የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትንቢተ ዘካርያስ 13

13
1የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “በዚያን ጊዜ ለዳዊት ልጆችና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ከኃጢአታቸውና ከርኲሰታቸው የሚያነጻ ምንጭ ይከፈታል። 2በዚያን ጊዜ የጣዖቶችን ስሞች ከምድሪቱ ላይ አስወግዳለሁ፤ ዳግመኛም የሚያስታውሳቸው አይኖርም፤ የጣዖት ነቢያትንና ርኩሳን መናፍስትን አስወግዳለሁ። 3ማንም ነቢይ ነኝ ብሎ ቢነሣ የወለዱት አባቱና እናቱ በእግዚአብሔር ስም ሐሰትን ስለ ተናገርክ መሞት አለብህ ይሉታል፤ ትንቢትም ሲናገር ወላጆቹ ወግተው ይገድሉታል። 4በዚያን ጊዜ ማንኛውም ነቢይ ነኝ ባይ በሚያየው ትንቢታዊ ራእይ ያፍርበታል፤ ሰዎችንም ለማታለል ጠጒር ያለበትን ልብስ ለብሶ አይታይም። 5እኔ ገበሬ ነኝ እንጂ ነቢይ አይደለሁም፤ ከወጣትነቴ ጀምሮ የእርሻ መሬት ባለቤት ነኝ ይላል። 6አንድ ሰው ‘ታዲያ ይህ በሰውነትህ ላይ ያሉት ቊስሎች ምንድን ናቸው?’ ብሎ ቢጠይቀው ‘በወዳጄ ቤት የቈሰልኩት ነው’ ብሎ ይመልስለታል።”
የእግዚአብሔር እረኛ
7የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “ሰይፍ ሆይ! ተባባሪዬ በሆነው በእረኛዬ ላይ ንቃ! በጎቹ ይበተኑ ዘንድ እረኛውን ምታ! እኔም በታናናሾቹ ላይ እጄን አነሣለሁ። #ማቴ. 26፥31፤ ማር. 14፥27። 8በአገሪቱ ላይ ካሉት ሕዝቦች ከሦስቱ ሁለቱ እጅ ተመተው ይሞታሉ፤ ሆኖም ከሦስቱ አንዱ እጅ ይቀራል። 9እነርሱንም ወደ እሳት እጨምራቸዋለሁ፤ ብርም በእሳት እንደሚጠራ አጠራቸዋለሁ፤ ወርቅም እንደሚፈተን እፈትናቸዋለሁ፤ ከዚያን በኋላ ወደ እኔ ይጸልያሉ፤ እኔም እመልስላቸዋለሁ። እኔ ‘ሕዝቤ’ ብዬ እጠራቸዋለሁ፤ እነርሱም ‘እግዚአብሔር አምላካችን’ ብለው ይጠሩኛል።”

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ