ለሴምም ደግሞ ልጆች ተወለዱለት፥ እርሱም የያፌት ታላቅ ወንድምና የዔቦር ልጆች ሁሉ ቅድመ አያት ነው። የሴም ልጆች፦ ዔላም፥ አሦር፥ አርፋክስድ፥ ሉድ እና አራም ናቸው። የአራም ልጆች፦ ዑፅ፥ ሑል፥ ጌተር እና ሜሼክ ናቸው። አርፋክስድ ሼላሕን ወለደ፤ ሼላሕም ዔቦርን ወለደ። ዔቦር ሁለት ልጆች ወለደ፤ አንደኛው እርሱ በተወለደበት ዘመን ሕዝቦች ስለ ተከፋፈሉ ፋሌቅ ተባለ፤ ሌላው ዮቅጣን ይባል ነበር። የዮቅጣን ልጆች፦ አልሞዳድ፥ ሼሌፍ ሐጻርማዌት፥ ዬራሕ፥ ሀዶራም፥ ኡዛል፥ ዲቅላ፥ ዖባል፥ አቢማኤል፥ ሳባ፥ ኦፊር፥ ሐዊላና ዮባብ ናቸው፤ እነዚህ ሁሉ የዮቅጣን ዘሮች ናቸው። እነርሱ የኖሩበት ግዛት በስተ ምሥራቅ ባለው በተራራማው አገር ከሜሻ እስከ ሰፋር ይደርስ ነበር። የሴም ልጆች በየነገዳቸውና በየቋንቋቸው፥ በየምድራቸውና በየሕዝባቸው እነዚህ ናቸው። ከጥፋት ውሃ በኋላ የምድር ሕዝቦች፥ እነዚህ በየነገዳቸው የተከፋፈሉ የኖኅ ዘሮች ነበሩ፤ ሁሉም የተገኙት ከእነዚህ ከኖኅ ልጆች ነበር።
ኦሪት ዘፍጥረት 10 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ኦሪት ዘፍጥረት 10:21-32
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች