መጽሐፈ ኢዮብ 26

26
1ኢዮብም መለሰ፤ እንዲህም አለ፦
2“ኃይል የሌለውን ምንኛ ረዳኸው!#26፥2 የኢዮብ ንግግር ምፀት የተሞላበት ነው። “ምንኛ ረዳኸው” ሲል፥ ምንም አልረዳኸውም ማለቱ ነው። ምዕራፉ በሙሉ በዚህ መልክ ነው የተጻፈው። ኢዮብ ቢልዳድን እየወቀሰ ነው።
ብርታት የሌለውን ክንድ ምንኛ አዳንኸው!
3ጥበብስ የሌለውን ምንኛ መከርኸው!
ብዙ እውቀትንስ ምንኛ ገለጥህለት!
4ይህንንስ ቃል በማን እርዳታ ተናገርህ?
ያነሣሣህስ የማን መንፈስ ነው?
5ሙታን ከውኆች በታች፥
በውኆችም ውስጥ ከሚኖሩ በታች ይንቀጠቀጣሉ።
6ሲኦል በፊቱ ራቁትዋን ናት፥
ለጥፋትም መጋረጃ የለውም።
7ሰሜንን በባዶ ስፍራ ላይ ይዘረጋል፥
ምድሪቱንም ያለአንዳች ድጋፍ ያንጠለጥላል።
8ውኆችን በደመናዎቹ ውስጥ ያስራል፥
ደመናይቱም ከታች አልተቀደደችም።
9የዙፋኑን ፊት ይሸፍናል፥
ደመናውንም ይዘረጋበታል።
10ብርሃንና ጨለማ እስከሚለያዩበት ዳርቻ ድረስ፥
በውኆች ፊት ላይ ድንበርን አሰመረ።
11የሰማይ አዕማድ ይንቀጠቀጣሉ፥
ከተግሣጹም የተነሣ ይደነግጣሉ።
12በኃይሉ ባሕርን ጸጥ ያደርጋል፥
በማስተዋሉም ረዓብን ይመታል።
13በመንፈሱ ሰማያት ውበትን አገኙ፥
እጁም የሚሸሸውን እባብ ወጋች።
14እነሆ፥ እነኚህ የሥራዎቹ ጫፎች ብቻ ነው፥
ይህም የሰማነው ነገር ምንኛ ጥቂት ነው!
የኃይሉንስ ነጐድጓድ ማን ማስተዋል ይችላል?”

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ