1
መዝሙረ ዳዊት 103:2
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
ነፍሴ ሆይ፥ ጌታን ባርኪ፥ ውለታውንም ከቶ አትርሺ፥
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
መዝሙረ ዳዊት 103:3-5
ጥፋትሽንም ሁሉ ይቅር የሚል፥ ደዌሽንም ሁሉ የሚፈውስ፥ ሕይወትሽን ከጥፋት የሚያድናት፥ በፍቅርና በርኅራኄ የሚከልልሽ፥ ምኞትሽን ከበረከቱ የሚያጠግባት፥ ጎልማሳነትሽን እንደ ንስር ያድሳል።
3
መዝሙረ ዳዊት 103:1
ነፍሴ ሆይ፥ ጌታን ባርኪ፥ አጥንቶቼም ሁሉ፥ የተቀደሰ ስሙን።
4
መዝሙረ ዳዊት 103:13
አባት ለልጆቹ እንደሚራራ እንዲሁ ጌታም ለሚፈሩት ይራራል፥
5
መዝሙረ ዳዊት 103:12
ምሥራቅ ከምዕራብ እንደሚርቅ፥ እንዲሁ ኃጢአታችንን ከእኛ አራቀ።
6
መዝሙረ ዳዊት 103:8
ጌታ ርኅሩኅና ቸር ነው፥ ከቁጣ የራቀ ፍቅሩም የበዛ።
7
መዝሙረ ዳዊት 103:10-11
እንደ ኃጢአታችን አላደረገብንም፥ እንደ በደላችንም አልከፈለንም። ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል፥ እንዲሁ ምሕረቱን በሚፈሩት ላይ አጠነከረ።
8
መዝሙረ ዳዊት 103:19
ጌታ ዙፋኑን በሰማይ አዘጋጀ፥ መንግሥቱም ሁሉን ትገዛለች።
Home
Bible
Plans
Videos