ዘፍጥረት 10:21-32

ዘፍጥረት 10:21-32 NASV

ለያፌት ታላቅ ወንድም ለሴም ደግሞ ወንዶች ልጆች ተወለዱለት፤ እርሱም የዔቦር ልጆች ሁሉ ቅደመ አያት ነው። የሴም ልጆች፦ ኤላም፣ አሦር፣ አርፋክስድ፣ ሉድ፣ አራም ናቸው። የአራም ልጆች፤ ዑፅ፣ ሁል፣ ጌቴር፣ ሜሼኽ። አርፋክስድ ሳላን ወለደ፤ ሳላም ዔቦርን ወለደ። ለዔቦርም ሁለት ወንዶች ልጆች ተወለዱለት፤ አንደኛው ልጅ በዘመኑ ምድር ተከፍላ ስለ ነበር ፋሌቅ ተባለ፤ ወንድሙም ዮቅጣን ተባለ። ዮቅጣንም፦ አልሞዳድን፣ ሣሌፍን፣ ሐስረሞትን፣ ያራሕን፣ ሀዶራምን፣ አውዛልን፣ ደቅላን፣ ዖባልን፣ አቢማኤልን፣ ሳባን፣ የኦፊር፣ የኤውላጥ፣ የዮባብ አባት ነበረ፤ እነዚህ ሁሉ የዮቅጣን ልጆች ናቸው። መኖሪያ ስፍራቸውም እስከ ሶፋር ድረስ ይዘልቃል። እነዚህም በየጐሣቸውና በየቋንቋቸው፣ በየምድራቸውና በየነገዳቸው ይኖሩ የነበሩ የሴም ዝርያዎች ናቸው። የኖኅ ወንዶች ልጆች ጐሣዎች እንደ ትውልዳቸው በየነገዳቸው እነዚህ ነበሩ። ከጥፋት ውሃ በኋላ ሕዝቦች በምድር ላይ የተሠራጩት ከእነዚሁ ነው።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}