት ነበሩ። 7የቤ​ላም ልጆች፥ ኤሲ​ቦን፥ ኦዚ፥ ዑዝ​ኤል፥ ኢያ​ሬ​ሙት፥ ዔሪ አም​ስት ነበሩ፤ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች አለ​ቆች፥ ጽኑ​ዓን ኀያ​ላን ሰዎች ነበሩ፤ ቍጥ​ራ​ቸ​ውም ሃያ ሁለት ሺህ ሠላሳ አራት ነበሩ። 8የቤ​ኬ​ርም ልጆች ዝሜራ፥ ኢዮ​አስ፥ አል​ዓ​ዛር፥ ኤል​ዮ​ኤ​ናይ፥ ዖምሪ፥ ኢያ​ሪ​ሙት፥ ዓብያ፥ ዓና​ቶት፤ ዓሌ​ሜት፤ እነ​ዚህ ሁሉ የቤ​ኬር ልጆች ነበሩ። 9በየ​ት​ው​ል​ዳ​ቸ​ውም መዝ​ገብ የተ​ቈ​ጠሩ፥ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች አለ​ቆች፥ ጽኑ​ዓን ኀያ​ላን ሰዎች ሃያ ሺህ ሁለት መቶ ነበሩ። 10የይ​ዴ​ኤ​ልም ልጅ ቢል​ሐን ነበረ፤ የቢ​ል​ሐ​ንም ልጆች የዑስ፥ ብን​ያም፥ ኤሁድ፥ ክን​ዓና፥ ዜታን፥ ተር​ሴስ፥ አኬ​ሳ​አር ነበሩ። 11እነ​ዚህ ሁሉ የይ​ዴ​ኤል ልጆች ነበሩ፤ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች አለ​ቆች፥ ጭፍራ እየ​ሆኑ ወደ ሰልፍ የሚ​ወጡ ጽኑ​ዓን ኀያ​ላን ሰዎች ዐሥራ ሰባት ሺህ ሁለት መቶ ነበሩ። 12ደግ​ሞም ሳፊን፥ ሑፊም የዔር ልጆች፥ ሑሲም የአ​ሔር ልጅ ነበረ።
13የን​ፍ​ታ​ሌ​ምም ልጆች፥ ያሕ​ጽ​ኤል፥ ጎኒ፥ ዬጽር፥ ሼሌም፥ እነ​ዚህ አራቱ የባላ ልጆች ነበሩ። 14የም​ናሴ ልጆች ሶሪ​ያ​ዪቱ ቁባቱ የወ​ለ​ደ​ች​ለት አስ​ር​ኤ​ልና የገ​ለ​ዓድ አባት ማኪር ናቸው። 15ማኪ​ርም ከሑ​ፊ​ምና ከሳ​ፊን ወገን ሚስት አገባ፤ የእ​ኅ​ት​የ​ዋም ስም መዓካ ነበረ፤ የሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ስም ሰለ​ጰ​ዓድ ነበረ፤ ለሰ​ለ​ጰ​ዓ​ድም ሴቶች ልጆች ነበ​ሩት። 16የማ​ኪ​ርም ሚስት መዓካ ልጅ ወለ​ደች፥ ስሙ​ንም ፋሬስ ብላ ጠራ​ችው፤ የወ​ን​ድ​ሙም ስም ሱሮስ ነበረ፤ ልጆ​ቹም ኡላ​ምና ራቄም ነበሩ። 17የኡ​ላ​ምም ልጅ ባዳን ነበረ፤ እነ​ዚህ የም​ናሴ ልጅ የማ​ኪር ልጅ የገ​ለ​ዓድ ልጆች ነበሩ። 18እኅቱ መለ​ኪት ኢሱ​ድን፥ አቢ​ዔ​ዜ​ርን፥ መሕ​ላን ወለ​ደች። 19የሰ​ሜ​ራም ልጆች አሒ​ያን፥ ሴኬም፥ ሌቅሔ፥ አኔ​ዓም ነበሩ።
20የኤ​ፍ​ሬም ልጆች፤ ሱቱላ፥ ልጁ ባሬድ፥ ልጁ ታሐት፥ ልጁ ኤል​ዓዳ፥ ልጁ ታክት፤ 21ልጁ ዛባድ፥ ልጁ ሹቱላ፥ ልጁ ኤድር፥ ልጁ ኤል​ዓድ ነበሩ፤ የሀ​ገ​ሩም ተወ​ላ​ጆች የጌት ሰዎች ከብ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ሊወ​ስዱ ወር​ደው ነበ​ርና ገደ​ሉ​አ​ቸው። 22አባ​ታ​ቸው ኤፍ​ሬ​ምም ብዙ ቀን አለ​ቀሰ፤ ወን​ድ​ሞ​ቹም ሊያ​ጽ​ና​ኑት መጡ። 23ወደ ሚስ​ቱም ገባ፥ አረ​ገ​ዘ​ችም፤ ወንድ ልጅም ወለ​ደች፤ በቤ​ቴም መከራ ሆኖ​አ​ልና ሲል ስሙን በሪዓ ብሎ ጠራው። 24የሴት ልጁም ስም ሲአራ ነበረ፤ በዚ​ያም በቀ​ሩት ታች​ኛ​ው​ንና ላይ​ኛ​ውን ቤት​ሖ​ሮ​ንን ሠራ#ዕብ. “ሴት ልጁም ታች​ኛ​ው​ንና ላይ​ኛ​ውን ቤት ሖሮ​ን​ንና ዑዜን ሼራን ሠራች” ይላል። የኡ​ዛ​ንም ልጁ ሠይራ ነበረ፤ 25ወን​ዶች ልጆ​ቹም ራፋኢ፥ ሳራፍ፥ ልጁ ቴላ፥ ልጁ ታሐን፤ 26ልጁ ለአ​ዳን፥ ልጁ ዓሜ​ሁድ፥ ልጁ ኤሌ​ሳማ፤ 27ልጁ ነዌ፥ ልጁ ኢያሱ።
28ግዛ​ታ​ቸ​ውና ማደ​ሪ​ያ​ቸው ቤቴ​ልና መን​ደ​ሮ​ችዋ፥ በም​ሥ​ራ​ቅም በኩል ነዓ​ራን፥ በም​ዕ​ራ​ብም በኩል ጌዝ​ርና መን​ደ​ሮ​ችዋ፥ ደግ​ሞም ሴኬ​ምና መን​ደ​ሮ​ችዋ፥ እስከ ጋዛና እስከ መን​ደ​ሮ​ችዋ ድረስ፤ 29በም​ና​ሴም ልጆች ዳርቻ ቤት​ሳ​ንና መን​ደ​ሮ​ችዋ፥ ታዕ​ና​ክና መን​ደ​ሮ​ችዋ፥ መጊ​ዶና መን​ደ​ሮ​ችዋ፥ ዶርና መን​ደ​ሮ​ችዋ፥ በላ​ድና መን​ደ​ሮ​ችዋ ነበሩ፤ በእ​ነ​ዚህ ያዕ​ቆብ የተ​ባለ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጅ የዮ​ሴፍ ልጆች ተቀ​መጡ።
30የአ​ሴር ልጆች፤ ኢያ​ምና፥ የሱዋ፥ የሱዊ፥ በሬዓ፥ እኅ​ታ​ቸ​ውም ሤራሕ ነበሩ። 31የበ​ሪ​ዓም ልጆች፤ ሔቤ​ርና፥ የቤ​ር​ዛ​ዊት አባት የነ​በ​ረው መል​ኪ​ኤል ናቸው። 32ሔቤ​ርም ያፍ​ሌ​ጥን፥ ሳሜ​ርን፥ ኮታ​ምን፥ እኅ​ታ​ቸ​ው​ንም ሶላን ወለደ። 33የያ​ፍ​ሌ​ጥም ልጆች፤ ፋሴክ፥ ቢም​ሃል፥ ዓሴት ነበሩ፤ እነ​ዚህ የያ​ፍ​ሌጥ ልጆች ነበሩ። 34የሳ​ሜ​ርም ልጆች፤ አኪ፥ ሮኦጋ፥ ይሁባ፥ አራም ነበሩ። 35የወ​ን​ድ​ሙም የኡ​ላም ልጆች ጾፋ፥ ይምና፥ ሰሌስ፥ ዓማል ነበሩ። 36የጾ​ፋም ልጆች፤ ሴዋ፥ ሐር​ኔ​ፍር፥ ሦአል፥ ቤሪ፥ ይምራ፥ 37ቤጼር፥ ሆድ፦ ሳማ፦ ሰሌሳ፥ ይት​ራን፦ ብኤራ ነበሩ። 38የዬ​ቴ​ርም ልጆች፤ ያፊና፥ ፊስጳ፥ አራ ነበሩ። 39የዑላ ልጆች፤ ኤራ፥ ሐኔ​ኤል፥ ሪጽያ ነበሩ። 40እነ​ዚህ ሁሉ የአ​ሴር ልጆች፥ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች አለ​ቆች፥ የተ​መ​ረጡ ጽኑ​ዓን ኀያ​ላን ሰዎች፥ የመ​ኳ​ን​ንቱ አለ​ቆች ነበሩ። በት​ው​ል​ዳ​ቸ​ውም በሰ​ልፍ ለመ​ዋ​ጋት የተ​ቈ​ጠሩ ሃያ ስድ​ስት ሺህ ሰዎች ነበሩ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ