የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙረ ዳዊት 107

107
1ሃሌ ሉያ! #መዝ. 100፥4-5፤ 106፥1፤ ኤር. 33፥11።ቸር ነውና፥ ፍቅሩም ለዘለዓለም ነውና
ጌታን አመስግኑ፥
2 # ኢሳ. 63፥12። ጌታ የታደጋቸው፥
ከጠላትም እጅ ያዳናቸው ይናገሩ።
3 # ኢሳ. 43፥5-6፤ 49፥12፤ ዘካ. 8፥7። ከምሥራቅና ከምዕራብ፥ ከሰሜንና ከባሕር፥
ከየአገሩ ሰበሰባቸው።
4በበረሃ፥ በምድረ በዳ ተቅበዘበዙ፥
የሚኖሩበትንም ከተማ መንገድ አላገኙም።
5 # ዘዳ. 8፥15፤ 32፥10፤ ኢሳ. 49፥10። ተራቡ፥ ተጠሙም፥
ነፍሳቸውም ዛለች።
6በተጨነቁ ጊዜ ወደ ጌታ ጮኹ፥
ከመከራቸውም አዳናቸው፥
7 # ዘዳ. 6፥10። ወደሚኖሩበት ከተማ ይሄዱ ዘንድ
በቀና መንገድን መራቸው።
8ለሰው ልጆች ስላደረገው ተኣምራት
ስለ ጽኑ ፍቅሩም ጌታን ያመስግኑ፥
9 # ሉቃ. 1፥53። የተጠማችን ነፍስ አጥግቦአልና፥
የተራበችን ነፍስ በበረከት ሞልቶአልና።
10በጨለማ በሞትም ጥላ የተቀመጡ፥
በችግር በብረትም የታሰሩ፥
11 # ኢሳ. 42፥7፤22፤ ኢዮብ 36፥8-9፤ ምሳ. 1፥25። በእግዚአብሔር ቃል ላይ ስለ ዐመፁ፥
የልዑልንም ምክር ስለ ናቁ፥
12 # መዝ. 106፥43። ልባቸው በድካም ተዋረደ፥
ተሰናከሉ የሚረዳቸውም አጡ።
13በተጨነቁ ጊዜ ወደ ጌታ ጮኹ፥
ከመከራቸውም አዳናቸው።
14 # ኢሳ. 42፥7፤ 49፥9፤ 51፥14። ከጨለማና ከሞት ጥላ አወጣቸው፥
ሰንሰለታቸውንም በጣጠሰ።
15ለሰው ልጆች ስላደረገው ተኣምራት
ስለ ጽኑ ፍቅሩም ጌታን ያመስግኑ፥
16የናሱን ደጆች ሰብሮአልና፥
የብረቱንም መወርወሪያ ቈራርጦአልና።
17በዓመፅ መንገዳቸው አላዋቂ ሆኑ፥
በጥፋታቸው ተጎሳቆሉ።
18 # ኢዮብ 6፥6-7፤ 33፥20። ሰውነታቸው መብልን ሁሉ ተጸየፈች፥
ወደ ሞትም ደጆች ቀረቡ።
19በተጨነቁ ጊዜም ወደ ጌታ ጮኹ፥
ከጭንቀታቸው አዳናቸው።
20 # መዝ. 147፥15፤ ጥበ. 16፥12፤ ኢሳ. 55፥11፤ ማቴ. 8፥8። ቃሉን ላከ ፈወሳቸውም፥
ከአዘቅትም አዳናቸው።
21ለሰው ልጆች ስላደረገው ተኣምራት
ስለ ጽኑ ፍቅሩም ጌታን ያመስግኑ፥
22የምስጋና መሥዋዕትንም ይሠውለት፥
በእልልታም ሥራውን ይንገሩ።
23 # ሲራ. 43፥25። በመርከቦች ወደ ባሕር የሚወርዱ፥
በታላላቅ ውኆች ሥራቸውን የሚሠሩ፥
24እነርሱ የጌታን ሥራ፥
በታላቅ አዘቅትም ያሉትን ድንቅ ሥራዎች አዩ።
25 # ዮናስ 1፥4። ተናገረ፥ ዐውሎ ነፋስም ተነሣ፥
ሞገዶችንም አስነሣ።
26ወደ ሰማይ ይወጣሉ ወደ ጥልቅም ይወርዳሉ፥
ነፍሳቸውም በመከራ ቀለጠች።
27 # ኢሳ. 29፥9። ደነገጡ እንደ ስካርም ተንገደገዱ፥
ጥበባቸውም ሁሉ ተዋጠች።
28በተጨነቁ ጊዜ ወደ ጌታ ጮኹ፥
ከመከራቸውም አዳናቸው።
29 # መዝ. 65፥8፤ 89፥10፤ ማቴ. 8፥26። ዐውሎ ነፋሱን አስቆመ፥
ሞገዱም ጸጥ አለ።
30ዝም ብለዋልና ደስ አላቸው፥
ወደ ፈለጉትም ወደብ መራቸው።
31ስለ ጽኑ ፍቅሩ፥
ለሰው ልጆች ስላደረገው ተአምራት ጌታን ያመስግኑ።
32በሕዝብ ጉባኤ መካከል ከፍ ከፍ ያድርጉት፥
በሽማግሌዎችም ሸንጎ ያመስግኑት።
33 # ኢሳ. 35፥7፤ 42፥15፤ 50፥2። ወንዞችን ምድረ በዳ፥
የውኃውንም ምንጮች ደረቅ መሬት አደረገው፥
34 # ዘፍ. 19፥23-28፤ ዘዳ. 29፥22፤ ሲራ. 39፥23። ከነዋሪዎቿ ክፋት የተነሣ
ፍሬያማዋን ምድር ጨው አደረጋት።
35 # መዝ. 114፥8፤ ኢሳ. 41፥8። ምድረ በዳን ወደ ውኃ ማጠራቀምያ፥
ደረቁንም ምድር ወደ ውኃ ምንጭነት ቀየረ።
36 # ሕዝ. 36፥35። በዚያም ረሀብተኞችን አስቀመጠ፥
የሚኖሩባትንም ከተማ ሠሩ።
37 # ኢሳ. 65፥21፤ ኤር. 31፥5። እርሻዎችንም ዘሩ፥ ወይኖችንም ተከሉ፥
ፍሬንም ሰበሰቡ።
38 # ዘዳ. 7፥13-14፤ ኢዮብ 12፥23-25። ባረካቸውም እጅግም በዙ፥
እንስሶቻቸውንም አላሳነሰባቸውም።
39እነርሱ በጭቈና፥ በስቃይና በኃዘን ተዋርደው እያነሱ ሄዱ፥
40በመኰንኖችም ላይ ውርደትን ዘረገፈ፥
መንገድም በሌለበት በምድረ በዳ አንከራተታቸው።
41 # መዝ. 113፥7። ችግረኛንም ከመከራው አወጣው፥
ቤተሰቦችን እንደ በጎች መንጋ አበዛ።
42 # መዝ. 58፥11፤ 63፥12። ቅኖች ያያሉ፥ ደስም ይላቸዋል፥
ክፋት በሙሉ አፉን ይዘጋል።
43 # ሆሴዕ 14፥10። ጠቢብ ማነው? ይህንን ይፈጽም፥
እርሱ የጌታንም ጽኑ ፍቅር ይገነዘባል።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ