መጽሐፈ ኢዮብ 11

11
1ናዕማታዊውም ሶፋር መለሰ፤ እንዲህም አለ፦
2“በውኑ ነገር ለሚያበዛ መልስ መስጠት አይገባምን?
ወይስ ተናጋሪ ሰው እንደ ጻድቅ ይቈጠራልን?
3ከንቱ ልፍለፋህ ሰዎችን ዝም ያሰኛቸዋልን?
ብትሳለቅስ የሚያሳፍርህ የለምን?
4አንተ፦ ትምህርቴ የተጣራ ነው፥
በዓይንህም ፊት ንጹሕ ነኝ ትላለህ።
5ምነው እግዚአብሔር ቢናገርህ!
በአንተም ላይ ከንፈሩን ቢከፍት!
6የጥበቡን ምሥጢር ቢገልጥልህ!
ማስተዋሉ እጥፍ ነውና።
እግዚአብሔር ለበደልህ ከሚገባው አሳንሶ እንደሚያስከፍልህ እወቅ።”
7“የእግዚአብሔርን ጥልቅ ነገር ልትመረምር ትችላለህን?
ሁሉን የሚችል አምላክን ፍጻሜ ልትመረምር ትችላለህን?
8ከሰማይ ይልቅ ከፍ ይላል፥ ምን ልታደርግ ትችላለህ?
ከሲኦልም ይልቅ ይጠልቃል፥ ምን ልታውቅ ትችላለህ?
9ርዝመቱ ከምድር ይልቅ ይረዝማል፥
ከባሕርም ይልቅ ይሰፋል።
10እርሱ ቢያልፍ፥ ቢዘጋም፥ ጉባኤንም ቢሰበስብ፥
የሚከለክለው ማን ነው?
11የማይረቡ ሰዎችን ያውቃልና፥
በደልንም ሲያይ ዝም ብሎ አይመለከትም።
12የሜዳ አህያ ሰው ሆኖ ሲወለድ፥
ከንቱ ሰው ጥበብን ያገኛል።”
13-14“አንተ ልብህን ቅን ብታደርግ፥
እጆችህን ወደ እርሱ ትዘረጋለህ፥
በእጅህ በደል ቢኖር አርቀው፥
በድንኳንህም#11፥13-14 በቤትህም ኃጢአት አይኑር፥
15በዚያን ጊዜ በእውነት ፊትህን ያለ ነውር ታነሣለህ፥
ትበረታለህ፥ አትፈራምም።
16መከራህንም ትረሳለህ፥
እንዳለፈ ውኃ ታስበዋለህ።
17ሕይወትህ ከቀትር ይልቅ ያበራል፥
ጨለማም ቢሆን እንደ ጥዋት ይሆናል።
18ተስፋም ስላለህ ተማምነህ ትቀመጣለህ፥
በዙሪያህ ትመለከታለህ#11፥18 ይህንን ጥቅስ እንደሚከተለው መተርጎም ይቻላል፥ “ብታፍርም እንኳን በደኅንነት ታርፋለህ።”፥ በደኅንነትም ታርፋለህ።
19ትተኛለህ፥ የሚያስፈራህም የለም፥
ብዙ ሰዎችም ልመና ያቀርቡልሃል።
20የክፉዎች ዐይን ግን ትጨልማለች፥
የሚሸሹበትንም ያጣሉ፥
ተስፋቸውም ነፍስን አሳልፎ መስጠት ነው።”

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ