የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

1ኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 3

3
የዳዊትና የሰሎሞን ትውልድ
1በኬብሮንም ለዳዊት የተለወዱለት ልጆች እነዚህ ናቸው። በኩሩ አምኖን ከኢይዝራኤላዊቱ ከአኪናሆም፥ ሁለተኛውም ዳንኤል ከቀርሜሎሳዊቱ ከአቢግያ፤ 2ሦስተኛው አቤሴሎም የመዓካ ልጅ እርሷም የጌሹር ንጉሥ የተልማይ ልጅ ነበረች፥ አራተኛው አዶንያስ የአጊት ልጅ፤ 3አምስተኛው ሰፋጥያስ ከአቢጣል፥ ስድስተኛው ይትረኃም ከሚስቱ ከዔግላ፤ 4#2ሳሙ. 5፥4፤5፤ 1ነገ. 2፥11፤ 1ዜ.መ. 29፥27።ስድስቱ በኬብሮን ተወለዱለት፤ በዚያም ሰባት ዓመት ከስድስት ወር ነገሠ፤ በኢየሩሳሌምም ሠላሳ ሦስት ዓመት ነገሠ። 5#2ሳሙ. 11፥3።እነዚህ ደግሞ በኢየሩሳሌም ተወለዱለት፤ ከዓሚኤል ልጅ ከቤርሳቤህ አራት ልጆች እነርሱም ሳምዓ፥ ሶባብ፥ ናታን፥ ሰሎሞን፤ 6ከዚያም በኋላ ኢያቤሐር፥ ኤሊሱዔ፥ ኤሊፋላት፥ 7ኖጋ፥ ናፌቅ፥ ያፍያ፥ 8ኤሊሳማ፥ ኤሊዳሄ፥ ኤሊፋላት ዘጠኝ ነበሩ። 9እነዚህ ሁሉ ከቁባቶች ልጆች በቀር የዳዊት ልጆች ነበሩ፤ ትዕማርም እኅታቸው ነበረች።
10የሰሎሞንም ልጅ ሮብዓም ነበረ፤ ልጁ አቢያ፥ ልጁ አሳ፥ ልጁ ኢዮሣፍጥ፥ 11ልጁ ኢዮራም፥ ልጁ አካዝያስ፥ ልጁ ኢዮአስ፥ 12ልጁ አሜስያስ፥ ልጁ ዓዛርያስ፥ ልጁ ኢዮአታም፥ 13ልጁ አካዝ፥ ልጁ ሕዝቅያስ፥ ልጁ ምናሴ፥ 14ልጁ አሞጽ፥ ልጁ ኢዮስያስ ነበሩ። 15የኢዮስያስም ልጆች፤ በኩሩ ዮሐናን፥ ሁለተኛውም ኢዮአቄም፥ ሦስተኛውም ሴዴቅያስ፥ አራተኛውም ሰሎም ነበሩ። 16የኢዮአቄምም ልጆች፤ ልጁ ኢኮንያንና ልጁ ሴዴቅያስ ነበሩ። 17የምርኮኛውም የኢኮንያን ልጆች፤ ልጁ ሰላትያል፥ 18መልኪራም፥ ፈዳያ፥ ሼናጻር፥ ይቃምያ፥ ሆሻማ፥ ነዳብያ ነበሩ። 19የፈዳያ ልጆች ዘሩባቤልና ሰሜኢ ነበሩ፤ የዘሩባቤልም ልጆች፤ ሜሱላም፥ ሐናንያ፥ እኅታቸውም ሰሎሚት ነበረች። 20ሐሹባ፥ ኦሄል፥ በራክያ፥ ሐሳድያ፥ ዮሻብ-ሒሴድ አምስት ናቸው። 21የሐናንያም ልጆች ፈላጥያና የሻያ ነበሩ። የረፋያ ልጆች፥ የአርናን ልጆች፥ የአብድዩ ልጆች፥ የሴኬንያ ልጆች። 22የሴኬንያም ልጅ ሸማያ ነበረ። የሸማያም ልጆች ሐጡስ፥ ይግዓል፥ ባርያሕ፥ ነዓርያ፥ ሻፋጥ ስድስት ነበሩ። 23የነዓርያም ልጆች ኤልዮዔናይ፥ ሕዝቅያስ፥ ዓዝርቃም ሦስት ነበሩ። 24የኤልዮናይም ልጆች ሆዳይዋ፥ ኤልያሴብ፥ ፌልያ፥ ዓቁብ፥ ዮሐናን፥ ደላያ፥ ዓናኒ ሰባት ነበሩ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ