የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ ኢዮብ 17

17
1መንፈሴ ደከመ፥ ቀኖቼ አለቁ፥
መቃብርም ተዘጋጅቶልኛል።
2አላጋጮች በእኔ ዘንድ አሉ፥
ዓይኔም ማስቈጣታቸውን ትመለከታለች።
3“እባክህን፥ አንተ ዋስ ሁነኝ፥
ለእኔ ተያዥ የሚሆነኝ ማን ነው?
4ልባቸውም እንዳያስተውል ከልክለኸዋል፥
ስለዚህ ከፍ ከፍ አታደርጋቸውም።
5ለብዝበዛ ባልንጀሮቹን አሳልፎ የሚሰጥ ሰው፥
የልጆቹ ዐይን ይጨልማል።”
6“ለሕዝብም ምሳሌ አደረገኝ፥
በፊቱ ላይ እንደሚተፉበት ሰው ሆንሁ።
7ዓይኔም ከኀዘን የተነሣ ፈዘዘች፥
መላ ሰውነቴ እንደ ጥላ ሆነ።
8ቅኖች ሰዎች በዚህ ነገር ይረበሻሉ፥
ንጹሕም አምላኩን በሚክድ ላይ ይበሳጫል።
9ጻድቅ ግን መንገዱን ያጠነክራል፥
እጁም ንጹሕ የሆነ ሰው ኃይልን እየጨመረ ይሄዳል።
10ነገር ግን እናንተ ሁሉ ተመልሳችሁ ወደ እኔ ኑ፥
በእናንተም ዘንድ ጠቢብ አላገኝም።
11ቀኖቼ አለፉ፥
ዕቅዴና የልቤ ምኞት ቀለጠ።
12ሌሊቱን ወደ ቀን ይለውጣሉ፥
ብርሃኑም ወደ ጨለማ የቀረበ ይመስላቸዋል።
13ተስፋ ባደርግ ሲኦል ቤቴ ናት፥
ምንጣፌንም በጨለማ ዘርግቻለሁ።
14መበስበስን፦ አንተ አባቴ ነህ፥
ትልንም፦ አንቺ እናቴ እኅቴም ነሽ ብያለሁ።
15እንግዲህ ተስፋዬ ወዴት ነው?
ተስፋዬንስ የሚያይ ማን ነው?
16ወደ ሲኦል ይወርዳልን?
አብረን ወደ አፍር ውስጥ እንገባ የለምን?”

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ