መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ 4
4
የይሁዳ ትውልድ
1የይሁዳ ልጆች ፋሬስ፥ ኤስሮም ከርሚ፥ ሆርና ሱባል ናቸው። 2የሱባልም ልጅ ራያ ኢኤትን ወለደ፤ ኢኤትም አሑማይንና ላሃድን ወለደ። እነዚህ የሰራአውያን ትውልዶች ናቸው። 3እነዚህም የኤጣም ልጆች#ዕብ. “የኤጣም አባት ልጆች” ይላል። ናቸው፤ ኢይዝራኤል፥ ይሰማ፥ ኤጋቢስ፥ እኅታቸውም ኤሴልፎን። 4የጌዶርም አባት ፋኑኤል፥ የአሶን አባት አዜር፤ እነዚህ የቤተ ልሔም አባት የኤፍራታ የበኵሩ የሆር ልጆች ናቸው። 5ለቴቁሄም አባት ለአስሑር ሔላና ነዓራ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ኦዳና ቶዳ” ይላል። የተባሉ ሁለት ሚስቶች ነበሩት። 6ነዓራም አሑዛምን፥ ኦፌርን፥ ቴማንንና አስትራን ወለደችለት። እነዚህ የነዓራ ልጆች ናቸው። 7የሔላም ልጆች ሴሬት፥ ይጽሐርና ኢትናን ናቸው። 8ቆስ፥ ኢኖብን፥ ሲባባን፥ የሃሩምንም ልጅ የሬካብን ወንድም ወገኖች ወለደ። 9ያግቤጽም ከወንድሞቹ ይልቅ የተከበረ ነበረ፤ እናቱም፦ በጣር ወልጄዋለሁና ብላ ስሙን፦ ያግቤጽ ብላ ጠራችው። 10ያግቤጽም፥ “እባክህ፥ መባረክን ባርከኝ፥ ሀገሬንም አስፋው፤ እጅህም ከእኔ ጋር ትሁን፤ እንዳያሳዝነኝም ምልክት አድርግልኝ” ብሎ የእስራኤልን አምላክ ጠራ፤ እግዚአብሔርም የለመነውን ሰጠው።
11የሱሃም ወንድም#ግሪክ ሰባ. ሊ. “አባት” ይላል። ካሌብ የኤስቶንን አባት ማኪርን ወለደ። 12ኤስቶንም ቤቶራፋንና ፋሲሓን፥ የቄኔዛዊው የኤሴሎምን ወንድም የነዓስ ከተማ አባት ታሒናን ወለደ፤ እነዚህ የራፋ ሰዎች ናቸው። 13የቄኔዝም ልጆች ጎቶንያልና ሠራኢያ ነበሩ። የጎቶንያልም ልጅ አታት ነበረ። 14መናቲም ጎፍራን ወለደ። ሠራኢያም የጌራሲምን አባት ኢዮአብን ወለደ፤ እነርሱም ጠራቢዎች ነበሩ። 15የዮፎኒም ልጅ የካሌብ ልጆች ዔሩ፥ ኤላ፥ ነዓም ነበሩ። የኤላም ልጅ ቄኔዝ ነበረ። 16የኢያልኤል ልጆች ዜፍ፥ ዚፋ፥ ቲርያ፥ አሣርኤል ነበሩ። 17የኤዜራስም ልጆች፤ ኢያቴር፥ ሞራድ፥ ጋፌር፥ ኢያሎን ነበሩ፤ ኢያቴርም ማሮንን፥ ሰማዒን፥ የኢስቲሞንን አባት ይስባኤልን ወለደ። 18ሚስቱ አይሂዳም የጌዶርን አባት ያሬድን፥ የሦኮንም አባት ሔቤርን፥ የዛኖዋንም አባት ይቁቲኤልን ወለደች። እነዚህ ሞሬድ ያገባት የፈርዖን ልጅ የቢትያ ልጆች ናቸው። 19የሆድያ ሚስት የነሐም እኅት ልጆች የገርሜው የቅዔላ አባትና ማዕካታዊው ኤሲትሞዓ ነበሩ። 20የሴሞንም ልጆች አምኖን፥ የአናን ልጆች ሬኖንና ቲሎን ነበሩ፤ የይስቴም ልጆች ዘካትና የዘካት ልጆች ነበሩ። 21የይሁዳም ልጅ የሴሎም ልጆች የሌካ አባት ዔር፥ የመሪሳ አባት ለዓዳ፥ ከአስቤዓ ቤት የሚሆኑ ጥሩ በፍታ የሚሠሩ#“ጥሩ በፍታ የሚሠሩ” የሚለው በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ወገኖች፥ 22ኢዮአቄም፥ የካዚባ ሰዎች፥ ኢዮአስ፥ በሞዓብ አድሮ ስማቸውን፥ አብዶራንና ተቂኤም ብሎ የመለሰ ሣራፍ ነበሩ። 23እነዚህ በነጣዔምና በጋዲራ ከንጉሡ ጋር የሚቀመጡ ሸክላ ሠራተኞች ነበሩ። እነርሱም በመንግሥቱ ጸንተው በዚያ ይኖሩ ነበር።
24የስምዖንም ልጆች፤ ነሙኤል፥ ያሚን፥ ያሪብ፥ ዛራ፥ ሳኡል፤ 25ልጁ ሳሌም፥ ልጁ መብሳም፥ ልጁ ማስማዕ። 26የማስማዕም ልጆች፤ ልጁ ሃሙኤል፥ ልጁ ሳባድ፥#“ሳባድ” የሚለው በዕብ. የለም። ልጁ ዝኩር፥ ልጁ ሰሜኢ። 27ለሰሜኢም ዐሥራ ስድስት ወንዶችና ስድስት#“ሶስት” የሚል ዘርም ይገኛል። ሴቶች ልጆች ነበሩት፤ ለወንድሞቹ ግን ብዙ ልጆች አልነበሩአቸውም፥ ወገናቸውም ሁሉ እንደ ይሁዳ ልጆች አልተባዙም። 28በቤርሳቤህም፥ በሰምዓም፥ በሞላዳ፥ በሐጸርሱዓል፥ 29በቤልሃ፥ በዔጼም፥ በቶላድ፤ 30በቤቱኤል፥ በሔርማ፥ በሤቄላቅ፤ 31በቤትማርካቦት፥ በሐጸርሱሲም፥ በቤትቢሪ፥ በሰዓራይም ይቀመጡ ነበር። እስከ ዳዊትም መንግሥት ድረስ ከተሞቻቸው እነዚህ ነበሩ። 32መንደሮቻቸውም ኤጣም፥ ዓይን፥ ሬሞን፥ ቶኪን፥ ዓሻን፥ አምስቱ ከተሞች፤ 33መንደሮቻቸውም ሁሉ እስከ በኣል ድረስ በእነዚህ ከተሞች ዙሪያ ነበሩ። መቀመጫቸውና ድርሻቸውም ይህ ነበረ። 34መሶባብ፥ የምሌክ፥ የአሚስያስ ልጅ ኢዮስያ፤ 35ኢዮኤል፥ የዮስብያ ልጅ፥ የሠራያ ልጅ የአሣኤል ልጅ ኢዩ፤ 36ኤልዮዔናይ፥ ያዕቀባ፥ የሰሐያ፥ ዓሣያ፥ ዓዲዔል፥ ይስማኤል፥ በናያስ፤ 37የሳፋኤ ልጅ ዙዛ፥ የአሎን ልጅ የይዳያ ልጅ የሰማሪ ልጅ የሰማያ ልጅ፤ 38እነዚህ በስማቸው የተጠሩ በወገኖቻቸው ላይ አለቆች ነበሩ፤ የአባቶቻቸውም ቤቶች በዝተው ነበር። 39ለመንጎቻቸው መሰማርያ ይሹ ዘንድ ወደ ጌራራ እስኪደርሱ ድረስ ወደ ጋይ ምሥራቅ ሄዱ። 40ብዙና እጅግ ያማረ መሰማርያም አገኙ፤ ምድሪቱም በፊታቸው ሰፊና ጸጥተኛ ሰላም ያላትም ነበረች፤ በቀድሞም ጊዜ በዚያ ተቀምጠው የነበሩ ከካም ወገን ነበሩ። 41በስማቸው የተጻፉ እነዚህም በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ ዘመን መጥተው ድንኳኖቻቸውንና በዚያ የተገኙትን ምዑናውያንን መቱ፥ እስከ ዛሬም ድረስ ፈጽመው አጠፉአቸው፤ በዚያም ለመንጎቻቸው መሰማሪያ ነበርና በስፍራቸው ተቀመጡ። 42ከስምዖንም ልጆች አምስት መቶ ሰዎች ወደ ሴይር ተራራ ሄዱ፤ አለቆቻቸውም የይሰዔ ልጆች ፥ ፈላጥያ፥ ነዓርያ፥ ረፋያ፥ ዑዝኤል ነበሩ። 43ያመለጡትንም የአማሌቃውያንን ቅሬታ መቱ፥ በዚያም እስከ ዛሬ ድረስ ተቀምጠዋል።
Currently Selected:
መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ 4: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ