መጽሐፈ ኢዮብ 10
10
1“ሕይወቴ ሰለቸኝ፥
የኀዘን እንጉርጉሮዬን እለቅቀዋለሁ፥
በነፍሴም ምሬት እናገራለሁ።
2እግዚአብሔርን እንዲህ እለዋለሁ፦
አትፍረድብኝ፥ የምትከራከረኝ ለምን እንደሆነ ንገረኝ።
3ልታስጨንቅና የእጅህን ሥራ ልትንቅ
የክፉዎችንስ ምክር ልታበራ
በአንተ ዘንድ መልካም ነውን?
4በውኑ የሥጋ ዐይን አለህን?
ወይስ ሰው እንደሚያይ ታያለህን?
5ቀኖችህ እንደ ሰው ቀኖች ናቸውን?
ወይስ ዓመታትህ እንደ ሰው ቀናት ናቸውን?
6ታዲያ ክፋቴን የምትከታተለው፥
ኃጢአቴንም የምትመረምረው ለምንድን ነው?
7 #
ጥበ. 16፥15። ከዚህም በላይ በደለኛ እንዳልሆንሁ፥
ከእጅህም የሚያድን እንደሌለ አንተ ታውቃለህ።
8እጆችህ ቀረጹኝ ሠሩኝም፥
ከዚያም ተመልሰህ ታጠፋኝ ዘንድ ፈለግህ።
9ከጭቃ እንደሠራኸኝ አስታውስ፥
ወደ ትቢያም ትመልሰኛለህን?
10 #
ጥበ. 7፥1፤2። በውኑ እንደ ወተት አላፈሰስኸኝምን?
እንደ እርጎስ አላረጋኸኝምን?
11ቁርበትና ሥጋ አለበስኸኝ፥
በአጥንትና በጅማትም አጠንከርኸኝ።
12ሕይወትና ቸርነት አደረግህልኝ፥
መጐብኘትህም መንፈሴን ጠበቀች።
13እነዚህንም ነገሮች በልብህ ውስጥ ሰወርህ፥
ይህ ሁሉ በአሳብህ እንዳለ አውቃለሁ።
14ኃጢአት ብሠራ አንተ ትመለከተኛለህ፥
ከኃጢአቴም ንጹሕ አታደርገኝም።
15በደለኛ ብሆን ወዮልኝ፥
ጻድቅም ብሆን ራሴን አላነሣም፥
ጉስቁልናን ተሞልቻለሁና፥
መከራዬንም ተመልክቻለሁና።
16ራሴም ከፍ ከፍ ቢል እንደ አንበሳ ታድነኛለህ፥
ተመልሰህም ድንቅ ነገር ታድርግብኛለህ።
17ምስክሮችህን ታድስብኛለህ፥
ቁጣህንም ታበዛብኛለህ፥
ጭፍራ በጭፍራ ላይ ትጨምርብኛለህ።”
18“ስለምን ከማኅፀን አወጣኸኝ?
ዐይን ሳያየኝ ምነው በሞትሁ።
19እንዳልነበረ በሆንሁ፥
ከማኅፀንም ወደ መቃብር በወሰዱኝ።
20የሕይወቴ ቀኖች ጥቂት አይደሉምን?
21ወደማልመለስበት ስፍራ ሳልሄድ፥
ወደ ጨለማና ወደ ሞት ጥላ ምድር፥
22እንደ ጨለማም ወደ ጨለመች፥
ሥርዓትም ወደሌለባት ወደ ሞት ጥላ፥
ብርሃንዋም እንደ ጨለማ ወደ ሆነ ምድር ሳልሄድ፥
ጥቂት እጽናና ዘንድ ተወኝ፥ ልቀቀኝም።”
Currently Selected:
መጽሐፈ ኢዮብ 10: መቅካእኤ
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ
![None](/_next/image?url=https%3A%2F%2Fimageproxy.youversionapi.com%2F58%2Fhttps%3A%2F%2Fweb-assets.youversion.com%2Fapp-icons%2Fam.png&w=128&q=75)
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ