መጽሐፈ ኢዮብ 25

25
1ሹሐዊውም በልዳዶስ መለሰ፤ እንዲህም አለ፦
2“ገዢነትና መፈራት በእርሱ ዘንድ ናቸው፥
በከፍታውም#25፥2 በሰማያት። ሰላምን የሚያሰፍን ነው።
3በውኑ ለሠራዊቱ ቍጥር ስፍር አለውን?
ብርሃኑስ የማይወጣው በማን ላይ ነው?
4ሰውስ በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ ይሆን ዘንድ፥
ከሴትስ የተወለደ#25፥4 የሰው ልጅ። ንጹሕ ይሆን ዘንድ እንዴት ይችላል?
5እነሆ፥ ጨረቃ እንኳ ብሩህ ካልሆነች፥
ከዋክብትም በፊቱ ንጹሐን ካልሆኑ።
6ይልቁንስ ፈራሽ የሆነ ሰው፥
ትልም የሆነ የሰው ልጅ ምንኛ ያንስ!”

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ