ኦሪት ዘፍጥረት 10:21-32

ኦሪት ዘፍጥረት 10:21-32 አማ05

የያፌት ታላቅ ወንድም ሴም የዔቦር ዘሮች ቅድመ አያት ነው። የሴም ልጆች፦ ዔላም፥ አሦር፥ አርፋክስድ፥ ሉድና አራም ናቸው። የአራም ልጆች፦ ዑፅ፥ ሑል፥ ጌተርና ሜሼክ ናቸው፤ አርፋክስድ ሼላሕን ወለደ፤ ሼላሕም ዔቦርን ወለደ። ዔቦር ሁለት ልጆች ወለደ፤ አንደኛው እርሱ በተወለደበት ዘመን ሕዝቦች ስለ ተከፋፈሉ ፋሌቅ ተባለ፤ ሌላው ዮቅጣን ይባል ነበር። የዮቅጣን ልጆች፦ አልሞዳድ፥ ሼሌፍ ሐጻርማዌት፥ ዬራሕ፥ ሀዶራም፥ ኡዛል፥ ዲቅላ፥ ዖባል፥ አቢማኤል፥ ሳባ፥ ኦፊር፥ ሐዊላና ዮባብ ናቸው፤ እነዚህ ሁሉ የዮቅጣን ዘሮች ናቸው። እነርሱ የኖሩበት ምድር በስተምሥራቅ ባለው በተራራማው አገር ከሜሻ እስከ ሰፋር ይደርስ ነበር። እነዚህ ሁሉ የሴም ዘሮች ናቸው፤ እነርሱ በተለያዩ ጐሣዎችና አገሮች ተከፍለው ይኖሩ ነበር፤ እያንዳንዱም ጐሣ የሚነጋገረው በራሱ ቋንቋ ነበር። እነዚህ በየነገዳቸው የተከፋፈሉ ሕዝቦች የኖኅ ዘሮች ነበሩ፤ ከጥፋት ውሃ በኋላ የምድር ሕዝቦች ሁሉ የተገኙት ከእነዚህ ከኖኅ ልጆች ነበር።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}