ዘፍጥረት 10:21-32

ዘፍጥረት 10:21-32 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ለሴ​ምም ደግሞ ልጆች ተወ​ለ​ዱ​ለት፤ እር​ሱም የያ​ፌት ታላቅ ወን​ድ​ምና የዔ​ቦር ልጆች ሁሉ አባት የሆ​ነው ነው። የሴ​ምም ልጆች ኤላም፥ አሦር፥ አር​ፋ​ክ​ስድ፥ ሉድ፥ አራም፥ ቃይ​ናን። የአ​ራ​ምም ልጆች ዑፅ፥ ሁል፥ ጋቴር፥ ሞሳሕ ናቸው። አር​ፋ​ክ​ስ​ድም ቃይ​ና​ንን ወለደ፤ ቃይ​ና​ንም ሳላን፥ ሳላም ዔቦ​ርን ወለደ። ለዔ​ቦ​ርም ሁለት ልጆች ተወ​ለ​ዱ​ለት፤ የአ​ን​ደ​ኛው ስሙ ፋሌቅ ነው፤ ምድር በዘ​መኑ ተከ​ፍ​ላ​ለ​ችና፤ የወ​ን​ድ​ሙም ስም ዮቅ​ጣን ነው። ዮቅ​ጣ​ንም ኤል​ሞ​ዳ​ድን፥ ሳሌ​ፍ​ንም፥ ሐሰ​ረ​ሞ​ት​ንም፥ ያራ​ሕ​ንም፥ ሀዶ​ራ​ም​ንም፥ አዚ​ላ​ንም፥ ደቅ​ላ​ንም፥ ዖባ​ል​ንም፥ አቤ​ማ​ኤ​ል​ንም፥ ሳባ​ንም፥ አፌ​ር​ንም፥ ኤው​ላ​ጥ​ንም፥ ዮባ​ብ​ንም ወለደ፤ እነ​ዚህ ሁሉ የዮ​ቅ​ጣን ልጆች ናቸው። ስፍ​ራ​ቸ​ውም ከማሲ አን​ስቶ ወደ ስፋር ሲል እስከ ምሥ​ራቅ ተራራ ድረስ ነው። የሴም ልጆች በየ​ነ​ገ​ዳ​ቸ​ውና በየ​ቋ​ን​ቋ​ቸው፥ በየ​ም​ድ​ራ​ቸ​ውና በየ​ሕ​ዝ​ባ​ቸው እነ​ዚህ ናቸው። የኖኅ የል​ጆቹ ነገ​ዶች እንደ ትው​ል​ዳ​ቸው በየ​ሕ​ዝ​ባ​ቸው እነ​ዚህ ናቸው። ከእ​ነ​ዚ​ህም ከጥ​ፋት ውኃ በኋላ ሕዝ​ቦች በም​ድር ላይ ተዘሩ።

ዘፍጥረት 10:21-32 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ለያፌት ታላቅ ወንድም ለሴም ደግሞ ወንዶች ልጆች ተወለዱለት፤ እርሱም የዔቦር ልጆች ሁሉ ቅደመ አያት ነው። የሴም ልጆች፦ ኤላም፣ አሦር፣ አርፋክስድ፣ ሉድ፣ አራም ናቸው። የአራም ልጆች፤ ዑፅ፣ ሁል፣ ጌቴር፣ ሜሼኽ። አርፋክስድ ሳላን ወለደ፤ ሳላም ዔቦርን ወለደ። ለዔቦርም ሁለት ወንዶች ልጆች ተወለዱለት፤ አንደኛው ልጅ በዘመኑ ምድር ተከፍላ ስለ ነበር ፋሌቅ ተባለ፤ ወንድሙም ዮቅጣን ተባለ። ዮቅጣንም፦ አልሞዳድን፣ ሣሌፍን፣ ሐስረሞትን፣ ያራሕን፣ ሀዶራምን፣ አውዛልን፣ ደቅላን፣ ዖባልን፣ አቢማኤልን፣ ሳባን፣ የኦፊር፣ የኤውላጥ፣ የዮባብ አባት ነበረ፤ እነዚህ ሁሉ የዮቅጣን ልጆች ናቸው። መኖሪያ ስፍራቸውም እስከ ሶፋር ድረስ ይዘልቃል። እነዚህም በየጐሣቸውና በየቋንቋቸው፣ በየምድራቸውና በየነገዳቸው ይኖሩ የነበሩ የሴም ዝርያዎች ናቸው። የኖኅ ወንዶች ልጆች ጐሣዎች እንደ ትውልዳቸው በየነገዳቸው እነዚህ ነበሩ። ከጥፋት ውሃ በኋላ ሕዝቦች በምድር ላይ የተሠራጩት ከእነዚሁ ነው።

ዘፍጥረት 10:21-32 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ለሴምም ደግሞ ልጆች ተወለዳለት እርሱም የያፌት ታላቅ ወምድምና የዔቦር ልጆች ሁሉ አባት የሆነ ነው። የሴምም ልጆች ኤላም፥ አሦር፥ አርፋክስድ፥ ሉድ፥ አራም ናቸው። የአራምም ልጆች ዑፅ፥ ሁል፥ ጌቴር፥ ሞሶሕ ናቸው። አርፋክስድም ቃይንምን ወለደ፤ ቃይንምም ሳላን፥ ሳላም ዔቦርን ወለደ። ለዔቦርን ሁለት ልጆች ተወለዱለት የአንደኛው ስሙ ፋሌቅ ነው፥ ምድር በዘመኑ ተከፍላለችና፤ የወንድሙም ስም ዩቅጣን ነው። ዩቅጣንም ኤልሞዳድን፥ ሣሌፍንም፥ ሐስረሞትንም፥ ያራሕንም፥ ሀዶራምንም፥ አውዛልንም፥ ደቅላንም ዖበልን፥ አቢማኤልንም፥ ሳባንም፥ ኦፊርንም፥ ኤውላጥንም፥ ዩባብንም ወለደ፤ እነዚህ ሁሉ የዩቅጣን ልጆች ናቸው። ስፍራቸውም ከማሴ አንሥቶ ወደ ስፋር ሲል እስከ ምሥራቅ ተራራ ድረስ ነው። የሴም ልጆች በየነገዳቸውና በየቋንቋቸው፥ በየምድራቸውና በየሕዝባችው እነዚህ ናቸው። የኖኅ የልጆቹ ነገዶች እንደ ትውልዳቸው በየሕዝባቸው እነዚህ ናቸው። አሕዛብም ከጥፋት ውኃ በኍላ በምድር ላይ ከእነዚህ ተክከፋፈሉ።

ዘፍጥረት 10:21-32 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

የያፌት ታላቅ ወንድም ሴም የዔቦር ዘሮች ቅድመ አያት ነው። የሴም ልጆች፦ ዔላም፥ አሦር፥ አርፋክስድ፥ ሉድና አራም ናቸው። የአራም ልጆች፦ ዑፅ፥ ሑል፥ ጌተርና ሜሼክ ናቸው፤ አርፋክስድ ሼላሕን ወለደ፤ ሼላሕም ዔቦርን ወለደ። ዔቦር ሁለት ልጆች ወለደ፤ አንደኛው እርሱ በተወለደበት ዘመን ሕዝቦች ስለ ተከፋፈሉ ፋሌቅ ተባለ፤ ሌላው ዮቅጣን ይባል ነበር። የዮቅጣን ልጆች፦ አልሞዳድ፥ ሼሌፍ ሐጻርማዌት፥ ዬራሕ፥ ሀዶራም፥ ኡዛል፥ ዲቅላ፥ ዖባል፥ አቢማኤል፥ ሳባ፥ ኦፊር፥ ሐዊላና ዮባብ ናቸው፤ እነዚህ ሁሉ የዮቅጣን ዘሮች ናቸው። እነርሱ የኖሩበት ምድር በስተምሥራቅ ባለው በተራራማው አገር ከሜሻ እስከ ሰፋር ይደርስ ነበር። እነዚህ ሁሉ የሴም ዘሮች ናቸው፤ እነርሱ በተለያዩ ጐሣዎችና አገሮች ተከፍለው ይኖሩ ነበር፤ እያንዳንዱም ጐሣ የሚነጋገረው በራሱ ቋንቋ ነበር። እነዚህ በየነገዳቸው የተከፋፈሉ ሕዝቦች የኖኅ ዘሮች ነበሩ፤ ከጥፋት ውሃ በኋላ የምድር ሕዝቦች ሁሉ የተገኙት ከእነዚህ ከኖኅ ልጆች ነበር።

ዘፍጥረት 10:21-32 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ለሴምም ደግሞ ልጆች ተወለዱለት፥ እርሱም የያፌት ታላቅ ወንድምና የዔቦር ልጆች ሁሉ ቅድመ አያት ነው። የሴም ልጆች፦ ዔላም፥ አሦር፥ አርፋክስድ፥ ሉድ እና አራም ናቸው። የአራም ልጆች፦ ዑፅ፥ ሑል፥ ጌተር እና ሜሼክ ናቸው። አርፋክስድ ሼላሕን ወለደ፤ ሼላሕም ዔቦርን ወለደ። ዔቦር ሁለት ልጆች ወለደ፤ አንደኛው እርሱ በተወለደበት ዘመን ሕዝቦች ስለ ተከፋፈሉ ፋሌቅ ተባለ፤ ሌላው ዮቅጣን ይባል ነበር። የዮቅጣን ልጆች፦ አልሞዳድ፥ ሼሌፍ ሐጻርማዌት፥ ዬራሕ፥ ሀዶራም፥ ኡዛል፥ ዲቅላ፥ ዖባል፥ አቢማኤል፥ ሳባ፥ ኦፊር፥ ሐዊላና ዮባብ ናቸው፤ እነዚህ ሁሉ የዮቅጣን ዘሮች ናቸው። እነርሱ የኖሩበት ግዛት በስተ ምሥራቅ ባለው በተራራማው አገር ከሜሻ እስከ ሰፋር ይደርስ ነበር። የሴም ልጆች በየነገዳቸውና በየቋንቋቸው፥ በየምድራቸውና በየሕዝባቸው እነዚህ ናቸው። ከጥፋት ውሃ በኋላ የምድር ሕዝቦች፥ እነዚህ በየነገዳቸው የተከፋፈሉ የኖኅ ዘሮች ነበሩ፤ ሁሉም የተገኙት ከእነዚህ ከኖኅ ልጆች ነበር።