መዝሙረ ዳዊት 103
103
1የዳዊት መዝሙር።
ነፍሴ ሆይ፥ ጌታን ባርኪ፥
አጥንቶቼም#103፥1 ሁለመናዬ። ሁሉ፥ የተቀደሰ ስሙን።
2ነፍሴ ሆይ፥ ጌታን ባርኪ፥
ውለታውንም ከቶ አትርሺ፥
3ጥፋትሽንም ሁሉ ይቅር የሚል፥
ደዌሽንም ሁሉ የሚፈውስ፥
4 #
መዝ. 28፥1፤ 30፥4፤ 40፥3፤ 69፥16፤ 88፥5፤ 143፥7፤ ምሳ. 1፥12፤ ዮናስ 2፥7። ሕይወትሽን ከጥፋት የሚያድናት፥
በፍቅርና በርኅራኄ የሚከልልሽ፥
5ምኞትሽን ከበረከቱ የሚያጠግባት፥
ጎልማሳነትሽን እንደ ንስር ያድሳል።
6 #
መዝ. 146፥6-7። ጌታ ጽድቅን ይፈጽማል፥
ለተበደሉ ሁሉ ይፈርዳል።
7ለሙሴ መንገዱን አስታወቀ፥
ለእስራኤል ልጆችም ድንቅ ሥራዎቹን።
8 #
መዝ. 86፥15፤ 145፥8፤ ዘፀ. 34፥6-7፤ ዘኍ. 14፥18፤ ኤር. 3፥12፤ ኢዩ. 2፥13፤ ዮናስ 4፥2። ጌታ ርኅሩኅና ቸር ነው፥
ከቁጣ የራቀ ፍቅሩም የበዛ።
9ሁልጊዜም አይከስም፥ ለዘለዓለምም አይቈጣም።
10እንደ ኃጢአታችን አላደረገብንም፥
እንደ በደላችንም አልከፈለንም።
11 #
ኢሳ. 55፥9። ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል፥
እንዲሁ ምሕረቱን በሚፈሩት ላይ አጠነከረ።
12ምሥራቅ ከምዕራብ እንደሚርቅ፥
እንዲሁ ኃጢአታችንን ከእኛ አራቀ።
13አባት ለልጆቹ እንደሚራራ
እንዲሁ ጌታም ለሚፈሩት ይራራል፥
14 #
መዝ. 90፥3። ፍጥረታችንን እርሱ ያውቃልና፥
እኛ አፈር እንደ ሆንን ያስታውሳል።
15 #
መዝ. 37፥2፤ 90፥5-6፤ ኢሳ. 40፥7። ሰውስ ዘመኑ እንደ ሣር ነው፥
እንደ ዱር አበባ እንዲሁ ያብባል፥
16ነፋስ በነፈሰበት ጊዜ ያልፋልና፥
ስፍራውንም ደግሞ አያውቀውምና።
17የጌታ ጽኑ ፍቅር ግን ከዘለዓለም
እስከ ዘለዓለም በሚፈሩት ላይ፥
ጽድቁም በልጅ ልጆች ላይ ነው፥
18ቃል ኪዳኑን በሚጠብቁ፥
ትእዛዙንም ያደርጉአት ዘንድ በሚያስቡ ላይ ነው።
19ጌታ ዙፋኑን በሰማይ አዘጋጀ፥
መንግሥቱም ሁሉን ትገዛለች።
20 #
መዝ. 148፥2፤ ዳን. 3፥58። ቃሉን የምትፈጽሙ መላእክቱ፥ ብርቱዎችና ኃያላን፥
የቃሉንም ድምፅ የምትሰሙ ሁሉ፥
ጌታን ባርኩ።
21ሠራዊቱ ሁሉ፥
ፈቃዱን የምታደርጉ አገልጋዮቹ፥
ጌታን ባርኩ።
22ፍጥረቶቹ ሁሉ በግዛቱ ስፍራ ሁሉ፥
ጌታን ባርኩ።
ነፍሴ ሆይ፥ ጌታን ባርኪ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 103: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ